TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመረጃ ሳጥኑ ወደ ፈረንሳይ ተልኳል‼️

ባሳለፍነው እሁድ #የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላን የበረራ መረጃ ሳጥንና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ ለምርመራ ወደ ፈረንሳይ መላኩ ተገለፀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዳስታወቀው፥ በአደጋ ምርመራ ቢሮ የሚመራ የኢትዮጵያ ቡድን የበረራ መረጃ ሳጥን እና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ በመያዝ ለቀጣይ ምርመራ ወደ ፓሪስ #ፈረንሳይ አቅንቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ተወልደ ገብረማርያም በትናንትናው እለት ከአሜሪካው ሲ.ኤን.ኤን የቴሌቪዥ ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ የአውሮፕላኑ የመረጃ ሳጥን መመርመሪያ መሳሪያ ስለሌላት ለምርመራ ወደ ውጭ ይላካል ማለታቸው ይታወሳል።

አቶ ተወልደ፥ አውሮፕላኑ የበረራ መረጃ ሳጥንና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ ምርመራ ከቅርበትና ከፍጥነት አኳያ  ወደ አውሮፓ ሀገራት ሊላክም ይችላልም ብለው ነበር።

በዚህም መሰረት ነው የአደጋ ምርመራ ቢሮ የሚመራ የኢትዮጵያ ቡድን የበረራ መረጃ ሳጥን እና የበረራ መቆጣጠሪያ ክፍል መቅረፀ ድምፅ በመያዝ ለቀጣይ ምርመራ ወደ ፈረንሳይ ያቀናው።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ የአደጋ ምርመራ ቢሮ የተመራ ልዑካን ቡድን #የበረራ_መረጃ መመዝገበያ እና የአብራሪዎች ክፍል #የድምጽ_መቅጃ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ #ፈረንሳይ_መዘጓዙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር የጉዞ እገዳ ያደረገችባቸው ሀገራት 9 ደርሰዋል። ሀገራቱ ፦ ቻይና ፣ ፈንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ደቡብ ኮሪያ ፣ እንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ስፔን እና ኢራን ናቸው። ከዚህ ቀደም በእገዳው ውስጥ ያልተካተተችው #ፈረንሳይ እገዳው ተጥሎባታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

➡️ #አሜሪካ - በኒውዮርክ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። ሰልፉ በመሳሪያ የገዙ ጥቃቶችን ለማውገዝ የተካሄደ ነው። ሰልፉ የተካሄደው አንድ ወጣት በቴክሳስ ሮብ በሚሰኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 19 ህፃናት ተማሪዎችን እና 2 መምህራንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ ከቀናት በኃላ ነው።

➡️ #ስፔን - በሰሜናዊ ስፔን ላ ሪዮጃ ክልል በባዮዲዝል ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 2 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

➡️ #የመን - በየመን አደን ከተማ ሰዎች በሚበዙበት በተጨናነቀ ገበያ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 4 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል፤ እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዳለሁ ብሎ ብቅ ያለ የለም።

➡️ #ሱዳን - ከወራት በፊት በሱዳን የተካሄደውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም ያልበረደ ሲሆን ትላንትና በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በካርቱም ጎዳናዎች ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል። የጥቅምቱ መፈንቅለ መንግስት ሀገሪቱን ወደ ፖለቲካዊ ቀውስ አስገብቷል።

➡️ #ጣልያን - የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ የሩሲያው ፕሬዜዳንህ ፑቲን አሁን ላይ በዓለም የሚየው የምግብ ችግር "በሩሲያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ነው " ብለው እንደነገራቸው ተናግረዋል። የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ አንስቶ ምዕራባውያን ሀገራት ሩስያ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሚባሉ ማዕቀቦችን እየጣሉ እንደሆነ ይታወቃል። ለእነዚህ ማዕቀቦችም ሩስያ ምላሽ ከመስጠት ወደኃላ አላለችም።

➡️ #ቱርክ #ፈረንሳይ - የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከፈረንሳይ ፕሬዜዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የስውዲን እና ፊንላንድ ለNATO አባልነት ባቀረቡት ማመልከቻ፣ በዩክሬን ሩስያ ጦርነት፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተገናኝተው መክረዋል።

@tikvahethiopia
#ይገምቱ

የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማን ይሆናል ?

#ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና ከ12:00 ጀምሮ የዓለም ዋንጫው ባለድል ለመሆን ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ።

የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል ? የዋንጫው ባለቤት የሚሆነውን #ሀገር በትክክል ለመገመቱ 20 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ250 የሞባይል ብር ካርድ በሥጦታ የምናበረክት ይሆናል።

20 ትክክለኛ ገማቾች የሚለየቱ መልዕክቱን በላኩበት ቅደም ተከተል ነው።

ግምቱን መላክ ሚቻለው ጨዋታው እስከሚጀምርበት ደቂቃ ድረስ ብቻ ሲሆን #Edit የተደረገ ምላሽ ተቀባይነት አይኖረም።

(ግምትዎን #ከታች_ባለው የአስተያየት ማስቀመጫ ላይ ያኑሩ ፤ ፈረንሳይ ወይስ አርጀንቲና ? ከሁለቱ ሀገራት አንዱን ብቻ ይምረጡ ፤ ውጤት / በቁጥር መገመት #አያስፈልግም )

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይገምቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ማን ይሆናል ? #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና ከ12:00 ጀምሮ የዓለም ዋንጫው ባለድል ለመሆን ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጋሉ። የኳታሩን የዓለም ዋንጫ ማን ያሸንፋል ? የዋንጫው ባለቤት የሚሆነውን #ሀገር በትክክል ለመገመቱ 20 የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የ250 የሞባይል ብር ካርድ በሥጦታ የምናበረክት ይሆናል። 20 ትክክለኛ ገማቾች የሚለየቱ መልዕክቱን በላኩበት ቅደም ተከተል…
#Update #WorldCup

በFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እያደረጉ የሚገኙት #ፈረንሳይ እና #አርጀንቲና መደበኛ 90 ደቂቃውን በ2 ለ 2 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

ምንም እንኳን አርጀንቲና በሜሲ እና ዲማሪያ ጎል የመጀመሪያውን አጋማሽ በበላይነት ብታጠናቅቅም ፈረንሳይ በሁለተኛው አጋማሽ ቡድኗን አጠናክራው በወጣቱ ምባፔ ሁለት ጎሎች አቻ መሆን ችላለች።

ጨዋታው አቻ መሆኑን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ አምርቷል።

ይህን የዓለም ሀገራት የእግር ኳስ ዋንጫ ፍልሚያ ሚሊዮኖች እየተከታተሉት ይገኛሉ። ማን አሸናፊ ይሆን ?

More : https://t.iss.one/tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከፍትሕ ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው " ካለፉት 22 ዓመታ ጀምሮ ሽሽት ላይ የነበረውና በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወቅት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተክርስቲያን የተሸሸጉ 2,000 (ሁለት ሺህ) ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የተጠረጠረው ፉልጌንሴ ካይሼማ መያዝ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች #ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው ተብሏል። የተባበሩት…
የዘር ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፈው የፖሊስ መኮንን ከዓመታት በኃላ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።

ፈረንሳይ ሀገር የሚገኝ ፍርድ ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል በተከሰሰ አንድ የቀድሞ የሩዋንዳ ፖሊስ መኮንን ላይ የዕድሜ ልክ እሥራት መፍረዱን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (ኤኤፍፒ)ን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

ስሙ ፊሊፔ ሄትጌኪማና የተባለው ሩዋንዳዊው የፖሊስ መኮንን ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት በተፈጸመው የጅምላ ፍጅት ወቅት የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል መፈፀሙ ተረጋግጧል።

የፖሊስ መኮንኑ ወንጀሉን የፈፀመው በፈረንጆቹ 1994 በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ወቅት ነው።

በወቅቱ የሁቱ ታጣቂዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎችን መግደላቸው ይታወሳል።

የፈረንሳይ ዐቃቤ ሕግ እንደሚለው ግለሰቡ እሱ ራሱ የሰዎችን ነብስ ከማጥፋቱም በላይ #ሌሎች ግድያ እንዲፈፅሙ #ያነሳሳ ነበር።

ፊሊፔ በጅምላ ግድያው ወቅት ኒያንዛ በተሰኘችው የደቡብ ሩዋንዳ አካባቢ የፖሊስ መኮንን ሆኖ ያገለግል ነበር።

ነገር ግን የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ካቆመ በኋላ ወደ #ፈረንሳይ አቅንቶ ለአስርታት ማንነቱ ደብቆ ሲኖር ቆይቷል።

ግለሰቡ ፈረንሳይ ከገባ በኋላ መጀመሪያ የስደተኛ ወረቀት አግኝቶ፤ ቀጥሎ ደግሞ ፊሊፔ ማኒዬ በተሰኘ ስም ዜግነት ተሰጥቶት ኖሯል።

ፈረንሳይ ውስጥ ሳለ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ጥበቃ ሆኖ ሲያገልግል ከቆየ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2017 ወደ #ካሜሩን ያቀናል።

ሰውዬው ይህን ያደረገው አንድ ሰው እሱ ላይ ቅሬታ እንዳለው ድምፁን ካሰማ በኋላ ነው።

ፊሊፔ በቁጥጥር ሥር የዋለው በካሜሩኗ ዋና ከተማ ያውንዴ ውስጥ ሲሆን ከዚያም ወደ ፈረንሳይ እንዲሄድ ተደርግ የፍርድ ሂደቱን ሲከታተል ቆይቷል።

በመጨረሻም የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።

በሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳታፊ ሆነው የተገኙ ግለቦች ፈረንሳይ ውስጥ ፍርድ ሲሰጣቸው ፊሊፔ አምስተኛው ነው።

በሚቀጥለው ዓመት 30ኛ ዓመቱን የሚይዘው እና በ100 ቀናት ውስጥ 800 ሺህ ቱትሲዎች እና ለዘብተኛ ሁቱዎች የተገደሉበት የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂዎች አሁን ድረስ ጉዳያቸው አልተዘጋም።

ከወር በፊት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረ የቀድሞ የፖሊስ አባል (ፉልጌንሴ ካይሼማ) ከ22 ዓመታት ሽሽት በኃላ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙ ይታወሳል።

ግለሰቡ በተያዘበት ወቅት የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፤ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ ፤ ከሩብ ምዕተ አመታት በኃላም ቢሆን እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች ከፍትህና ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ እንደሆነ ተናግረው ነበር።

@tikvahethiopia
#አውሮፓ

የአውሮፓ ፓርላማ የህብረቱን #የስደተኞች እና #የጥገኝነት ደንቦችን የሚያጠናክር ትልቅ ማሻሻያ አጽድቋል።

የአውሮፓ ህብረት የጥገኝነትና ፍልሰት ስምምነት ከ2015 ጀምሮ ሲመከርበት የቆየ ሲሆን በ2 ዓመት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

አዲሱ ሕግ ምን ይዟል ?

➡️ የጥገኝነት ሂደት ጥያቄ #ያፋጥናል ፤ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ #ያስገድዳል

➡️ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት የጥገኝነት ጠያቂዎችን ኃላፊነት እንዲጋሩ ያደርጋል።

➡️ የአውሮፓ ህብረት 27 አባል አገራት በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከጣሊያን፣ ግሪክ እና ስፔን ካሉ " #የድንበር " አገራት እንዲወስዱ ወይም በምትኩ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያደርጋል።

➡️ ዝቅተኛ ተቀባይነት የማግኘት እድል ያላቸው የጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ አውሮፓ ህብረት ግዛት ሳያስገቡ ጉዳያቸው በፍጥነት መታየት አለበት ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄዎች ቢበዛ በ12 ሳምንታት ውስጥ እንዲያልቁ ይላል።

➡️ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገባቸው በ12 ሳምንታት ጊዜ ውስጥ #በግዳጅ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው  ይላል።

➡️ ስደተኞች ከመግባታቸው በፊት ባሉ በ7 ቀናት ውስጥ ጠንከር ያለ የማጣራት ሂደት ይደረግላቸዋል። የጤና እና የደህንነት ፍተሻዎችን ይጨምራል።

➡️ ከ6 ዓመት እና ከዛ በላይ ለሆኑ ማናቸውም ስደተኞች የባዮሜትሪክ መረጃ ይሰበሰባል። ስደተኞች ቁጥር በአጋጣሚ ካሻቀበም ምላሽ የሚሰጥበት አሠራር ተዘርግቷል።

ምንም እንኳን አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አገራት የተወሰኑ የስምምነቱን ክፍሎችን ቢቃወሙም በሚያዝያ ወር መጨረሻ በሚደረግ ድምጽ አሰጣጥ የአብዛኛውን ይሁኝታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው አመት 380 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የአውሮፓ ህብረትን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ አቋርጠዋል። ይህም እ.አ.አ ከ 2016 ወዲህ ከፍተኛው ቁጥር ነው።

ስለ ሕጉ ምን ተባለ ?

#ጀርመን፦ የጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስ “ ታሪካዊና አስፈላጊ እርምጃ ” ብለውታል።

#የአውሮፓ_ፓርላማ፦ የፓርላማው ፕሬዝዳንት ሮቤታ ሜሶላ “ በአብሮነት እና በኃላፊነት መካከል ያለውን ሚዛን ጠብቋል ሁሉንም ነገር በአንድ ጀምበር ባይፈታም ግን 10 ግዙፍ እርምጃ የተጓዘ ነው " ብለዋል።

#ሀንጋሪ ፦ ምንም አይነት የስደት ስምምነት ቢደረስ መደበኛ ያልሆኑ ስደተኞችን አልወስድም ብላለች።

#ፖላንድ ፦ የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ቱስክ የተወሰኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችን መውሰድ አልያም ለድንበር አገራት ገንዘብ መክፈል የሚለውን ሃሳብ " ተቀባይነት የሌለው " ሲሉ ውድቅ አድርገዋል።

#ስሎቫንያ፦ “ ልንሰራበት የምንችለው ስምምነት ነው ” ስትል ደግፋለች።

#ቤልጂየም፦ “ ፍፁም አይደለም (ሕጉን) ግን እንደግፈዋልን ” ስትል አሳውቃለች።

#ፈረንሳይ ፦ ፕ/ት ኢማኑኤል ማክሮን ድጋፍ ሰጥተዋል። የፈረንሣዩ ቀኝ አክራሪ ናሽናል ራሊ አባል ጆርዳን ባርዴላ ስምምነቱ “ #አስፈሪ ” ነው ሲሉ ተቃውመዋል።

#አምነስቲ_ኢንተርናሽናል ፦ ስምምነቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ “ከፍተኛ ስቃይ” የሚመራ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚነሳው አንዱ ተቃውሞ ዝቅተኛ ተቀባይነት የሚኖራቸው #ጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳያቸው በድንበር #መግቢያዎች ላይ ወይም #በማቆያ_ስፍራዎች እንዲስተናገዱ በማድረግ ፍትሃዊ ዕድል የማግኘት ተስፋቸውን ያመነምነዋል የሚል ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia