TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GamoZone

የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ። የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንደተናገሩት ከሞያሌ ኮንሶ አድርጎ በአርባ ምንጭ ወደ ማዕከል ከተሞች የሚንቀሳቀሰው ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ የጦር መሳሪያ በጸጥታው ስራ ላይ ጫና ከመፍጠሩም በላይ ህጋዊ ነጋዴዎች ከገበያ እንዲውጡ በማድረግ በሃገር እኮኖሚ ላይ አሉታዊ እየፈጠረ ነው፡፡

እንደ ኮማንደር ረታ ተክሉ ገለጻ ጥቅምት 23 /2012 ዓ/ም ከለሊቱ 6፡30 ገደማ የዞኑ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት አርባ ሁለት ካርቶን ሶስት ዓይነት የሰው መድሀንት ፣ሰላሳ አንድ ቦንዳ ልባሽ ጨርቅ የጫነ ኮድ 3 አአ 43366 አይሱዙ መኪና ከነ አሽከርካሪው በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው እየተጣራ ይገኛል፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ ኢንዶክትሪኔሽንና ህዝብ ግኑኝነት ሥራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር አዳነ ኦኬ እንደገለጹት የኮንትሮባንድ ንግድ በህጋዊ መንገድ የሚሰሩትን ነጋደዎች ከውድድር ውጭ በማድረግ መንግስት ከንግዱ ዘርፍ የሚያገኘውን ገቢ ከማቀጨጭም ባሻገር ህገውጥነትን በማስፋፋት በሀገር ደህንነትና በጸጥታ ስራው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ህብረተሰቡ በመረዳት ይህንን ህገወጥነት በመከላከል ረገድ ከፖሊስ ጎን እንድቆም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ከ2011 በጀት ዓመት ጀምሮ እስካሁን ከ19 ሚልዬን ብር በላይ የሚገመት የ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር መዋን ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ጋሞ ዞን - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GamoZone #EmbassyOfItaly

የጋሞ ዞን ከጣሊያን ኢምባሲ ጋር በመተባበር Italian Trade Agency (ICE) ከተባለ ድርጅት ጋር በአትክልትና ፍራፍሬ ምርት አቅርቦትና ማቀነባበር ዙሪያ ውይይት እየተካደ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ በአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበር የሚታወቁ ሶስት የጣሊያን ኩባንያዎች (Tropical Food Machinery, CERMAC,MACFIRUT) የተባሉ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን የአከባቢውን ምርት ማቀነባበር እና በቀላሉ ለአለም ገበያ ማድረስi በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከዞኑ አመራር፣ ከኢንቨስተሮች እና ህብረት ሥራ ማህበራትና ዩኒየኖች ጋር ተወያይተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GamoZone : አቶ ብርሃኑ ዘውዴ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል።

የጋሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር መረሀ ግብር 9ኛ ዓመት የሥራ ዘመን አስቸኳይ ጉባኤው አቶ ብርሃኑ ዘውዴን የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።

ሹመቱን ተከትሎ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia
#GamoZone

በጋሞ ዞን የሰዓት እላፊ ማሻሻያ ተደረገበት።

የጋሞ ዞን ኮማንድ ፖስት #ለተሽከርካሪዎች የሠዓት ማሻሻያ ማድረጉን ትላንት ምሽት አሳውቋል።

ኮማንድ ፖስቱ የዞኑ ሠላም እንዲጠበቅ ለማድረግ በቂ የሆነ የሕዝባዊ ሠራዊት በመሠልጠኑ እንዲሁም የህብረተሰቡ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዳይገደብ የሠዓት ማሻሻያ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ገልጿል።

በዚሁ መሠረት፦

- ለባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል እስከ ምሽቱ 3:00 ሠዓት

- ለባለሦስት እግር ባጃጅ እስከ ምሽቱ 4:00 ሠዓት ማሻሻያ ማድረጉን የዞኑ ኮማንድ ፖስት ገልጿል።

@tikvahethiopia
#GamoZone , #Arbaminch📍

" ጋሞ ወጋ ክፍል አንድ የጋሞ ሕዝብ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የሠላም ግንባታ ሥርዓት " በሚል ርዕስ በአቶ ዘነበ በየነ የተዘጋጀ መጽሐፍ ተመረቀ።

የመጽሐፉ አዘጋጅ አቶ ዘነበ በየነ መጽሐፉ ከተዘጋጀ ከ7 ዓመታት በኋላ ለሕትመት መብቃቱን ተናግረዋል።

8 ምዕራፎች ያሉት ባለ 105 ገጽ መጽሐፍ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ፦ የጋሞ ሕዝብ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ፣ የጋሞ ሕዝብ ታሪካዊ አመጣጥ እና አሰፋፈር ፣ ባህላዊ የአስተዳደር ሥርዓት ፣ ዘመናዊና ባህላዊ የግጭት አፈታት ፣ ግጭትን በመፍታት ወደ በጎ መለወጥ ፣ ሀገረሰባዊ የእርቅና የሽምግልና ዕውቀቶች ፣ ባህላዊ የግጭት አፈታትና የሠላም ግንባታ ተግዳሮቶች የያዘ መሆኑን አቶ ዘነበ አብራርተዋል።

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን ፣ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የመጽሐፉ ደራሲ አቶ ዘነበ በየነ ከዚህ በፊት " የጋሞኛ ምሳሌያዊ ንግግሮች እና ሌሎች ስነ ቃሎች በሚል መጽሐፍ አሳትመው ነበር ከጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia