TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የ20/80 እና 40/60 ጉዳይ ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ መግለጫውን ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ ከኢንሳ የአጣሪ ቡድን መሪ በጋራ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና…
#Update

ከ14ኛ ዙር የ20/80 እና ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ።

በዚህም መሰረት፦

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃፍቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነታቸው የተነሱ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን፦ ዳይሬክተር

3ኛ. ሀብታሙ ከበደ፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

4ኛ. ዬሴፍ ሙላት፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

5ኛ. ጌታቸው በሪሁን፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

6ኛ. ቃሲም ከድር፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

7ኛ. ስጦታው ግዛቸው፦ ሶፍትዌሩን ያለማ

8.ኛ. ባየልኝ ረታ፦ ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ

9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፦ የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

10ኛ .ኩምሳ ቶላ፦ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)

@tikvahethiopia
ሶስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ገለፀ።

የቡርጂ ልዩ ወረዳ በተለያዩ ጊዜያት በገላና ሸጥ እና ከምዕራብ ጉጂ ጋር በሚያዋስኑን አከባቢዎች የአከባቢውን ሠላም የማይፈልጉ ሀይሎች የንፁሐንን ሕይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ ብሏል።

" ምንም እንኳን የፀጥታ ሥጋት ብኖርም መተዳደሪያቸው የሆነውን የእርሻ ሥራ በማካሄድና ጤፍ በማጨድ ላይ የነበሩ ንፁሐን አርሶ አደሮች በገዛ መሬታቸው እና አከባቢያቸው ሲገደሉ ቁጥራቸው በርከት እያለ ያለ ነው " ብሏል።

ትላንትና በተመሳሳይ መልኩ #በዋሌያ ቀበሌ የዕለት ተግባራቸውን ለመከወን የወጡ ሶስት አርሶ አደረሮች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥፏል ሲል አሳውቋል።

ልዩ ወረዳው የቡርጂ ማሕበረሰብ እና የሟች ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ሀዘኑን ገልጾ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ አንዳሳዘነውና ቁጭት እንደፈጠረበት ገልጿል።

" ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እነዚህ ፀረ ሰላም ኃይሎች የእጃቸውን እንዲያገኙ በጥብቅ እየሠራን ነው " ያለው የቡርጂ ልዩ ወረዳ " " የክልል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን እንዳለ ለማረጋገጥ እንወዳለን " ሲል አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU ዛሬ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም ደነቀ በተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው ላይም ይህን ብለዋል (ከኢፕድ የተወሰደ) ፦ - ተማሪ ቢኒያም ኢሳያስ 4ኛ አመት ተማሪ እያለ ነው የአካል ጉዳት እንዳለበት የታወቀው ፤ ዩኒቨርሲቲው ላለፉት 8 ወራት ጉዳዩን ይዞ ሲመረምር ቆይቷል። - ባዋቀረው ኮሚቴ በቀረበለት…
#Update

ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ እንዲሁም አባቱ አቶ ኢሳያስ ገ/ወልድ እንዲሁም የቤተሰቡ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅን ውሳኔ እንደማይቀበለቱ ገለፁ።

ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን እንዲቀለብስ እና ተማሪ ቢንያምን ከ4 ዓመት በላይ ወደለፋበት የትምህርት ገበታው እንዲመልሰው ጠይቀዋል።

ይህንን የጠየቁት " ሸገር ኢንፎ " በሚሰኝ የዩትዩብ ገፅ ላይ በቀረቡበት ወቅት ነው።

የተማሪ ወላጅ አባት አቶ ኢሳያስ " ውሳኔው ተቀባይነት አለው ብዬ አላስብም ፤ በውሳኔውም አዝኛለሁ አልቀበለውም፤ ውሳኔውን ተመልሰው እንዲያጤኑት " ሲሉ ጠይቀዋል።

" በሌላ ዓለም እንክብካቤ እየተደረገ እውቀት ያለው ጭንቅላት ያለውን ኡፍኡፍ እያሉ ነው የሚይዙት እዚህ ሳየው ተቃራኒ ሆኖብኛል " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ኢሳያስ ልጃቸው ወደፊት ትልቅ ደረጃ ደርሶ የህዝቡ አገልጋይ ሆኖ እንደሚመጣ ምንም ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል።

ተማሪ ቢንያም በበኩሉ ፤ ውሳኔው ከዚህ በፊት ከነበረው ያልተለየ መሆኑን ገልጾ " በእነሱ ምክንያት ሀገሪቱ እየከሰረች ነው " ሲል ገልጿል።

" እኔ ፕሮሰሱን ጠብቄ ነው የገባሁት እኔ ባላጠፋሁት ምን አይነት ኃላፊነት እንደወሰዱ አልገባኝም ፤ እኔን ማብቃት ነው የሚገባቸው እንጂ ቴክኒካል ጉዳዮችን ጠቅሰው መናገራቸው ሲሉት የነበሩትን ነው የደገሙት ለእኔ የተለየ ውሳኔ አይደለም፤ የተለየ ውሳኔም አልጠበኩም " ብሏል።

ተማሪ ቢንያም ዩኒቨርሲቲው የለፋበትን ትምህርት ሊያስጨርሰው እንደሚገባ ገልጾ በሌላ ዓለም ላይ ያሉ ተሞክሮዎችን መውሰድ ይቻላል ብሏል።

ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ፤ ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን ድጋሚ እንዲያጤነው ካልሆነ ወደ ክስ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Binyam-Esayas-07-14

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ስር ዋሉ።  ኮሚሽነሩ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው ዛሬ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት። በፌደራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት፥ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኤልሻዳይ…
የአቶ ምትኩ ካሳ ጉዳይ !

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ትላንት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉ ይታወቃል።

አቶ ምትኩ ከኤልሻዳይ የበጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ነው የታሰሩት።

ፖሊስ የእሳቸውን ጉዳይ መከታተል ከጀመረ የቆየ ሲሆን (ከሁለት ዓመት በፊት) እስከዛሬ እንዴት ሳይታሰሩ ሊቆዩ ቻሉ ? የሚለውን በተመለከተ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያበሰጡት ቃል ተከታዩን ብለዋል ፦

" ፖሊስ በ2012 ዓ/ም አካባቢ ነው ጉዳዩን ያጣራው ፤ እስከዛ ግን የመንግስት ውሳኔ ስለሚያስፈልገው ፖሊስ አጣርቶ ጨርሶ እሳቸው ሳይያዙ የቆዩት በዚህ ምክንያት ተጓቶ ነው አሁን ላይ የደረሰው አሁን ውሳኔ ስለተሠጠ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል "

ዛሬ አቶ ምትኩ ካሳ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤት የቀረቡት ከልጃቸው ጋር ነው ፦ https://telegra.ph/Trial-07-14-2

በሌላ በኩል፤ ከአቶ ምትኩ ጋር ተመሳጥረው ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ የእርዳት እህል እና አልባሳት በመረከብ ለሽያጭ አውለዋል የተባሉ የኤልሻዳይ ኃላፊዎች በፖሊስ እየተፈለጉ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
ጋምቤላ - ሰዓት እላፊ !

በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የሰዓት እላፊ ተጥሎ እንደነበር ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ለማህበረሰቡ ደህንነት ታስቦ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ክፍተት መታየቱን ተገልጿል።

በዙህም በከተማው የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን በመለየት ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 ድረስ የተጣለው ገደብ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

ከአንቡላንስና ከፀጥታ ሀይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት መሆኑ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በአሁኑ ወቅት በጋምቤላ ከተማ ሰላማዊ ሁኔታ መኖሩ የተገለፀ ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ በየአካባቢው ተደራጅቶ መረጃ በመስጠት እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
ጋዜጠኛ አልዓዛር ተረፈ ታሰረ።

የ " አል አይን ኒውስ " የኢትዮጵያ ዘጋቢ መታሰሩን ለማወቅ ችለናል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መገናኛ ብዙሃን ለሆነው " አል አይን ኒውስ " በዘጋቢነት የሚሰራው ጋዜጠኛ አልዓዛር ተረፈ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 7 ከሰዓት ሲቪል በለበሱ ጸጥታ ኃይሎች መያዙን ባለቤቱ እና ባልደረባው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት ገልፀዋል።

ጋዜጠኛው በጸጥታ አካላት ከተያዘ በኋላ በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን አመልክተዋል።

አልዓዛርን በታሰረበት ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ የጎበኘው ባልደረባው ዳዊት በጋሻው፤ ጋዜጠኛው የተያዘው ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ ከሚገኝ ካፌ እንደሆነ ገልጿል።

የሲቪል ልብስ የለበሱ ሁለት ግለሰቦች ጋዜጠኛውን መታወቂያ እንዲያሳያቸው እንደጠየቁት እና " እንፈልግሃለን " ብለው እንደወሰዱት የዓይን እማኞች ነግረውኛል ብሏል።

ሁለቱ ግለሰቦች አልዓዛርን በያዙበት ወቅት " ለችግኝ ተከላ ጥሩ አመለካከት የለህም፤ ‘ቤተ መንግስት ገብተን፤ በደም የበቀለውን ችግኝ እንነቅላለን’ ብለሃል " በሚል ሲወነጅሉት መሰማታቸውን ጋዜጠኛ ዳዊት ተናግሯል።

" አል ዓይን ኒውስ " የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መገናኛ ብዙሃን ሲሆን በአማርኛ አገልግሎት ክፍሉ በኩል በተለይ የውጭ ሀገር መረጃዎችን እንዲሁም የሀገር ውስጥ መረጃዎችን በማቅረብ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በህይወት ያለን ሰው ያቃጠሉት ግለሰቦች ምን ተደረጉ ? • ካቃጠሉት ውስጥ እስካሁን አራት የሚደርሱ አልተያዙም። • ወንጀሉን ከፈፀሙት ውስጥ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከድተው ጠፍተዋል፤ 2 የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ለህግ እንዲሰጡ ለክልሉ ፖሊስ አመራሮች ተጠይቋል። • 3 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው (ሁለት የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት አንድ ሲቪል)…
የፍትህ ሚኒስቴር የምርመራ ሪፖርት ምን ይላል ?

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ጋር በመተባበር በሚያዚያ ወር ላይ በጎንደር ፣ በወራቤና በጂንካ አካባቢ በተከሰተ ግጭት ተፈፅመዋል ያላቸውን ወንጀሎች የምርመራ ግኝት ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ በሚያዚያ 2014 በጎንደር እና በወራቤ ሀይማኖትን መሰረት አድርጎ እንዲሁም በጂንካና አካባቢው ማንነትን መሰረት አድርጎ ተከስቷል ባለድ ግጭት የተፈጸሙ ወንጀሎችን የምርመራ ግኝት በዚህ ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Ministry-of-Justice-07-15

@tikvahethiopia
#Ethiopia 🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትካፈልበት ተጠባቂው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ለሊት ይጀምራል።

ዛሬ ለሊት አትሌቶቻችን ውድድራቸውን ያካሂዳሉ።

በዚህም መሰረት :-

- ሌሊት 9:15 :- የወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ

🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ጌትነት ዋሌ
🇪🇹 ኃይለማሪያም አማረ

- ሌሊት 10:10 :- የሴቶች 1,500 ሜትር ማጣርያ

🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ፍሬወይኒ ኃይሉ
🇪🇹 ሒሩት መሸሻ

የ " ኦሪጎን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር " በDSTV ልዩ ቻናል እና ብሄራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ መዝናኛ ቻናሎች በቀጥታ መከታተል ይችላሉ ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ #ስፖርት https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
#Kenya

የጎረቤት ኬንያ መንግስት ምንም እንኳን በዓለም አቀፉ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ቢጨምርም በሀገሪቱ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል አዲስ የነዳጅ ድጎማ አድርጓል።

ይህ ውሳኔ ኬንያውያን በሌሎች መሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ካጋጠማቸው የዋጋ ጭማሪ በተጨማሪ ከሌላ የዋጋ ንረት ጋር ትግል ውስጥ እንዳይገቡ ነው ተብሏል።

መንግሥት ከወረሃዊ የዋጋ ማሻሻያ በፊት በነዳጅ ላይ ያደርግ የነበረው ድጎማ ሊያነሳ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቶ ነበር።

ይሁን እንጂ የአገሪቱ መንግሥት የውሳኔ ለውጥ በማድረግ አሁን ያለውን የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ለተጨማሪ 30 ቀናት ባለበት እንዲቀጥል የ141 ሚሊዮን ዶላር ድጎማ አድርጓል።

በሰኔ ወር ባለስጣናት አሁን እየተደረገ ያለው የነዳጅ ድጎማ ''ዘላቂነት የሌለው ነው" ብለው ነበር።

ባለፈው ዓመት ኬንያ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መከሰቱን ተከትሎ ለነዳጅ ድጎማ ከ860 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ አድርጋለች።

ኬንያ በቀጠናው ካሉ አገራት ነዳጅ በውድ የምታቀርብ አገር ነች። ድጎማው ባይኖር ኖሮ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አንድ ሊትር ቤንዚን 1.80 ዶላር (93 ብር ከ90 ሳንቲም) ይደርስ ነበር። አሁን ላይ ዋጋው 1.34 ዶላር (69 ብር 90 ሳንቲም) ነው።

ከኬንያ ቀጥሎ በአካባቢው በከፍተኛ ዋጋ ነዳጅ የሚገዛባቸው አገራት ሱዳንና ኡጋንዳ ናቸው።

ነዳጅ የምታመርተው ሱዳን ለ1 ሊትር 1.50 ዶላር (78 ብር ከ25 ሳንቲም) ስታስከፍል፣ በቅርቡ የነዳጅ ዘይት ያገኘችው ኡጋንዳ 1 ሊትር በ1.6 ዶላር (83 ብር 47 ሳንቲም) ታቀርባለች።

በአፍሪካ ነዳጅ በከፍተኛ ዋጋ ከሚሸጡባቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ናት ፤ 1 ሊትር ነዳጅ የሚሸጠው በ1.48 ዶላር (77 ብር ከ21 ሳንቲም) መሆኑን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia