TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ቢሾፍቱ⬆️

ከአዲስ አበባ የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ #ወጣቶች #የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቢሾፍቱ በዓሉ የሚከበርበትን አከባቢ #አፀዱ። ወጣቶቹ በመጪው እሁድ የኢሬቻ በዓል በድምቀት የሚከበርበትን ስፍራ ከቢሾፍቱ ከተማ ወጣቶች ጋር በመሆኑን ማፅዳታቸው ተነግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የ2011 ዓ.ም የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚመጡ እንግዶችን በመልካም ለማስተናገድ መዘጋጀታቸውን የቢሾፍቱ እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል። #የኢሬቻ በዓል በየዓመቱ መስቀል ባለፈ በመጀመሪያ እሁድ በቢሾፍቱ #ሆራ_አርሰዲ ሀይቅ የሚከበረውን በዓል ለማክበር በርካታ እንግዶች ከውጭም ከውስጥም በቢሾፍቱ ይሰባሰባሉ።

ምንጭ፦ የመንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የኢሬቻ የሰላም ሽልማት🕊

ሀገር በቀል ባህሎችን በማጎልበት ለሀገራዊ ፋይዳ ማዋል አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል። የመጀመሪያው #የኢሬቻ የሰላም ሽልማት ትላንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የVOAን ዘገባ አድምጡት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቢሾፍቱ⬆️

#የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ከጋሞ ብሔረሰብ የመጡ አባቶችና ወጣቶች #ቢሸፍቱ ደረሱ። #የኦሮሞ አባ ጋዳዎችም እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለዋቸዋል። የኢሬቻ በዓል የክረምቱ ወራት አልፎ የበጋው ወራት በመጀመሩ ለአምላክ #ምስጋና የሚቀርብበት በዓል በመሆኑ የሁላችንም በዓል ነው እንኳንም የኛን በዓል #በዓላቸሁ አድርጋችሁ ለማክበር በመምጣታችሁ እናመሰግናለን ብለዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2011 በሰላም ተጠናቋል!

Ofkollee Jirra!
Ayyaanni Irreechaa guddichi bara 2011 bakka Oromootni fi ummatni obbolaa miliyoonotaan lakkaawaman argamanitti haala miidhagaa ta'een nagaan kabajamee xumuramee jira!
Baga Gammadne!

የዘንድሮው ታላቁ #የኢሬቻ በዓል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የኦሮሞ ህዝብ ወዳጆች እና ወንድም ሕዝቦችን በማሳተፍ እጅግ ደማቅ በሆነ ስነ ስርዓት በሰላም ተጠናቋል። እንኳን ደስ አለን!

ምንጭ፦ አቶ አዲሱ አረጋ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦቦ ለማ መገርሳ⬇️

የዘንድሮ #የኢሬቻ በዓል አንድነታችንንና ሰላማችንን ለማወክ ለሚፈልጉ ትልቅ መልዕክት አስተላልፏል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ አቶ ለማ በቢሾፍቱ ከተማ ዛሬ የተከበረውን የ”ኢሬቻ” በዓል አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በዓሉ ፍጹም ሰላማዋዊ እንደነበር ገልጸዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ታላቅ አስተዋጽኦ ላበረከተው መላው ህብረተሰብ ምስጋና አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ ልዩ አስተዋጽኦ ለነበራቸው ለአባ ገዳዎች ምክር ቤት፣ ለክልሉ ወጣቶች (ፎሌ)፣ ለኦሮሚያ ክልል ፖሊስ፣ ለፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት አባላት እንዲሁም ለቢሾፍቱ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ምስጋና አቀርበዋል።

ዘንድሮ በዓሉ ሰላማዊ ከመሆኑም ባሻገር ከክልሎች በስፍራው የተገኙና በበዓሉ ላይ የታደሙ ብሄር ብሄረሰቦች ልዩ ድምቀት እንደሰጡት ነው የገለጹት።

ይህም ብሄር ብሄረሰቦች በጋራ ከቆሙ ሁሉንም ነገር ማሳካት እንደሚችሉ ማሳያ ሆኖ ማለፉን ጠቁመዋል።

በዓሉ #ሊከፋፍሉን ለሚፈልጉ፣ ትልቅ መልዕክት ማስተላለፉን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ቅዳሜ የሚከበረው " #የኢሬቻ_ሆራ_ፊንፊኔ በዓል " ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

ከነገ ዓርብ መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቅ ድረስ ፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒዬም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ወሎ ሰፈር አደባባይ

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ 22 ማዞሪያ

- ከ4ኪሎ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መስቀለኛ ወይም ወዳጅነት ፓርክ

- ከፒያሳ በቸርቸር ጎዳና  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከጦር ሃይሎች በለገሃር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት

- ከጀሞ በትንባሆ ሞኖፖል ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

- ከቄራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚሄደው መንገድ ቡልጋርያ ማዞሪያ

- በአዲሱ መንገድ ከቄራ በቂርቆስ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ታቦት ማደሪያ

- ከሳሪስ ፣ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎተራ ማሳለጫ

- ከቦሌ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ  አትላስ ሆቴል አካባቢ

- ከአዋሬ ወደ ካሳንቺዝ  የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ

- ከልደታ በጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ የሚወስደው መንገድ አብነት ፈረሰኛ ፖሊስ አካባቢ

- ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ አምስተኛ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ

- ከመርካቶ በራስ ቴአትር ወደ ጎማ ቁጠባ ተክለ ሃይማኖት አደባባይ

መንገዶች ከነገ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት በ991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52- 63-02/03 ፣ 011-542-40-77፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987 ፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች መጠቀም እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethiopia