ትላንት ምሽት ከ4 ሰዓት በኃላ በአዲስ አበባ አንድ ስማቸውን መግለፅ የማያስፈልግ ግለሰብ #ታርጋ_በሌለው 2 ሎንግ ቤዝ መኪና በመጡ ወደ 20 በሚጠጉ የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ እና አብረዋቸው ሲቪል በለበሱ ሰዎች ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደው ነበር።
በኃላም ዛሬ ንጋት አካባቢ በቪ8 መኪና መንገድ ላይ ጥለዋቸው ሄደዋል።
የፀጥታ ኃይል ልብስ የለበሱና የታጠቁት ግለሰቦች በቅድሚያ በር በማንኳኳት የግቢው ጥበቃ በሩን ሲከፍትላቸው ገፍትረው በመግባት እኚሁን ግለሰብ ከቤት እየደበደቡ አስወጥተው መኪና ላይ ጭነዋቸው እንደወሰዷቸው ቤተሰቦቻቸውን ገልፀዋል።
በወቅቱ ቤት ውስጥ የነበሩ የቤተሰብ አባላት ጉዳዩን በስልክ ለመቅረፅ ቢሞክሩም መሳሪያ ደቅነው እየዳበደቡ ስልክ እንደቀሙባቸው አስረድተዋል።
"እነዚህ ግለሰቦች ማንነታቸውን የሚገልፅ አንድም ነገር አልያዙም፤በትክክል የህግ አካል ከሆኑም የፍ/ቤት መጥሪያ አላሳዩም፤ ምንም ነገር የላቸውም ልንጠይቃቸው ስንሞክር ማሳሪያ ደቅነው #እንዳትጠጉን ነው ያሉት፤ እንዳይሄዱ ለመከላከል ስንጮህ መሳሪያ እየተኮሱ ነው የሄዱት" ብለዋል።
በአቅራቢያው ፖሊስ ጣቢያ ስለነበር ፖሊስ ይዘው ቢመጡም ፖሊስ ባለበት እየተኮሱ ነው የሄዱት።
ከእኚሁ ግለሰብ ጋር የቤቱ ጥበቃ እና መንገድ ላይ የተያዙ 2 የአካባቢው ልጆችም ተወስደው የነበረ ሲሆን ሁሉም ፊታቸው ተሸፍኖ አንድ መጋዘን የሚመስል ቦታ እንደነበሩ ድብደባም እንደተፈፀመባቸው አስረድተዋል።
ግለሰቡ ከፖለቲካ ሆነ ከሌላ ማንኛውም ጉዳዮች ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ነገር ግን በግል ጉዳይ የፍ/ቤት ቀጥሮ እንደነበራቸው ትላንትም ፍ/ቤት እንደነበሩ ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል።
ትላንት የተፈፀመውን ድርጊት በተመለከተ ፖሊስ ቤት መጥቶ ቃል የተቀበለ ሲሆን ለፌዴራልና አ/አ ፖሊስ እንዲያመለክቱ አሳውቋቸዋል።
@tikvahethiopia