TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በ2 ቀን ውስጥ በጎሳ ግጭት 400 ሰዎች ሞቱ‼️

በዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ በታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረ #የጎሳ_ግጭት የ400 ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።

በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ አካባቢ ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ ተከስቶ በነበረው የጎሳ ግጭት በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 400 የሚሆኑ ዜጎች ህይዎት አልፏል።

ግጭቱ የተፈጠረውም በዩምቢ ከተማና አካባቢው በሚገኙት #ባቴንድ እና #ባኑን በተሰኙ ጎሳዎች መካከል መሆኑ ነው የተገለፀው።

የግጭቱ ምክንያትም በአካባቢው ለመካሄድ ዝግጅት ላይ በነበረው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት ነው ተብሏል።

የባቴንድ ጎሳዎች የገዢውን መንግስት መመረጥ #የሚደግፉ ሲሆን ፥ባኑኖች ደግሞ በአካባቢው እነሱን ወክሎ የሚወዳደረውን #የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ነበሩ።

በተፈጠረው ግጭትም ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪም በርካቶች ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡

እንዲሁም በግጭቱ ብዛት ያላቸው ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

ግጭቱን ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ታህሳስ 30 ላይ በአካባቢው ሊካሄድ የነበረውን ምርጫ መሰረዙ ይታወሳል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“እኛ #ኢትዮጵያዊያን እርስ በርስ የሚያስተሳስሩ በርካታ ማንነቶች ያሉን፣ ለዘመናት የቆየ የሐይማኖት መከባበር ልምድ፣ የአኩሪ ባህል ባለቤቶች፣ አንገትን ከፍ አድርገን እንድንራመድ የሚያደርጉን የታሪክ ባለቤቶች መገኛ ነን፡፡ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ እየተነሱ ያሉ #የዘርና #የጎሳ ግጭቶች ለእንደኛ አይነት ህዝቦች #ማይመጥኑ አስነዋሪ ተግባራት በመሆናቸው ሁላችንም በቃ ልንላቸው ያስፈልጋል” የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶ/ር #ሂሩት_ካሳው

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚዲያ የሩዋንዳውን የዘር ጭፍጨፋ (ጄኖሳይድ) እንዴት አቀጣጠለ ? በ100 ቀናት ከ800,000 እስከ 1,000,000 ቱትሲዎችና ለዘብተኛ የሚባሉ ሁቱዎች ባለቁበት የሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ/ጄኖሳይድ ሚዲያዎች ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው። እንዴት ? - ራዲዮ-ቴሌቭዥን ሊብሬስ ዴስ ሚልስ ኮሊንስ (RTML) እንዲሁም መንግታዊው ' ሬድዮ ሩዋንዳ ' በቱትሲዎች ላይ በመላ ሀገሪቱ ጥላቻ እንዲፈጠርና የሩዋንዳ…
#Kwibuka

" ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " - ፖል ካጋሜ

ከ30 ዓመታት በፊት በሩዋንዳ በ100 ቀናት ብቻ እስከ 1,000,000 ሚደርሱ ሰዎች የተጨፈጨፉበት የሩዋንዳ ዘር ፍጅት እየታሰበ ይገኛል።

የዘር ፍጅቱ የተፈፀመበትን 100 ቀናት ታሳቢ በማድረግ ከሚያዚያ 7 (እ.ኤ.አ) አንስቶ ለ100 ቀናት የዘር ጭፍጨፋው ሰለባዎች ይታሰባሉ ፤ ይህም ኪውቡካ /Kwibuka/ ይባለል።

ከሳምንት በፊት በኪጋሊ በነበረ ስነስርዓት ላይ ፕሬዜዳንት ፖል ካጋሜ ፤ ከዘር ፍጅቱ በህይወት የተረፉ ዜጎች ለብሄራዊ አንድነት ሲሉ ስላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

" እጅግ የሚከብደውን የእርቀ ሰላም ሸክም እናተ እንድትሸከሙ ጠየቅናችሁ እንሆ ለሀገራችን ስትሉ ይሄንን በየቀኑ ማድረጋችሁን ቀጥላችኃል ስለዚህ እናመሰግናችኃለን " ነው ያሉት።

ፖል ካጋሜ ፥ አሁንም ድረስ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት #የጎሳ_ፖለቲካ እየተባባሰ መሄዱን እና የብሄረሰብ ማጽዳት አደጋ መደቀኑን በማንሳት አስጠንቅቀዋል።

" ሩዋንዳ ውስጥ የደረሰው መከራ ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል። ክፍፍል እና ፅንፈኝነት ካልተገታ በማናቸውም ቦታ ወደ ዘር ማጥፋት ሊያመራ ይችላል " ብለዋል።

ሩዋንዳ መከራ ውስጥ በገባችበት ጊዜ በርካታ ሀገራት የሰላም አስከባሪ ልጆቻቸውን ሩዋንዳ መላካቸውን እና እነዛም ወታደሮች ለሩዋንዳ እንደደረሱላት ገልጸዋል።

" ነገር ግን #በጥላቻም ይሁን #በፍራቻ ያልደረሰልን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ በወቅቱ በነበረው የሁቱ መንግሥት መሪነትና የሁቱ ብሄረሰብ አባላት በሆኑ ጽንፈኛ አክራሪዎች እንዲሁም በመንግሥት በሚደገፈው የ " ኢንተርሀምዌ '  ሚሊሻ አማካኝነት እስከ 1,000,000 ቱትሲዎች ፣ ለዘብተኛ ሁቱዎችና ትዋዎች ተጨፍጭፈዋል።

Rwandan genocide
Apr 7, 1994 – Jul 15, 1994
AP / VOA

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia