TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

ሰባ ገደማ #ኢትዮጵያውያን በቀይ ባህር #የጀልባ_መገልበጥ አደጋ #ሞቱ:: ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ እና የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ 70 ገደማ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመገልበጥ አደጋ ደርሶባቸው ሞቱ። ከሟቾቹ ውስጥ ስድሳዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተነሱ ነበሩ ተብሏል።

ሰባ ገደማ ወጣቶች ይዛ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ የመገልበጥ አደጋ የደረሰባት ቅዳሜ መጋቢት 28 ለሊት መሆኑን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል።

ከጀልባዋ ተሳፋሪዎች መካከል 60ዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተጓዙ መሆናቸው ከተሰማ በኋላ በወረዳዋ በከባድ የሐዘን እና ድንጋጤ ድባብ እንደምትገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

በተገለበጠችው ጀልባ ላይ የነበሩት ቀሪዎቹ ወጣቶች ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ቢነገርም ትክክለኛ ቁጥራቸውን እና ከየት አካባቢ እንደመጡ በተመለከተ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ አብዛኞቹ የሟች ወጣቶች ቤተሰቦች የሞት መርዶውን በአደጋው ማግስት እሁድ እና ትናንት እንደተረዱ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ከ40 በላይ የሟች ቤተሰቦች መርዶው እንደደረሳቸው ገልጿል። የትግራይ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ትናንት ምሽት ባወጣው የሐዘን መግለጫ የአርባዎቹን ወጣቶች መሞት አረጋግጧል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ናይጄሪያ

ናይጄሪያ ውስጥ አንድ ባለሃብት ገንዘብ ለማደል በጠራበት ዝግጅት ላይ በተፈጠረ ግርግር አንዲት የ8 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 7 ሰዎች ተረጋግጠው እንደ #ሞቱ ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ትላንትና እሁድ አልሃጂ ያኩቡ የተባለ ባለሀብት በሰሜን ምሥራቅ የባውቺ ግዛት ነዋሪዎች ወደ ቢሮው ከመጡ ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ናይራ (የናይጄሪያ ገንዘብ) ለመስጠት ቃል ይገባል።

5 ሺህ ናይራ ወደ ዶላር ሲመነዘር 3 ዶላር ከ70 ሳንቲም ሲሆን፣ ወደ ብር ሲቀየር 210 ነው።

የባለሀብቱን የገንዘብ እደላ ጥሪ ተከተሎ በርካታ ሰዎች ይወጣሉ በዚህ ወቅት በተፈጠረ ግርግር ዕድሜያቸው ከ8 እስከ 55 የሚሆን 7 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አረጋግጧል።

ነዋሪዎች ግን የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተጠቀሰው ይበልጣል ብለዋል።

ብዙ ጊዜ እንዲህ ያለ እደላ/እርዳታ ላይ ወንዶች የእርዳታ ገንዘብ ሲቀበሉ መታየት  ስለማይፈልጉ ሴቶችን እንደሚልኩ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በዕለቱ የተፈጠረውን ነገር ለማጣራት ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ቢሮው አካባቢ የጥሬ ገንዘብ ልገሳ ያሰናዳው ባለሀብቱ አልሃጂ ያኩቡ ማይሻኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የናይጄሪያ የምጣኔ ሀብት #መላሸቁን ተከትሎ በርካቶች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። 5 ሺህ ናይራ አንድን ቤተሰብ ለአንድ ቀን መመገብ ይችላል።

ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ናይጄሪያ የናሳራዋ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ሩዝ ሲታደል ለመቀበል የወጡ የተወሰኑ #ተማሪዎች ተረጋግጠው #ሞተዋል

ባለፈው ወር የናይጄሪያ ገቢዎች አገልግሎት ሩዝ በቅናሽ ዋጋ ሲሸጥ በተፈጠረ ግርግር የተወሰኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቆ ነበር።

ናይጄሪያ ውስጥ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት በርካቶች የሚቀበሉት ደመወዝ ከወር ወር ሊያደርሳቸው እንዳልቻለ ቢቢሲ አስነብቧል።

Via https://t.iss.one/thiqahEth

@tikvahethiopia