TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምስራቅ ወለጋ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰው #ህይወትና ንብረት ላይ #ጉዳት መድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ ለfbc አንደተናገሩት፥ በግጭቱ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስን ጨምሮ የበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አልፏል።

እንዲሁም ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ በርካታ ንብረት መውደሙንም ነው አቶ ዴሬሳ የተናገሩት።

ችግሩ ያጋጠመውም ባሳለፍነው ማክሰኞ ህዳር 18 2011 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሊሙ ወረዳ አርቁምቤ በሚባል አካባቢ መሆኑንም ነው የቢሮው ምክትል ኃላፊ ያስታወቁት።

በግጭቱም በአካባቢው ነዋሪዎች እና በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ላይ አሰቃቂ ወንጀል ተፈጽሟል ያሉት አቶ ዴሬሳ፥ በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ እና የተጎዱ ሰዎች ቁጥር በቅርቡ ይፋ ይደረጋልም ብለዋል።

በግጭቱ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች አስክሬን በትናንትናው እለት ነቀምቴ ከተማ ሲገባ ህዝቡ ሰልፍ በመውጣት #ስሜታዊ በመሆኑ የአንድ ሰው #ህይወት ማለፉንም ተናግረዋል።

ምክትል ኃላፊው አቶ ዴሬሳ ተረፈ፥ በምእራብ ኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዋነኛ ምክንያት የክልሉን እና የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ እንዲሁም አሁን በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚሯሯጡ አካላት ናቸው ብለዋል።

የእነዚህ አካላት እቅድም እንደ ኦሮሚያ ክልል እና እንደ ሀገር እየመጣ ያለውን ለውጥ ማደናቀፍ በመሆኑ፤ ህዝቡ ከስሜታዊነት በመውጣት መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚወስደውን እርምጃ እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia