TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የማህበራዊ ሚዲያ ህግ‼️ በእኔ ምልከታ በኢትዮጵያ የሚተገበረው የማህበራዊ ሚዲያ ህግ በርካታ ችግሮችን ሊቀርፍ የሚችል ነው። እንያንዳንዱ ሰው ለሚያሰራጨው መረጃ ተጠያቂ ሊሆን ይገባል። የሀገርን ሰላም #በሀሰተኛ መረጃ የሚያደፈርሱና በህዝቦች መካከል መቃቃርን በሚፈጥሩ እንዲሁም ህዝቡን የሚያሸብሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከያሉበት ተለቅመው ለህግ የሚቀርቡበትን መንገድ የሚያመቻች ይሆናል ብዬ ገምታለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake Page Alert‼️

አልጀዚራ-የአማርኛ የፌስቡክ ገፅ የለኝም በፌስቡክ ላይ ተከፍተው የምትመለከቷቸውም #ሀሰተኛ/Fake የፌስቡክ ገፆች ናቸው ብሏል። የአልጀዚራ ባልደረባ በኢትዮጵያ እንደነገረችን #በሀሰተኛ ገፆቹ ላይ የሚተላለፉት መረጃዎች ወይም መልዕክቶች አልጀዚራን የሚወክሉ አይደሉም፤ህዝቡም ይህ ይወቅልን ብላለች።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሁለት ተሽከርካሪን ጨምሮ 4.7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። መነሻው ኬንያ እንደሆነ የተገመተ 3,251,800 ብር የሚያወጣ የብር ጌጣጌጥ ሞያሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ በፍተሻ ተይዟል፡፡

የብር ጌጣጌጡ መጠኑ 65.3 ኪ.ግ እንደሆነ የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-36031 ኦሮ በሆነ ሃይሩፍ ተሽከርካሪ ወደ መሀል ሀገር በመጓጓዝ ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡ በኮንትሮባንድ ድርጊቱ የተጠረጠረ አንድ ግለሰብም ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ በተመሳሳይም በቀን 06/12/2011-09/12/2011 በተለያዩ ኬላዎችና የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች የተያዙ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ዋጋዉ 1.5 ሚሊየን ብር የሚገመት ፓስታ አወበሬ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ተይዟል፡፡

እንዲሁም #በሀሰተኛ የሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኮድ 3- 03068 ድሬ ሃይሉክስ ተሽከርካሪ እና በቱሪስት መልክ በመተማ በኩል የገባ ኮድ2-07207 ኦሮ ተሸክርካሪዎች ጅግጅጋ እና በአዳማ ከተማ መያዙን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲአን ትክክለኛው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የፌስቡክ ገፅ ይህ 5,740 like ያለው ነው። ከዚህ ቀደም ዋዜማ ሬድዮና ሌሎች ስለሀዋሳው የቀድሞ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ መረጃ አገኘን ብለው ያሰራጩት ከዚህ ትክክለኛ ገፅ የተወሰደ አይደለም። በሌላ አገላለፅ #በሀሰተኛ ገፅ ተታለው ነበር።

የሲአን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 5,740 like ያለው ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በማዕከላዊ ጎንደር ዞን #በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ያለአግባብ ደመወዝ ሲከፈላቸው በነበሩ 95 ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰዱን የዞኑ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር መምሪያ አስታውቋል።

https://telegra.ph/ETH-09-25-7

@tsegabwolde @tikvahethiopia