TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ከጅቢቲ ወደ የመን በማምራት ላይ ሳሉ በሰጠሙት ሁለት ጀልባዎች ውስጥ ከተጫኑት #ኢትዮጵያውያን ናቸው ከተባሉ ስደተኞች መካከል #የሞቱት ቁጥር ወደ 52 ከፍ ማለቱ ተነገረ። ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት በምህጻሩ IOM እንዳስታወቀው የህይወት አድን ሠራተኞች ከሁለቱ ጀልባዎች ተጨማሪ አስከሬኖችን በማግኘታቸው ትናንት 43 የነበረው የሟቾቹ ቁጥር ዛሬ ወደ 52 ከፍ ብሏል። 16 ሰዎች ከአደጋው መትረፋቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። በአደጋው የሞቱት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እስካሁን በግልጽ አልታወቀም። ድርጅቱ አንደኛዋ ጀልባ 130 ሰዎችን አሳፍራ ነበር የሚል እምነት አለው። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ያነጋገረው አንድ ከአደጋው የተረፈ የ15 ዓመት ወጣት ቁጥራቸው 80 ከሚሆን ኢትዮጵያውያን ጋር በአንደኛው #ጀልባ ተጭኖ እንደነበር ገልጿል። የጀልባዋ ነጂ ሞተሩ ከባድ #ችግር እንዳጋጠመው ከተናገረ በኋላ ጀልባዋ መስመጠም መጀመሯን እርሱ ግን ከባህር ውስጥ በጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ #ተጎትቶ መውጣቱን ወጣቱ ተናግሯል። ጦርነት እየተካሄደባት ቢሆንም ወደ #የመን የሚደረገው ስደት እንደቀጠለ ነው።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና

16 ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው አለፈ!

ከሊቢያ ወደ ጣሊያን በባህር ሲጓዝ በነበረ #ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ የ16 ኢትዮጵያውን ዜጎች ህይወት አለፈ። ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ባጋጠመው በዚህ አደጋ 16 የትግራይ ተወላጆች ህይወት ማለፉን የክልሉ የህዝብና መንግስት ግንኙነት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በዛሬው ዕለት በሰጠው የሀዘን መግለጫ ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ሲጓዝ በነበረ ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ ህይወታቸው ካለፉት ዜጎች ውስጥ 10ሩ ሴቶች መሆናቸውን ገልጿል። በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ዜጎችም በክልሉ ኢሮብ ተብሎ የሚጠራው ወረዳ ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል።

የክልሉ መንግስት በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ፥ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia