TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢጋድ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) 13ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
ከሰሞኑን ተከታትለው የወጡት የተኩስ አቁም ጥሪዎች !

በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከጀመረ ሰዓት አንስቶ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ተኩስ እንዲቆም ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

ከሰሞኑን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት በተከታታይ የተኩስ አቁም እና የድርድር ጥሪዎችን ሲያቀርቡ ተስተውሏል።

1ኛ. #ሩሲያ፦ በድጋሚ ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጠይቃለች።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሩሲያ የኢትዮጵያን ጉዳይ እየተከታተለች እንደሆነ ገልፃለች ፤ ሰሞኑን በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የተካሄዱት ጦርነቶች የሲቪል ዜጎችን ህይወት ጎድቷል ብለዋል።

ሩሲያ #የኢትዮጵያን_ግዛት_አንድነት መከበር ለድርድር የማይቀርብ እና ግጭቱን መፈቻ መንገድ ሊሆን እንደማይችል ታምናለች ብለዋል።

2ኛ. #ኬንያ ፦ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም ኢትዮጵያውያን እንዲወያዩ አሳስበዋል።

ኬንያታ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ድርድር ይጀምሩ ሲሉ ጠይቀዋል።

ህወሓት እና ኦነግ ሸኔ የፌደራል መንግስቱን ለመውጋት ቅንጅት መፍጠራቸው ጦርነቱ ሌላ መልክ እንዲኖረው እና እንዲራዘም እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፌደራል መንግስቱ እና በህወሃት መካከል እስካሁን ትርጉም ያለው ድርድር አለመጀመሩ ጦርነቱ ከአንድ ዓመት በላይ እንዲቀጥል አድርጎታል ብለዋል ኡሁሩ።

ኬንያን ጨምሮ አፍሪካ እና ዓለም ሰላማዊ ኢትዮጵያን ማየት ይፈልጋል ያሉም ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመካክሮ ለአገሩ ሰላም መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

3ኛ. #ኢጋድ ፦ የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጦርነት እንዲቆምና አስቸኳይ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ፥ እየከረረ መጥቷል ያሉትን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።

ኢጋድ ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት ባለፈው ዓመት ሁኔታውን በማስመልከት ጥሪ ማቅረቡን ያስተወሱት ዶ/ር ወርቅነህ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ከግጭት ተቆጥበው በመካከላቸው ያለውን መካረር እንዲያረግቡ እና ልዩነቶቻቸውን ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እና እርቅ እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል።

4ኛ. #ዩጋንዳ ፦ ፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አባል ሐገራት መሪዎች ጦርነቱ ሥለሚቆምበት ሁኔታ ለመነጋገር እንዲሰበሰቡ ጠይቀዋል።

5ኛ. #አሜሪካ ፦ ዛሬም (ጥቅምት 26) አሜሪካ በድጋሚ በኢትዮጵያ ተኩስ ይቆም ዘንድ ጥሪ አቅርባለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ማብቃት አለበት ፤ አሁኑኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ድርድር መጀመር አለበት ብለል፤ ተኩስ እንዲቆምም ጠይቀዋል።

6ኛ. #AU ፦ የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኢትዮጵያ ያለው ወታደራዊ ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸውና በቅርበትም እየተከታተሉት እንደሆነ ገልፀዋል።

ጦርነቱ በተቀሰቀሰበት ሰሞን ያወጡትን መግለጫ በማስታወስ የጦርነቱ ተሳታፊ ሁሉም ወገኖች የኢትዮጵያን ግዛት አንድነት፣ ብሄራዊ ሉዓላዊነት እንዲጠብቁ በድጋሚ አሳስበዋል።

በአገር ጉዳይ ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲገቡም አሳስበዋል።

ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የዜጎች ህይወትና ንብረት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር፣ እንዲሁም የመንግስት መሠረተ ልማት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።

የጦርነቱ ተሳታፊ ወገኖች ደጋፊዎቻቸው በማንኛውም ማህበረሰብ ላይ የበቀል እርምጃ እንዳይወስዱ እንዲሁም ከጥላቻ ትርክቶች፣ ክፍፍልንና ግጭቶችን ከሚያበረታቱ ሁኔታዎች እንዲቆጠቡ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

በሌላ መረጃ ፦

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውንና ለድርድር የሚሆን ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚሰጡ እንደገለጹላቸው አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ UN ፣ AU ፣ ኢጋድ ፣ አል አይን ኒውስ ፣ Daily Nation ፣ António Guterres (Twitter) ፣ BBC ፣ Antony Blinken (Twitter)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አውሮፓ ህብረት ምን አለ ? የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ አጭር መግለጫን ትላንት ምሽት አውጥቶ ነበር። በዚህ መግለጫው፤ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ  የባህር በር አገልግሎት (በሊዝ) ማግኘት የሚያችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል…
#ኢጋድ #ሶማሊያ

ዛሬ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲላፕሎማሲው መስክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት መካከል እያታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ኢጋድ ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ መሆኑን እና በቀጠናው መረጋጋት ላይ ያለውን ተፅእኖ እንደሚገነዘብ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁኔታዎችን በሰላማዊ እና በመግባባት መንፈስ ለመፍታት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር ወርቅነህ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ስለተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ያነሱት ነገር የለም።

የሶማሊያ መንግሥት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ እንዳበሳጨው ለመረዳት ተችሏል።

የሶማሊያ መንግሥት " የመግለጫው ሃሳብ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው " በማለት ዶ/ር ወርቅነህ በአስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ የይቅርታ መግለጫም በማውጣት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ብሏል።

ሶማሊያ ፤ የኔ አንድ ግዛት ናት በምትላት ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተረፈመው ስምምነት ያበሳጫት ሲሆን ስምምነቱ የግዛት አንድነቴን እና ሉዓላዊነትን የጣሰ ነው በማለት እየተቃወመች ትገኛለች።

(የሁለቱም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia