TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ነገሩ ሁሉ በጥድፊያ ነበር የሆነው #በፌስቡክ የተለቀቀውን ፎቶ እንኳን መነሳቴን አላውቅም " -  ወ/ሮ አማረች ያዕቆብ

ከወር በፊት በመንግሥት የኮሚኒኬሽን ገጾች ፣  በመንግሥት ሚዲያዎች እና ከነዚህ በወሰዱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች አንዲት ሰራተኛ " መድሃኒት ሰርቃ ልትወጣ ስልት እጅ ከፍንጅ ተይዛ በቁጥጥር ስር ዋለች " የሚል ዜና መሰራጨቱ ይታወሳል።

ይህች ግለሰብ ወ/ሮ አማረች ያዕቆብ ትባላለች።

በወላይታ ዞን ፣ አባላ አባያ ወረዳ ከምትሰራበት የህክምና ተቋም ተረኛ ሆና ለሊት አድራ ልትወጣ እየተዘጋጀች በነበረበት ወቅት መድሀኒት ጠፋ ተብሎ ሲፈለግ ቆይቶ በመጨረሻ እርሷ ትያዛለች።

" መድሃኒቱ ግን የእርሷ ባልሆነ ጋወን ውስጥ መገኘቱን " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጻለች።

ወ/ሮ አማረች ፥ " መድሀኒት ስትሰርቅ እጅ ከፍንጅ ተያዘች " ተብላ በጥድፊያ ለእስር እና ለእንግልት መዳረጓን አስረድታለች።

ይህ ሳያንስ የመንግስት ኮሚኒኬሽኖች ገጾችና የመንግስት ሚዲያዎች ዜናውን በማህበራዊ ገጾቻቸዉ ማራገባቸዉ ለከፍተኛ የስነልቦና ጉዳት እንደዳረጋት ተናግራለች።

በመጨረሻ በእስር ቤት ውስጥ እያለች የደረሱላት የጠበቆች ቡድን እውነቱን አውጥተው ነጻ እንዳደረጓት ገልጻለች።

" እነሱ ባይደርሱልኝ ኖሮ ባልሰራሁት ወንጀል ወደ ወህኒ ልወርድ ነበር " ያለችው ወ/ሮ አማረች " ጉዳዩን አሁን ላይ ሳስበው ህልም መስሎ ነው የሚታየኝ " ብላለች።

በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን የሰጡት የጠበቆች ቡድን አባሉ ጠበቃና የህግ አማካሪዉ አቶ መብራቱ ኮርኪሳ ፥ " በደንበኛችን ላይ የቀረበዉ የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ #ነጻ_ተብላ_የመገመት መብቷን ከመጣስ ባለፈ ሁኔታዉን ለማጣራት ስንሞክርም ብዙ የሚያጠራጥሩ መረጃዎች ልናገኝ ችለናል " ብለዋል።

በዚህም በወላይታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተበዳዩዋን የዋስ መብት ከመጠየቅ አንስቶ " በነጻ በእስር እስክትወጣ ድረስ ታግለናል " ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላዉ የጠበቆች ቡድን አባሉ የህግ ጠበቃ እና መምህሩ አቶ አበባየሁ ጌታ ፤ " ክሱን ያቀረበባት አቃቤ ህግ ያቀረባቸዉ ምስክሮች በሰጡት ቃል ወንጀሉን እንዳልፈጸመች ማረጋገጡን ተከትሎ ፍ/ቤቱ በነጻ አሰናብቷታል " ብለዋል።

አሁን ላይ ነጻ ብትወጣም የደረሰባት የስም ማጥፋት ከፍተኛ የስነልቦና ጫና እንዳሳደረባት ጠቁመዋል።

ከዚህ በኋላ የሚቀረዉ በሚዲያ የጠፋዉን ስሟን የመመለስና ለደረሰባት ጉዳት ካሳ የመጠየቅ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ይህም በግለሰቧ ፍላጎት የሚመሰረት ነው ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia