TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ በረከትና አቶ ታደሰ ፍርድ ቤት ቀረቡ‼️

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩና ጉዳዩ አዲስ አበባ እንዲታይላቸውም ጠይቀዋል፡፡ በምክንያትነት ደግሞ የጤና ችግርና የቤተሰብን ድጋፍ በቅርበት ለማግኘት በሚል አቅርበዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ‹‹ተመዘበረ›› ካለው የሀብት መጠን ከፍተኛነት አንጻር ዋስትና እንዳይሰጣቸውና እንዲሁም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ ጉዳያቸው በባሕር ዳር እንዲታይ ለፍርድ ቤቱ ጠይቋል፡፡ ምሥክሮችን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ስለሚያቀርብም የጉዳዩን በባሕር ዳር መታዬት ተገቢነት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የዋስትና መብታቸውን ከልክሎ በጥብቅ ጥበቃ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ወስኗል፡፡ የተጠረጠሩበት ወንጀል ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ዋስትና የከለከለው ፍርድ ቤቱ #የተመዘበረው ሀብት በአማራ ክልል ስለሆነ ጉዳዩ መታዬት ያለበት በባሕር ዳር እንደሆነም ፍርድ ቤቱ ወስኗል፡፡

በጥብቅ ጥበቃ እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ የወሰነው ከነበራቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አንጻር መሆኑንም ችሎቱ አስታውቋል፡፡ #የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ አጠናክሮ እንዲያቀርብ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የዛሬ ውሎውን ችሎቱ አጠናቅቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 17/2011 ዓ.ም.

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
.
.
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የዱባይ ማራቶን ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
.
.

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
.
.
#የአገር_መከላከያ_ሰራዊት አባላት እና የሶማሌ ክልል #ልዩ_ሀይል አባላት ዛሬ #በጅግጅጋ_ከተማ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
.
.
በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት እሳት ተነስቶ 1 ሺ ሄክታር የሚሆን የፓርኩ ክፍል ወድሟል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሎ ውሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
.
.
የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ ገምግሟል።
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
.
.
በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ገብተዋል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
.
.
በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል።
.
.
የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
.
.
በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገልፀዋል።
.
.
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰዋል

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ elu፣ ቢቢሲ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

.
.
አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችን ቸር ትደር!!
ጥር 17/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ አረፉ‼️

ኮ/ል #ታደሰ_ሙሉነህ በኢትዮጵያ አየር ኃይል የ71 ቅጥር አባል ናቸው። በቀደመው አየር ኃይል በሚግ-23 ተዋጊ ስኳድሮን ውስጥ በምሥራቅም ሆነ በሰሜን ግንባር ተሰልፈው ከፍተኛ ተጋድሎ ካደረጉት የአገራችን ኢትዮጵያ ባለውለታ አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ።

በ1991 ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ በመቃወም ወደ ኤርትራ አቅንተዋል።

የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን በመምራት በኤርትራና በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ምዕራብ በረሃዎች ሳሉ በኤርትራ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር በመዋላቸዉ ለበርካታ አመታት ደብዛቸው፤ አድራሻቸው ጠፍቶ ነበር።

ከወራት በፊት ኮ/ል ታደሰ ከኤርትራ እስር ነፃ ይሁን እንጂ ጤንነታቸው ታውኮ ሰውነታቸው እንደልቡ በማያዝቡት ሁኔታ በመሆኑ በህክምና #በህንድ ሐገር ሲታከሙ ቆይተው ጥር 27 ቀን 2011 ዓም አርፈዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጸመ‼️

የኮሎኔል #ታደሰ_ሙሉነህ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ፡፡ ኮሎኔል ታደሰ ከወይዘሮ አዛለች ጥሩነህ እና ከአቶ ሙሉነህ ሃምሌ 16/1944 ዓ.ም በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ እንደተወለዱ ከትግል አጋሮቻቸው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትም በ67 ዓመታቸው ነው፡፡ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ የአራት ሴቶችና የሁለት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በማህደረ ስብሀት መርዓዊ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ተፈጽሟል፡፡

በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ላቀ አያሌው፣ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እና የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባላት ተገኝተዋል፡፡ የአበባ ጉንጉንም አስቀምጠዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምቦ ዩኒቨርሲቲ!

#የአምቦ_ዩኒቨርሲቲ በሎሬት #ፀጋዬ_ገብረመድህን ስም የባህል ማዕከል እንደሚያቋቁም አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር #ታደሰ_ቀነዓ ለኢዜአ እንደገለጹት ማዕከሉ የሚቋቋመው የሎሬቱን ጨምሮ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግና ተሰጥኦ ያላቸውን ጠቢባን ለማፍራት ነው።

“ማእከሉን ለሟቋቋም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማዕከሉን ለማቋቋም ከአዲስ አበባ፣ ከባህር ዳርና ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ልምድ ቀስሟል ብለዋል።

ከሎሬት ጸጋዬ ወጥ ሥራዎች መካከል የአቴቴ ሥርዓት፣ የገዳ ሥርዓት፣ ዝክረ መርካቶ፣የኩሽ ሕዝቦች ሥልጣኔ፣ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ ኦዳና አቡነ ጴጥሮስን የሚዘክሩት ተጠቃሽ ናቸው።

ከትርጉም ሥራዎቻቸው መካከል የዊሊያም ሼክስፒር ድርሰቶች ሃምሌትና ኦቴሎ  ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች  ይገኙበታል።

#የአምቦ_አካባቢ_ተወላጅ የሆኑት ሎሬት ፀጋዬ በ60 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም የተለዩት በ1998 ነበር።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮ/ሌ በዛብህ ጉዳይ...‼️

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

"ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስን ሰኔ ላይ ኤርትራ ውስጥ በአካል አግኝቻቸዋለሁ። በመጪው ሰኔ ላይ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ" -- ኢንጅነር #ታደሰ

"እኔ ምንም መረጃ የለኝም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ #ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው"-- ፕ/ር #በየነ_ጴጥሮስ
.
.
ኢንጅነር ታደሰ ይባላሉ። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ወደ ኤርትራ ተጉዘው እንደነበር እና በቆይታቸው ወቅትም በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበሩት ጀት ተመትቶ የተማረኩትን ኢትዮጵያዊውን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን እንዳገኟቸው ለጋዜጠኛ #አልያስ_መሰረት ተናግረዋል፤ አክለውም "በአሁን ሰአት እንደ ሌሎች የጦር ምርኮኞች በቀይ መስቀል ስር ይገኛሉ። እኔም እዛ አግኝቻቸዋለሁ። ትንሽ ከእድሜ መግፋት ውጪ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ሰኔ ወር ሲመጣ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ። ዝርዝሩን የመንግስት ሰዎች ያውቃሉ" ብለዋል።

የኮ/ሌ በዛብህ ጴጥሮስ ታላቅ ወንድም ወደሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ስለጉዳዩ በሰጡት ምላሽ፦ "እኛ ይህ መረጃ የለንም። እኚህ ያልካቸው ግለሰብ እንዴት access ሊኖራቸው እንደቻለ አላውቅም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው። ወንድሜ በህይወት አለ ወይስ የለም የሚለውን ለማረጋገጥ እንኳን ካደረግነው ጥረት አንፃር ሲታይ የዚህ ሰውዬ መረጃ በጣም extreme ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ሲጠቃለል በኮሎኔል በዛብህ ዙርያ መነጋገር አንፈልግም የሚል ነው። ከዚያም አልፎ ጉዳዩን sensitive አርጎ መናደድ አለ። እኛን አትጠይቁን አይነት ነገር ነው ያየነው። በህይወት ተይዞ የአስመራ መንገዶች ላይ parade የተደረገ ሰው ነው። የኛ አቋም ህይወቱ አልፏል ከተባለ ታውቃላችሁ እና አካሉ የት ነው እያልን ነው። ግን ይህንን ጉዳይ መወያየት አይፈልጉም። ከኢትዮጵያ መንግስት ወገን ደሞ አሁን የተጀመረውን ንግግር ያበላሽብናል የሚል ነገር አለ። ለማንኛውም ያልካቸውን ሰውዬ አገናኘኝ። ይህ ለኛ ትልቅ development ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፍርድ ቤቱ በአቶ #በረከት_ስምዖንና በአቶ #ታደሰ_ካሳ ተጨማሪ ቀጠሮ ላይ ለመወሰን ለሰኞ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በጥረት ኮርፖሬት የመሪነት ዘመናቸው በሀብት ብክነትና ምዝበራ የተጠረጠሩት አቶ በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ ዛሬ በቀጠሯቸው መሠረት በባሕር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ስላልመጡና መረጃዎች በበቂ #ስላልተጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን ቀጠሮ ጠይቋል፡፡ በዚህ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለሰኞ የካቲት 18 ቀን 2011ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእስር ላይ የሚገኙት እነ አቶ በረከት ስምዖን #ኮምፒውተር#ስልክ እና #የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት #ውድቅ አድርጎባቸዋል። ተጠርጣሪዎቹ አቶ በረከት ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ ከዚህ በፊት ምስክሮችንና የሕግ ባለሞያዎችን ምክር ለማገኘት እንዲረዳቸው የኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎቶች በባህር ዳር ማረሚያ ቤት እንዲሟላላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ሆኖም ለአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ኮምፒዩተሮችና የስልክ አገልግሎት በማረሚያ ቤቱ ስለሚገኙ ተጠርጣሪዎቹም በዛው እንዲገለገሉ በማለት የባሕር ዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥያቄውን ዛሬ ወድቅ ማድረጉን የጀርመን ራድዮ ዘግቧል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቦቹ እንደሌሎች ጠጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤቱ የሚያቀርበውን ማንኛውንም ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው አርብ እለት የአማራ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ #ተጠርጣሪዎቹ ለመጋቢት 2 ቀን 2011 ዓ.ም እንዲቀርቡ አዟል።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የእሳት አደጋ አጋጥሞታል፤ ቃጠሎውም #እየተባባሰ እንደሆነ ነው የተሰማው። ከደባርቅ ከተማ ወጣቶች ተሰብስበው ወደ ፓርኩ ሄደው #ለማጥፋት ቢፈልጉም ተሽከርካሪ ማግኘት አለመቻላቸውን ለአብመድ ተናግረዋል።

እሳቱ #ሳንቃ_በር አካባቢም መከሰቱን ወጣቶቹ ተናግረዋል የደባርቅ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት የወጣቶችን #ጥቆማ ተጋርቷል።

ከፓርከ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መካከል አቶ #ታደሰ_ይግዛው እሳቱ እሜት ጎጎ እና ሳንቃበር አካባቢ #መባባሱን ገልጸው ወደ ቦታው ለማቅናት ተሽከርካሪ እያፈላለጉ መሆኑን ገልጸዋል። ጊዜው #በመምሸቱ ስልክ የሚያነሳላቸው ሰው ማጣታቸውንም ተናግረዋል። ከዞንና ክልል የሥራ ኃላፊዎች መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ሲል አብመድ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #በረከት_ስምዖን እና አቶ #ታደሰ_ካሳ የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ለሚያዝያ 14 ቀን ተቀጠሩ፡፡ በጥረት ኮርፖሬት የሀብት ምዝበራ ተጠርጥረው በፍርድ ቤት ጉዳያቸው እየታዬ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ #የተከሰሱበት ዝርዝር ጉዳይ ትናንት በጽሑፍ ደርሷቸዋል፡፡ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎቹ ጽሑፉ ብዛት ስላለው በአግባቡ አንብበውና ተረድተው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም የተከሳሾቹን አቤቱታ ተመልክቶ ለሚያዝያ 14 ቀን 2011ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia