TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ14ኛ ዙር የ20/80 እና ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ። በዚህም መሰረት፦ 1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃፍቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነታቸው የተነሱ በቁጥጥር ስር የዋሉ፡- 1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ 2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን፦…
" ያለመከሰስ መብታቸው ይነሳ "
የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ጥያቄ ቀረበ።
ጥያቄው መቅረቡ የተገለፀው በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ነው።
የፍትህ ሚኒስቴር #ከጋራ_መኖሪያ_ቤቶች እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር ፤ የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት ይነሳልን ጥያቄው ከጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን ስልጣንና ሃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ የቀረበ መሆኑንም አስረድተዋል።
(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር)
@tikvahethiopia

" ያለመከሰስ መብታቸው ይነሳ " የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ጥያቄ ቀረበ። ጥያቄው መቅረቡ የተገለፀው በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ጉባኤ ላይ ነው። የፍትህ ሚኒስቴር #ከጋራ_መኖሪያ_ቤቶች እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና…
#NewsAlert
የዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ /ያለመከሰስ መብት ተነሳ።
የደገፉ የምክር ቤት አባላት ፦ 93
ድምፀ ተአቅቦ ፦ 6
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል እና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ የተደረገው በፍትህ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ ነው።
የህግ ከለላው የተነሳው ከቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን ስልጣንና ሃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ ነው።

#NewsAlert የዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ /ያለመከሰስ መብት ተነሳ። የደገፉ የምክር ቤት አባላት ፦ 93 ድምፀ ተአቅቦ ፦ 6 የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል እና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ሙሉቀን ሀፍቱ የህግ ከለላ እንዲነሳ የተደረገው በፍትህ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ ነው። የህግ ከለላው የተነሳው ከቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን…
#የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች #ፍትህሚኒስቴር
ፍትህ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ ላይ (ከዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት መነሳት ጋር የተያያዘ) ፦
" ... ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ምሩፅ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ቀርበው በሰጡት መግላጫ እንዲሁም በእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ላይ ለህዝብ በይፋ በሰጡት ማብራሪያ ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ቴክኖሎጂውን አልምቶ የጨረሰ በመሆኑ ቴክኖሎጂው ከሰው ንክኪ ነፃ በመሆኑና በኢንሳ በኩል ተፈትሾ ማረጋገጫ ያገኘ እንዲሁም ለዕጣው አወጣጥ ከባንክ የተላከው ዳታ በአግባቡ የተጫነ መሆኑ ማረጋገጫ ሰጥተው ነበር።
መስተዳደሩም የኃላፊውን ማረጋገጫ በመቀበል እና በማመን ዕጣው ሐምሌ 1 በህዝብ ፊት እንዲወጣ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከተሰጠው ማረጋገጫ በተቃራኒ ከፍተኛ ከፍተኛ የሆነ የዳታ ማጭበርበር ተግባር የተፈፀመ መሆኑ አመላካች መረጃ በማግኘት ኦዲት እንዲደረግ አቅጣጫ ተሰጥቶ እንዲፈተሽ ተደርጓል።
በዚህ መሰረት ከኢንሳ ፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ከኢኖቬሽን ሚኒስቴር በተዋቀረው የባለሞያ ቡድን በተደረገው ማጣራት ፦
1ኛ. ሲስተሙ አዲስ እና የገባው ዳታ በማንም ያልታየ ለመሆኑ ለከተማው አመራር ጭምር በኃላፊው ማረጋገጫ የተሰጠ ቢሆንም ዕጣው ከመውጣቱ በፊት ወደ ኮምፒዩተሩ የገባውን ዳታ ለአምስት ጊዜ የተመለከቱ መሆኑ፤
2ኛ. ለዕጣ ብቁ ናቸው ተብሎ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተላከው 79 ሺህ ተመዝጋቢዎች በላይ ለዕጣው ብቁ ያልሆኑ 73 ሺህ ሰዎችን በድብቅ ወደ ኮምፒዩተሩ በመጫን የተጠቃሚዎችን ቁጥር ወደ 172 ሺህ እንዲያድግ ያደረጉ መሆኑ፤
3ኛ. ኃላፊው ከቤቶች ልማት የተላከውን የተወዳዳሪዎችን መረጃ ለሚያስገባ ባለሞያ ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ እንዲሰራ ማድረግ ሲገባቸው በቀጥታ ለአልሚው በመስጠት የዳታ ማጭበርበሩ እንዲፈፀም ያስደረጉ መሆኑ፤
4ኛ. ሲስተሙ የማልማት ተግባሩ አለም አቀፍ ስታንዳርዱን ያልጠበቀና የሚና መደበላለቅ የታየበት በተለይም ሶስቱን አካላት አልሚውን፣ የተጠቃሚውን እና አረጋጋጩን አካላት የሚና ክፍፍል የሌለበት እና ሁሉም በአንድ ሰው ማለትም በአልሚው ብቻ የተሰራ በመሆኑ አሁን ለተከሰተው ማጭበርበር በር እንዲከፍት ያደረገ መሆኑ፤
5ኛ. ዳታው የተጫነበት ኮምፒዩተር አዲስ እና የዳታ አጠቃቀሙን ከእጅ ንክኪ ነፃ እንዲሆን የሚፈልግ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ኮምፒዩተሩ ለስራው የማይፈለግ ባዕድ ሶፍትዌር ጭምር የተጫነበት ከመሆኑ በላይ የዕጣ አወጣጥ ሂደቱን በኦንላይን ጭምር እንዲከታተሉ የሚያስችል የነበረ መሆኑ ፤
6ኛ. ስለደህንነቱ ምንም አይነት ፍተሻ ባልተደረገበት ቴክኖሎጂ በኢንሳ ተፈትሾ ችግር እንደሌለበት ማረጋገጫ የተሰጠበት ነው በሚል የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ የከተማ አስታዳደር አመራሩን በማሳሳት ዕጣ እንዲወጣ ያስደረጉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።
በአጠቃላይ ዕጣውን ለማውጣት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ ወይም ሲስተም የአሰራር ስርዓቱን ያልተከተለ፣ አግባብ ባለው ተቋም ያልታየና ምንም አይነት የደህንነት ማረጋገጫ ያልተሰጠበት፣ ለማጭበርበር የሚረዳ ባዕድ ሶፍትዌር የተጫነበት ፣ ለዕጣው ብቁ ናቸው ተብሎ ከሚመለከተው አካል ተረጋግጦ ከተላከው ዳታ ውጭ ሌላ ዳታ ማስገባት መረጃ መጨመር፣ ማጥፋት እንዲሁም ማስተካከል የሚያስችል እድል ለአልሚው በድብቅ የሚሰጥ ስለመሆኑ ማረጋገጥ ተችሏል።
ድርጊቱ በቢሮው ኃላፊ እና በስሩ የተሳተፉት ሌሎች ግለሰቦች የተፈፀመ መሆኑ ተረጋግጦ አብዛኛዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የወንጀል ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። "

#የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች #ፍትህሚኒስቴር ፍትህ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ምክር ቤት በፃፈው ደብዳቤ ላይ (ከዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ያለመከሰስ መብት መነሳት ጋር የተያያዘ) ፦ " ... ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ምሩፅ ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ቀርበው በሰጡት መግላጫ እንዲሁም በእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ ላይ ለህዝብ በይፋ በሰጡት ማብራሪያ ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ቴክኖሎጂውን አልምቶ የጨረሰ በመሆኑ…
#Update
ዶ/ር መሉቀን ሀፍቱ በፀጥታ ኃይሎች ተያዙ።
የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የነበሩትና ያለመከሰስ መብታቸው በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተነሳው ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ እንደወጡ ሲቪል በለበሱ ሰዎች ተይዘዋል።
ዶ/ር ሙሉቀን ከቅርብ ደቂቃዎች በፊት ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ በመውጣት ላይ ሳሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ተይዘው መወሰዳቸውን " አዲስ ማለዳ ጋዜጣ " ከስፍራው ዘግቧል።

Photo
በም/ቤቱ እራሳቸውን የተከላከሉት ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ !
" እኔ መጀመሪያ ማንሳት የምፈልገው ፤ መጀመሪያ ከግል ስብእናዬ መነሳት ፈልጋለሁ እኔ እስከማስበው ድረስ ምስኪኑ ህዝብ ቆጥቦ ቤት እንዲያገኝ ነው ፍላጎቴ ፤ ይሄ ከነበረኝ ስብእና እንፃር ሙስና የሚለው የሚገልፀኝ አይደለም።
ነገር ግን ድርጊቱ ተደርጎ ከሆነ እኔም አዝኛለሁ፤ ይሄም ጥልቅ የሆነ ምርመራ ተደርጎ ነገ ሁላችንም የምናየው ይሆናል።
ወደ ዋናው ሀሳቤ ስሄድ የአመራር ሚና ምድነው እኔ የቢሮ ኃላፊነ ነኝ፣ በተለይ የቢሮ ኃላፊ ስሆን አጠቃላይ strategic የሆነ direction ነው የምሰጠው።
እነዚህ የ routine የሆኑ ስራዎች ላይ ስራዎችን አልሰጥም። ነገር ግን በዚህ ሂደት ማየት የሚገባኝን የአመራር ክፍተቶችን እወስዳለሁ። እሱን የምክደው አይደለም።
እኔ በ Presentation ላይ በኢንሳ ተረጋገጠ አላልኩም። የቪድዮ ቅጂ ስላለ እሱን ማየት ይቻላል። ነገር ግን እንዴት ነበር የሚለውን ለዚህ ምክር ቤት ለታሪክ መቅረት ስላለበት ማቅረብ ይገባኛል።
መጀመሪያ ለዕጣው ዝግጁ ስናደርገው ከ9 ወር በፊት ነው ይሄ ስራ ያተጀመረው ይሄ ስራ ከተጀመረ በኃላ መጀመሪያ የተደረገው ለኢኖቬሽን ... እ "
የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ወ/ሮ ሱፌና አልከድር ፦
" የተከበሩ ዶ/ር ሙልቀን ... በሂደቱ ላይ ሳይሆን "
ዶ/ር ሙሉቀን ፦
" አይደለም ሀሳቤን ... "
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" በቀረበው ላይ ብቻ አስተያየት ይስጡ "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" ገብቶኛል ክብርት አፈጉባኤ ... "
የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ ፦
" እሱን ፍርድ ቤት የማያጣራው ጉዳይ ይሆናል "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" አይደለም፤ ይሄ ም/ቤትም... ለመደመጥም እንትን ልሁን ምክንያቱም ይሄ ምክር ቤትም ማወቅ የሚገባውን አካሄዱን ማወቅ ስለሚገባው ስላለበት ነው መናገር ያለብኝ ።
ስለዚህ በሂደቱ አስተያየት መስጠት ያለብኝ በዚህ መልክ ነው።
ሎተሪው ዕጣ ከመውጣቱ በፊት 2 ደብዳቤ በህዳር 17 /2014 በአብርሃም ተፈርሞ ለኢኖቬሽን ሚኒስቴር እና ለኢንሳ የሞያዊ ድጋፍ ኣስፈላጊድን እንድታደርጉ ብለን ፅፈናል።
የኢኖቬሽን ሚኒስቴር በታህሳስ 26/2014 በደብዳቤ ምክረ ሀሳብ ሰጥቶናል። ከዛ በምክረ ሀሳቡ መሰረት የሚስተካከለውን አስተካክለናል። ኢንሳን በተመለከተ ግን ምንም አይነት ነጥብ አልሰጠንም personally እንደውም ዶ/ር ሹመቴን አግኝቼ ለማውራት እባክህን...ክብርት ያስሚንም ስላለች ክብርት ያስሚንም ደውላለት እንደውም ፍቃደኛ ያልሆነበት ሁኔታ ነበር የነበረው። ዕጣው ከመውጣቱ በፊት የነበረው ሂደት ይሄው ነው።
ሰኔ 21 ቀን 2014 በአቶ ሽመልስ የተፃፈ ደብዳቤ ተወካይ ይመደብልን በተባለው ሰዓት ..."
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" በጣም ያሳጥሩልን "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" አሳጥራለሁ ግን ካልተሰማሁ at least ይሄ ምክር ቤት ይስማኝ ካዛ በኃላ ችግር የለውም ሌላውን ነገር ..."
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" ማለት ይሄ የተከበረው ምክር ቤት ይሄንን ከማጣራት ስልጣን የለውም፤ የማጣራት ስልጣን ያለው ፍትህ ሚኒስቴር ነው "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" ለታሪክ መቀመጥ ስላለበት እኔ ከግል ስብእናዬ ከከፈልኩት የፖለቲካ ዋጋ ካለኝ ነገር ይሄ ምክር ቤት understand አድርጎ ለታሪክ መቀመጥ ስላለበት ነው። ይሄን መናገር የፈለኩት።
ከይቅርታ ጋር ክብርት አፈጉባኤ ባያቋርጡኝ ብቀጥል። አጭር አጭር አድርጌ ልግለፅ።
ስለዚህ ሰኔ 21 ቀን በአቶ ሽመልስ በተፃፈው ደብዳቤ የዘርፉ ምክትል ኃላፊ ለሆኑት ለአቶ አብርሃም ደርሷቸዋል። "
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" አሁንም ላስቆሞት ነው። አልፈቅድም። ሁሉንም ዝርዝር እንዳያቀርቡልን አልፈቅድም "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" አጭር ነው ፤ ሀሳቤን ወይም ደቂቃ ይስጡኝና... "
የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ፦
" ሀሳቡን አጭር አድርገው፣ የሚቃወሙትን ነገር ላይ ብቻ "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍታ፦
" ክብርት አፈ ጉባኤ የምቃወመው ይሄን ሀሳቤን ገለፅኩኝ በኃላ ነው "
የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ፦
" ለማስቆም እየተገደድኩ ነው "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ፦
" እሺ በምን ልናገር ታዲያ ? "
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" በጣም በማሳጠር "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" እሺ፣ ችግር የለውም ! በጣም አሳጥራለሁ። የምክር ቤት አባላትን በጣም ይቅርታ ጠይቃለሁ። ማወቅ ስላለባችሁ ነው።
ሰኔ 21 ቀን በአቶ ሽመልስ የተፃፈው ደብዳቤ እኔ ሰኔ 21 ምናልባት በጊዜው አልነበርኩም በባለቤቴ ወሊድ ምክንያት በዚህ ሰዓት ዳታ ሲቀበሉ፣ እንዲህ ያለውን ደብዳቤ ሲፃፃፉም በጊዜው አልነበርኩም።
የኔ ምክትል የነበረው ግን ይሄንን ዳብዳቤ ተቀብሎ ባለሞያ ወክልሉልን ባለን መሰረት ለሶፍትዌር ዳይሬክተር ባለሞያ እንዲወክል ፅፏል።
ከዛም በድጋሚ አቶ ሽመልስ ሰኔ 21 የቤት መረጃ ለቢሯቹ የላክን መሆኑን ይላል። እዚህ ጋር አቶ ሽመልስ አጠቃላይ የቤት ምዝገባ ያተደረጉበትን፣ ዕጣ የሚወጣባቸውን አቶ ሽመልስ ልኳል።
እኔ በዛ ሰዓት ስላልነበርኩ ምክትሌ አቶ አብርሃም አሁንም ይሄንን ለሶፍትዌር ዳይሬክተሮች መርቶ ወደባለሞያው የገባበት ሁኔታ አለ።
ለምን ይሄን አነሳሁኝ ለሚለው ሁለት ነገር ነው።
አንደኛው ዕጣ ከመውጣቱ በፊት ክብርት ያስሚንም እንደውም እኔ አልነበርኩም ክብርት ያስሚን የእኔ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ይዛ ቢሯችን መጥታ እዛ ስላልነበርኩኝ ያለውን ነገር ውይይት አድርጋ ሲስተሙ እንዴት ነበር ተብሎ display ተደርጎ ነበር እሱ በማየት ደረጃ እሳቸውም ስላሉ ይገልፁታል።
ሌላው ከ4 በላይ ሙከራ ተደርጓል የተባለው ምናልባት ክብርት ከንቲባ ባሉበት ሙከራ አድርገናል። ከዛም በኃላ ይሄ ኮምፒዩተር እኛ አዲስ ብለን ነው የሰጠነው። እንግዲህ ይሄ too በጣም technical እኔ የተማርኩት በሰላምና ደህንነት more of social science ነው። እኔ strategically በሆነ way ነው እንጂ መሥጠት ያለብኝ ምን አይነት algorithm ተጠቅሟል፣ behind የሰራውን ምን አይነት ሶፍትዌር ይጫን የሚልውን ነገር እኔ አላውቀውም።
ነገር ግን ይሄ ኮምፒዩተር አዲስ ነው። ከግዢ የሰጠነው ነው። ሰጠን ባለሞያው ይጠቀምበት ይሄን ያድርግበት እኔ እንደ አመራርነቴ ወርጄ የማየት role አለኝ ብዬ አላስብም።
ዕጣው ከመውጣቱ ለፊት ማታ ታሸገ፣ ከታሸገ በኃላ ታዛቢ ባለበት ታሸገ፣ ምንም ዳታ እንደሌለው ታይቶ ታሸገ። እኔ ኮምፒዩተሩ ጋርም ቀርቤ አላውቅም። ከዛ በነገታው መጡ ክብርት ያስሚን ባለችበት ሌላም ታዛቢ ባለበት በሩ ተከፍቶ ተገባ ካዛ ኮምፒዩተሩ ታየ ከዛም ክብርት ከንቲባ ባለችበት ያሬድ የሚባል ባለሞያ በቴክኖሎጂ የታወቀ ነው እሱ ይየው ተብሎ መጣ ያሬድ የሚባለው ሰውዬ ክሊክ አድርጎ ያለውን ነገር ጠቅላላ አየ መሄድ ይችላል ብሎ እዛው confirmation ሰጠን ምክንያቱም ክብርት ያስሚንም ስላሉ በዚህ መሰረት ወደ እጣው መጣ።
ወደ ዕጣው ሢመጣ presentation ተዘጋጀ፣ ከዛም ለቢሮው ይመጥናል አንተ ብታቀርበው ተብዬ እንዳቀርብ ተደረገ፤ ከዛ ውጭ Presentation ላይ ያቀረብኩት ደግሞ አንዱ ነገር ጠቅላላ የተሰጠኝን ሀሳብ ነው።
ለምሳሌ ከታች ባለሞያ አለ ከባለሞያው በላይ ዳይሬክተር አለ፣ ከዳይሬክተር በኃላ..."
ዶ/ር ሙሉቀን ይህንን እየተናገሩ እያሉ በቀጥታ በአዲስ ቴሌቪዥን ለህዝብ ሲሰራጭ የነበረው ንግግር ተቋርጧል። በኃላም ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል።

#Update ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ እንዲሁም አባቱ አቶ ኢሳያስ ገ/ወልድ እንዲሁም የቤተሰቡ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌው ቢታኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅን ውሳኔ እንደማይቀበለቱ ገለፁ። ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን እንዲቀለብስ እና ተማሪ ቢንያምን ከ4 ዓመት በላይ ወደለፋበት የትምህርት ገበታው እንዲመልሰው ጠይቀዋል። ይህንን የጠየቁት " ሸገር ኢንፎ " በሚሰኝ የዩትዩብ ገፅ ላይ በቀረቡበት…
#Update
ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል ተወስኗል።
የተማሪ ቢንያም ኢሳያስን ትምህርት በተመለከተ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
በመግለጫው ፤ የተማሪ ቢንያም ኢሳያስን ትምህርት በተመለከተ ለተማሪው የትምህርት ሂደት ይረዳሉ ያሏቸውን አማራጮች መቅረቡን አስታውሷል።
ሆኖም ተማሪ ቢንያም ብቸኛ ፍላጎቱ የሕክምና ትምህርትን መማር እንደሆነ ገልጿል።
በዚሁም መሠረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን በጋራ ባካሄዱት ስብሰባ ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ የሕክምና ትምህርቱን እንዲቀጥል መወሰኑ ተገልጿል።
እስካሁን የተቋረጡ ትምህርቶችንም በማካካስ ትምህርቱን ካቆመበት እንዲቀጥል ይደረጋል ተብሏል።
ምንም እንኳን የትምህርት ሂደቱ ከባድ እና ውስብስብ ቢሆንም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና የሕክምና ት/ቤቱ የተማሪ ቢንያምን ትምህርት የተሳካ እንዲሆን የሚችሉትን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

#መግለጫ
ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ማህበር መግለጫ ፦
" ... ጋዜጠኞችን በሥራቸው ምክንያት ብቻ የመሰወር፣ የማሰር፣ የማንገላታትና የመደብደብ ድርጊት ተባብሶ ታይቷል፡፡
ጋዜጠኞች በሰውነታቸው ጥፋት አያጠፉም የሚል ድምዳሜ ባይኖርም የሕዝብን ጥቅም ፣ መብት እንዲከበር እና ሙያውን ለማሳደግ ፣ አገር በሕግ እንዲመራ በሚያደርጉት መሠረታዊ ሥራ የመንግሥት አካል ቁጡ ሊሆን የተገባ አይደለም።
ጋዜጠኞች በሕግ ጥሰት ከተጠረጠሩ እና ተጠያቂነት ካለባቸው ብሎም በወንጀል ከተፈለጉ በሕግ አግባብ መያዝ እና መጠየቅ ሲገባቸው፣ በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ከቤተሰቦቻቸውና ከባልደረቦቻቸው እየተሰወሩ ቀናትን በጨለማ እንዲያሳልፉ መደረጉ መንግሥት ይህንን ዘርፍ ለማቀጨጭ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ሥራዬ ብሎ የያዘው አስመስሎበታል። "
🔻
" ... አንዳንድ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋዜጠኞችንና የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን የአገር ችግር ፈጣሪ አድርጎ የመሳል አዝማሚያ በግልጽ እየታየ ሲሆን ይህም ከንግግር ባለፈ በተግባር እየተስተዋለ ይገኛል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር በአሁን ወቅት ጋዜጠኞች የሚደርስባቸው ያልተገባ ወከባ እና እንግልት እንዲቆም ይጠይቃል "
🔻
" ... ፍርድ ቤቶች ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲለቀቁ የወሰኑት ውሳኔ በፖሊስ እንዳይተገበሩ መደረጋቸው የተቋሞቹን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት በመሆኑ እንዲታረም፣ መንግሥት በጎ ሲሰራ አወድሰው ፣ ጥፋትና ያልተገቡ አካሄዶችን ሲመለከቱ የሚሞግቱትን ጋዜጠኞችን በማሰርና በመደበቅ ፣ በማፈንና በማሸማቀቅ የሚያመጣው ለውጥ ለአገር የማይበጅ በመሆኑ መሰል እርምጃዎች እንዲቆሙ ማህበራችን ያሳስባል፡፡ "
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ !
የፌዴራል የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ ፤ የክልልነት ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኙ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ጉዳዩን የአመጽና የሁከት መነሻ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
ከመግለጫው የተወሰደ ፦
" የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በስሩ የሚገኙ ዞኖችን በአዲስ መልክ ለማዋቀር እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
ጌዲኦም በአዲስ መልክ ከሚዋቀሩ ዞኖች አንዱ ሲሆን፤ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በተጨባጭ ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ሰሞኑን የማወያያ ሰነዶች ተዘጋጅተው የዞኑ ነዋሪ እየመከረበት ነው።
ይሁንና የጌዲኦ ዞን የክልልነት ጥያቄ መፍትሔ የማይሰጠው ከሆን ጥያቄያችንን በኃይል እናስፈጽማለን የሚሉ አካላት በህቡዕ ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ በተጨባጭ ተረጋግጧል።
በህቡዕ የተደራጁት አካላት የጥፋት እቅዶቻቸውን ለማሳካት ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች በመክፈት የተዛቡና የፈጠራ መረጃዎችን እያሰራጩ ሲሆን ማኅበረሰቡንም በተሳሳቱ መረጃዎች ለማደናገር እየሞከሩ ይገኛሉ።
እነዚህ አካላት ያደራጇቸው ግለሠቦችና ቡድኖች #ቤት_ለቤት ጭምር እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ፤ ይህም ባግብረኃይሉ ተደርሶበታል።
ለዚህ እኩይ ዓላማ የተደራጁና የተሰለፉ ግለሠቦችንና ቡድኖችን በደኅንነትና በጸጥታ መዋቅር አማካኝነት ተለይተው ክትትል እየተደረገባቸው ነው። ይህን በማስገንዘብ፤ ከጥፋት ተልዕኳቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
ይህን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ እናስጠነቅቃለን። "

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሰራተኛ ማህበር አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄዱን ገለፀ።
ጉባኤው ትናንትና እና ዛሬ ነው የተካሄደው።
ትላንህ ጉባኤው በማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ፣ በአየርመንገዱ የሰዉ ሀብት ም ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘነበወርቅ ገ/ጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን የማህበሩ የስራና የኦዲት ሪፓርቶች፣ የማህበሩ የ2022/2023 በጀትና እቅድ ውይይትና ማጽደቅ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።
የማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በዛሬው ውሎ ከድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰውና ከፍተኛ የማኔጅሜንት አባላት ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከሰራተኞች በተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ምላሽ ተሰቶባቸዋል።
ጠቅላላ ጉባኤው ለተለያዩ የሰራተኛ ተወካዮች ፣ የተመሰገኑ የስራ መሪዎችን የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጠ ሲሆን ፤ የአየርመንገዱ ሰራተኞች የማህበሩን ፕሬዝዳንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳን በማህበሩ ላስመዘገቡት ለውጥ ከፍተኛ ሽልማት እንዲሁም የአየር መንገዱን ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክቷል።
በሌላ በኩል ጉባኤው ታግዷል ፣ አልተካሄደም በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰራጩት መረጃዎች ውሸትና አሉባልታ ናቸው ያለው ማህበሩ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ ነው የተጠናቀቀው ሲል ገልጿል።