TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ጥቃት አድራሾቹ #ባልና #ወንድም በቁጥጥር ስር ውለዋል " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ

ትላንት በባለቤቷ እንዲሁም በባለቤቷ እህት እና ወንድም  ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባት ገልጻ የህግ ድጋፍ ስለጠየቀችው ወይዘሮ አበባ ቦረና መረጃ ማጋራታችን ይታወሳል።

ጥቃት የደረሰባት ግለሰብ በሀላባ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ጥቃት ካደረሰባት ባለቤቷ ጋር 4 ልጆች አፍርታለች።

ወ/ሮ አበባ " ተሰብስበዉ ሲደበድቡኝ ለመገላገል የገባዉን የመጀመሪያ ልጃችንም የጥቃቱ ሰለባ ሆኗል " ማለቷ አይዘነጋም።

በጉዳዩ ላይ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሀላባ ዞን ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ  አቶ ሙደሲር ጉታጎ ፥ " የሴት ልጅን ጥቃት አንታገስም " በማለት ከሀላባ ከተማ ፖሊስ ጋር በመተባበር ሁኔታውን መመልከት እንደጀመሩ ገልጸው ነበር ።

ዛሬ አቶ ሙደሲር ባደረሱን መረጃ ጉዳቱን ካደረሱ በኋላ ተደብቀዉ የነበሩት ወንድማማች ጥቃት አድራሾች ፖሊስ ባደረገዉ ጥረት ተገኝተው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አቶ ሙደሲር የግል ተበዳዩዋን በስልክ ደውለዉ ማነጋገራቸውን ገልጸውልናል።

" አሁን ላይ ሰዎቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል " ያሉት ኃላፊው " ህጋዊ ምርመራ እንዲካሄድ ተበዳይ ሰኞ በአካል ቀርባ ክስ መመስረት ትችላለች " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia