TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ14ኛ ዙር የ20/80 እና ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ። በዚህም መሰረት፦ 1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃፍቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነታቸው የተነሱ በቁጥጥር ስር የዋሉ፡- 1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ 2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን፦…
" ያለመከሰስ መብታቸው ይነሳ "
የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ጥያቄ ቀረበ።
ጥያቄው መቅረቡ የተገለፀው በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ነው።
የፍትህ ሚኒስቴር #ከጋራ_መኖሪያ_ቤቶች እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር ፤ የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት ይነሳልን ጥያቄው ከጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን ስልጣንና ሃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ የቀረበ መሆኑንም አስረድተዋል።
(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)
@tikvahethiopia