TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን የሚቀበሉበት ሥነ ሥርዓት ነገ ማክሰኞ፤ ኅዳር 30 / 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ምሽት በኖርዌይ የኖቤል ተቋም የክብር እንግዳ መዝገብ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክብር እንግዳ መዝገቡ ላይ በአማርኛ አስተያየታቸውን ያሰፈሩ የመጀመሪያው ሎሬት መሆናቸውን ከኖርዌይ የኖቤል ተቋም የፌስቡክ ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ኢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን ለጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ከመስጠታቸው በፊት ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚንሥትሩ ለሰላም ላበረከቱት አስተዋጽዖ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማስፈን በርካታ ርምጃዎችን መውሰዳቸው እንዲሁም በካቢኔያቸው አምሳ በመቶ ሴቶችን መሾማቸዉ ተመስግኗል። በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የሰላም ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል፣ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሣኅለ-ወርቅ ዘውዴ እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ማአዛ አሸናፊ ሴቶች መኾናቸውን ሊቀመንበሯ አመስግነዋል።

ሽልማቱም የተሰጠው፦ ሰላም እና ብልጽግና በኢትዮጵያ ለማስፈን ዓልመው መነሳታቸው ሊቀመንበሯ ገልጠዉ የኖቤል ኮሚቴዉ ዕውቅና ሰጥቶታል። በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሰላም እንዲሰፍን ጠቅላይ ሚንስትሩ ላበረከቱት አስተዋጽዖም በኮሚቴው ተመስግነዋል።

ኤርትራ እና ጅቡቲ ሰላም እንዲፈጥሩ ጥረት መደረጉ፤ በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ሰላማዊ መፍትኄዎችን እንደ አማራጭ መወሰዳቸው ተወድሷል። «ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ ናት» ያሉት የኖቤል ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቤሪት ራይስ አንደርሰን፤ «የመጀመሪያው ሆሞ ሴፒያን የፈለሰው ከእርስዎ [ጠ/ሚ ዐቢይ]ሀገር ነው፣ በዚህም እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን» ብለዋል። ኢትዮጵያ በአዉሮጳዉያን ቅኝ አለመገዛትዋ፤ የአፍሪቃ ኅብረት መቀመጫ መኾኗ ከመድረኩ ሲገለጥም ሞቅ ያለ ጭብጨባ ከታዳሚያን ተሰምቷል።

(DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

የዓለም የኖቤል የሰላም ሎሬት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ማለዳ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆን ሽልማታቸውን ከትናንት በስቲያ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ደማቅ ስነ ስርዓት መቀበላቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አዲስ አበባ ሲደርሱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ለክብራቸውም 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።

(ኤፍቢሲ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NobelPeacePrize #AbiyAhemed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያገኙት የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አንደኛው ሜዳሊያና ዲፕሎማ በብሔራዊ ሙዚየም የማስቀመጥ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።

(📸ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AbiyAhemed #LemmaMegersa

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና የመከላከያ ሚኒስትሩ ለማ መገርሳ መካከል የነበረ አለመግባባት "በበሳል የድርጅታችን ስራ አስፈጻሚ አመራሮችና በቀድሞ የትግል ጓዶች" ተፈቷል ሲል የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ አስታውቋል። ዶ/ር አብይ እና አቶ ለማ በጋራ ለመታገል ተስማምተዋል።

(እሸት በቀለ - ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AbiyAhemed #LemmaMegersa

አቶ አዲሱ አረጋ ዛሬ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት በአስተዳራዊ ስርዓት በተለይም እንደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታና አዳዲስ ሀሳቦችና የፓርቲ ሪፎርሞች በሚካሄዱበት ወቅት የሀሳብ ልዩነቶች ሊኖሩ ቢችሉም የሀሳብ ልዩነት በራሱ ችግር እንዳልሆነ ገልጸው ትልቁ ጉዳይ ይህን የሀሳብ ልዩነት እንዴት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንፈታዋለን የሚለው ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

አቶ አዲሱ በቅርቡ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ ለመገናኛ ብዙሃን በመደመር ፍልስፍና እንዲሁም በፓርቲው ውህደት እንደማይስማሙ የገለጹትን ጠቅሰው ይህንን ጉዳይ በኦሮሞ ባህልና ስርዓት መሰረት የቀድሞ የኦዲፒ የስራ አመራሮች ሌሎችም ኃላፊዎች በተገኙበት የበሰለ ውይይት በማድረግና የነበሩ ልዩነቶችን በማጥበብ ከዚህ በኃላም አንድነትን አጠናክሮ አብሮ ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል፡፡

አቶ አዲሱ አክለውም ፓርቲያቸው በዲሞክራሲ ባህል እና በኦሮሞ ባህልና ስርዓት የውስጥ ችግሩን ለመፍታትና ህብረተሰቡ ያለውን ጥያቄ ሁሉ ለመፍታት የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AbiyAhemed #IsaiasAfwerki

የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ እና የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክንና ገልመ አባገዳን ጎበኙ!

በትናንትናው ዕለት ለይፋዊ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክን እና ገልመ አባገዳን ጎብኝተዋል።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለመሪዎቹ አቀባበል አድርገዋል።

የአዳማ ሕዝብ ለመሪዎቹ ደማቅ አቀባበል ከማድረግም ባሻገር በኦሮሞ ሕዝብ ባህል እና እሴት መሠረት የፈረስ ስጦታ እንዳበረከተላቸው ከኦቢኤን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(OBN)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AbiyAhemed #IsaiasAfwerki

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ ለሚገነባው የኤርትራ ኤምባሲ ህንፃ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ። ሀምሌ 19 መናፈሻ አካባቢ ለሚገነባው ለዚህ ኤምባሲ ሁለቱ መሪዎች የመሰረት ድንጋዩን በጋራ አስቀምጠዋል።

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AbiyAhemed #IsayasAfewerki

የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የስራ ጉብኝት...

- የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በመሆን አዲስ አበባ ውስጥ በእንጦጦና አካባቢው የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና በኢትዮጵያ ጉበኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአዳማ የኢንዱሰትሪ ፓርክን ዛሬ ጎብኝተዋል።

- የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዱከም የሚገኘውን የኢስተርን ኢንዱሰትሪ ዞንን ጎብኝተዋል። በኢንዱስትሪ ዞኑ ውስጥ የሚገኘውን ኤስ ኤስ ፒ የተባለን የመድሃኒት ፋብሪካን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘውን የሆላንድ የእንሰሳት እርባታ እና የወተት ተዋፅኦ ማቀነባበሪያን ጎብኝተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot