TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመምህራን ሰላማዊ ሰልፍ👆

መምህራን ለጥያቄዎቻቸው ተገቢ ምላሽ እንዲሰጣቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ፡፡ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የመልካም አስተዳደር እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች የተስተጋቡባቸው ሰላማዊ ሰልፎች በመምህራን ተካሂደዋል፡፡

የመምህራን የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ አሰጣጥ ደንብ ይከበር፤ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ይመለሱ፤ የትምህርቱ ዘርፍ በፖለቲከኞች ሳይሆን በባለሙያዎች ይመራ፤ የመምህራን ሙዊ ነጻነት ይከበር፤ መምህራን ለክልሉ ሰላም እና ለትምህርት ጥራት ኃላፊነታችንን እንወጣ የሚሉ መልዕክቶች በሰልፎቹ ተስተጋብተዋል፡፡

በሁሉም ክልሎች መፈናቀል ይቁም፤ አስተማማኝ ሰላም ይስፈን፤ ለመምህራን ሙያ ልዩ ትኩረት ይሰጠው የሚሉ መልዕክቶችም ቀርበዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ መምህራን እንደ አጠቃላይ ትምህርት መምህራን የደረጃ ዕድገት ይፈቀድ፤ የሙያ ላይ ደኅንነትም ይከበርልን በማለት ጠይቀዋል፡፡

ደብረ ታቦር ላይ በተካሄደው ሰልፍ ደግሞ በከተማዋ የመብራት እና የንጹህ መጠጥ ውኃ ችግሮች እንዲቀረፉም ተጠይቋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በመምህራኑ የቀረቡ ጥያቄዎችን በማስመልከት ለአብመድ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የደመወዝ እና የጥቅማጥቅም ጥያቄው ተገቢ በመሆኑ መስተካከል አለበት ተብሎ ታምኖበት በፌዴራል መንግሥት ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ጥያቄውም ተገቢ በመሆኑ ለዚህ በጀት ዓመት ብቻ 230 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው ዶክተር ይልቃል የገለጹት፡፡ ጉዳዩ የሀገሪቱን አቅም እና የአጋር አካላትን ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ በቶሎ ምላሽ ለመስጠት ስላስቸገረ እንጅ በትኩረት እየተሰራበት ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

የሙያ ነጻነትን በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ ደግሞ በመምህራን ሙያ ምንም አይነት #ጣልቃ ገብነት እንደማይኖር አረጋግጠዋለ፡፡

በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች አሰልጣኝ መምህራን ለተነሱ ጥያቄዎች ደግሞ የክልሉ ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሻምበል ከበደ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የደረጃ ዕድገት አያያዝ በበጀት የሚመራ በመሆኑ በግል ትምህርታቸው ያሻሻሉ አሰልጣኞች መረጃ አስቀድሞ መታወቅ እንዳለበት ነው ያስገነዘቡት፡፡ ይህ ካልሆነ #ስለመማራቸው መረጃ ሳይኖር በጀት ለመያዝና ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚያስቸግርም ነው የተናገሩት፡፡

በመምህራኑ ለተነሱ ጥያቄዎች ሀገራዊ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ ያስገባ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia