TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ ለማ መገርሳ⬇️

በቡራዩና አከባቢዋ በተፈጠረው #ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል
ገለፀ።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በቡራዩና አከባቢዋ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ለማ በመግለጫቸው በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ነው ያስታወቁት።

ክልሉ የተፈናቀሉ ወገኖችን ቀደ ቀያቸው ለመመለስና መልሶ ለመቋቋም #ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ይሰራልም ብለዋል።

እስከ አሁንም 300 አባወራዎችን ወደ ቀያቸው መመለሱንም ገልፀዋል።

በግጭቱ እጃቸው አለበት የተባሉ 200 ተጠርጣሪዎችና የተለያዩ የጦር #መሳርያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

ግጭቱን ወደተለያዩ አከባቢዎች በተለይ ወደ #አሰላ አከባቢ ለማስፋፈት ቢሞከርም ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ባደረገው ትብብር መክሸፉን ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ አሁንም በተረጋጋ ስሜት በማስተዋል ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በተለያዩ አከባቢዎች እየተንቀሳቀሱ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችና #አክቲቪስቶችም የሚያስተላልፉት #መልዕክት ህዝቦችን የሚያቀራርብ ወደ አንድነት እንዲመጣ የሚያደረግ እንጂ የሚያለያይ ሊሆን እንደማይገባም አቶ ለማ ተናግረዋል።

ከዚህ በኋላ መንግስት ነገሮችን በትዕግስት የሚያልፍበት ሁኔታ እንደማይኖርም አስታውቀዋል።

ከፌደራልና ከኦሮሚያ ፖሊስ የተውጣጣ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ያሉትን ሁኔታዎች ለማርገብና እንዲሁም ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ገልፀዋል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia