TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የእርቀ ሰላም ውይይት ተጀመረ!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ነጋዴ ባሕርና አካባቢው የሚኖሩ #የአማራና #የቅማንት ህዝቦች ተወካዮች የእርቀ ሰላም ውይይት ጀምረዋል፡፡ ውይይቱ ነጋዴ ባሕር ከተማ ላይ ነው እየተካሄደ ያለው፡፡ የእርቀ ሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ያደረጉት ከሁለቱም ወገኖች የኃማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ የውይይቱም ዓላማ አሁን ላይ ያለው #አለመግባባት እንዲያበቃና ወደቀደመው መከባበርና አንድነት ለመመለስ ነው፡፡ የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመት እንደማይጠቅምና ተጎጅዎችም ራሳቸው መሆናቸውን ተወያዮቹ ተናግረዋል፡፡

#ከግጭት ይልቅ የቀደመውን #አንድነት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹የጥፋቱ መንስኤ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ከሆነ ህግን ተከትሎ መንግስት ሊፈታው ይገባል፤ እኛ ሰላማዊ ነዋሪዎች ነን፤ ሰላማችንን ልንጠብቅ ይገባናል›› ነው ያሉት፡፡ በጥፋቱ የሚጠየቁ ግለሰቦች ካሉም በጋራ ሆነን ተጠርጣሪዎችን ለህግ እንዲቀርቡ እናደርጋለን ብለዋል ተወያዮቹ፡፡

‹‹መንግስት የሚደርሰው ጥፋት ከተከሰተ በኋላ ነው፤ ስለዚህ ለጥፋቱ የድርሻውን ይውሰድ፤ እኛም ችግሩን ወደ ሌላ ሳንገፋ የድርሻችንን ልንወስድ ይገባል›› ብለዋል፡፡ ለዘራፊዎች በራቸውን መክፈት ሳይሆን ሰላማቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል #አማረ_ገብሩ በውይይቱ ላይ ተገኝተው የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ህይዎትን_ለማትረፍ ቅድሚያ እንደሚሰጥ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ‹‹ሕዝብ ከሌለ ሀገር የለም፤የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚችል መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው አለ፤ ከሕዝብ የምንጠብቀው ወንጀለኞችን አሳልፎ መስጠትና ለችግሮች መፍትሔ መስጠት ነው›› ብለዋል፡፡ ሰራዊቱን ሕዝቡ እንዲደግፈውም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

#በእርቀ_ሰላም ውይይቱ እንዲሳተፉ ከአካባቢው 16 ቀበሌዎች ጥሪ ቀርቦላቸው እንደነበር ተገልጧል፡፡ አብዛኛዎቹ ተሳትፈዋል፤በተለያዩ ምክንያቶች ከሁለቱም ወገኖች ለውይይት ያልተገኙ የቀበሌ ተወካዮችም አሉ፡፡ ሁሉን አቀፍ የጋራ መግባባት እንዲኖር ለማድረግም ለየካቲት 15/2011 ዓ.ም ሕዝባዊ ውይይት ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዞ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

"ፀግሽ ባሁኑ ሰአት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ምክንያቱ #ባልተረጋገጠ ጉዳይ ፀጥታው አስጊ ሁኔታላይ ይገኛል። የሚመለከተውም አካል ጉዳዩን አጥንቶ መፍትሔ እንዲያበጅልን።"

ውድ ተማሪዎች እባካችሁ #ከግጭት እና #አለመግባባት ርቃችሁ ለሀገራችሁ ሰላም እና እድገት እንድትሰሩ በTIKVAH-ETH ስም እንጠይቃለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ከሰሞኑን የባህር በር ጉዳይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ጉዳዩ ክብደት እንዲያገኝ ያደረገው ደግሞ በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደረጃ መነሳቱ ነው።

አንዳንዶች ጉዳዩ መነሳቱን እና መነጋገሩን ሲያደንቁ ሌሎች ደግሞ " ጊዜውን የጠበቀ አይደለም ፤ አጀንዳ ለመስጠት ነው ፤ በቅድሚያ የሀገር ሰላምና የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ይቀድማል " በሚል ተቃውመዋል።

ለመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንድነው ያሉት ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የህዝብ እንደራሴዎችን ሰብሰበው የሰጡት ማብራሪያ በቴሌቪዥን ጣቢያዎች ተሰራጭቶ ነበር።

በዚህም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል።

- ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ፍላጎትን በግልፅ አስቀምጠዋል።

-  የሕዝብ ቁጥሯ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሄደው እና ከቀይ ባሕር እና ከሕንድ ውቅያኖስ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ሃሳብ የሕልውና ጉዳይ ነው መሆኑን አመልክተዋል።

- ቀይ ባሕር እና አባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ ለኢትዮጵያ ዕድገት እና ጥፋት መሠረት እንደሆኑ በመግለፅ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ መሸሽ እንደማይስፈልግ ገልጸዋል።

- ለባህር በር መተላለፊያ መገኘት ኤርትራ፣ ጂቡቲ እና ሶማሊላንድ አማራጮች ሊሆኑ እንደሚችሉ በማንሳት ይህ የኢትዮጵያ ፍላጎት ሊሳካባቸው የሚችልባቸውን #ከግጭት_ውጪ ያሉ አማራጮችን አስረድተዋል።

ይህም ፦

የታላቁ ሕዳሴ ግድብን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኢትዮ ቴሎኮም ጨምሮ በትልልቅ የአገሪቱ ተቋማት ውስጥ ድርሻ መስጠት እና የመሬት ልውውጥ ማድረግ እንደሚቻል ነው።

- በአጠቃላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ የባህር በር ጉዳይ ከመነጋገር ከመመካከር መሸሽ እንደማያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የሰሞኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ነጥሎ ስለ አንድ ሀገር ትኩረት ያላደረገ ቢሆንም ከኢትዮጵያውን አልፎ #ኤርትራውያንም ስለጉዳዩ አስተያየት ሲሰጡበት ተስተውሏል።

አንዳንዶች ስርዓት ባለው መልኩ ቢሰራበት እና እስካሁን ያልተፈቱ ችግሮች ተፈተው መግባባት ላይ ተደርሶ ቢሰራበት መላው ኤርትራውያንን እና ኢትዮጵያውያንን የሚጠቅም ጉዳይ እንደሆነ ሲያነሱ ሌሎች ደግሞ በፍፁም ይህ ጉዳይ ለውይይትም ሆነ ለንግግር ሊቀርብ አይገባም ባይ ናቸው።

ዛሬ ደግሞ የኤርትራ መንግስት ሰሞነኛው አጀንዳ ስለሆነው የውሃና የባህር በር ጉዳይ " ሰም ያልጠቀሰ " አጭር መግለጫ አሰራጭቷል።

የኤርትራ መንግስት ማስታወቂያ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአስመራ ያወጣው ስም ያልጠቀሰው አጭር መገለጫ " በቅርቡ ጊዚያት ስለ ውሃ እና የባህር በር የመሳሰሉ ርእሰ ጉዳዮች የተባለና ' ተብለዋል ' የተባለው መጨበጫ የለውም። ይህም ያላስገረመው ታዛቢም የለም "  ይላል። 

ስም ያልጠቀሰው ይህ አጭር መግለጫ የኤርትራ መንግስት እንደ ሁልግዜው ይህንን ወደ መሰሉ የባህር በር እና ተያያዥ ጉዳይ መድረኮች የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል።

" ይህን መሰል ነገር እንደማንታደም ደጋግመን እናረጋግጣለን " ያለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ " ሁሉም አስተዋዮች እና ተቆርቋሪዎች በዚህ እዳይቆጡ " ሲል አክለዋል።

መግለጫው በግልፅ ስለ የትኛው አካልና በየትኛው አካል ስለተነሳ ጉዳይ እንዲሁም ስለየትኛው መድረክ እንደሚያወራ ግልፅ ያለው አንዳች ነገር የለም።

@tikvahethiopia