TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ፍርድ

በጉራ ፈርዳ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አንዲደርስ ያደረጉ 45 ተከሳሾች እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አንዲቀጡ መወሰኑን የፍትህ ሚኒስቴር አሳውቋል።

በደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አንዲደርስ ያደረጉ 45 ተከሳሾች እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት አንዲቀጡ ተወሰኖባቸዋል ።

የቅጣት ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ነው ።

ተከሳሾች ከ2011 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11/2013 ዓ.ም ባሉ ጊዚያት የተለያዩ አጋጣሚዎችን በመጠቀም በወረዳው የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ምንም መሬት የላቸውም፤ መሬታችንን ለቀው መሄድ አለባቸው በማለት በደቡብ ክልል በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ የሸኮና የመዠንገር ብሔረሰቦች በአማራ ብሔር ላይ የጦር መሳሪያ አንስተው የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ለማድረግ በማሰብ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በጉራ ፈረዳ ወረዳ ጌኒቃ ቀበሌ ሌንጣ መንደር አንድ የሸኮ ብሔረሰብ ተወላጅ ተገድሎ በመገኘቱ ይህን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ገዳዩ ማን እንደሆነ ባልታወቀበት ሁኔታ ልጃችንን የገደሉት አማራዎች ናቸው፤ የእኛ ሰው ሞቶ አማራ እዚህ ሀገር ቆሞ አይሄድም በማለት ሌሎች የጦር መሳሪያ እንዲያነሱ በማድረግ ፦

- የ30 (ሰላሳ) ሰዎች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አንዲጠፋ፤

- 14 (አስራ አራት) ሰዎች የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ፤

- 3,930,850. (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ሺህ ስምንት መቶ ሀምሳ ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም

- 5,273 (አምሰት ሺ ሁለት መቶ ሰባ ሶስት ) የሚሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ያደረጉ በመሆኑ ተከሳሾች በህብረትና በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈፀሙት የእርስ በርስ ጦርነት ማስነሳት ወንጀል በጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ የተደራጁና ደንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶ ነበር።

ዐቃቤ ህግ ወንጀሉ በተፈፀመበት ቦታ በመገኘት ከፖሊስ ጋር በመሆን ከወንጀል ምርመራው አንስቶ ክስ መስርቶ ሲከራከር እንዲሁም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን ሲመለከተው ከቆየ በኋላ በ45 ተከሳሾች ላይ እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

በዚህም መሰረት የፌዳ,ደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የሚዛን -ቦንጋ-ጋምቤላ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት በ45 ተከሳሾች ላይ የሚከተለውን የቅጣት ወሳኔ አስተላልፏል።

➡️ ኮ/ብል ኢሳቅ ጃፍሮ የተባለ #ፖሊስን ጨምሮ ስምንት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ23 ዓመት ፅኑ እስራት፤

➡️ ሶስት ተከሳሾች በ18 ዓመት፣

➡️ አራት ተከሳሾች በ16 ዓመት ፣

➡️ አራት ተከሳሾች በ15 ዓመት ፣

➡️ ሰባት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት

➡️ አስራ ዘጠኝ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው ከ8 ዓመት ከ5 ወር እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።

#ፍትህ_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia