#Russia
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጸረ ኑክሌር ኃይላቸው በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዙ፡፡
ፑቲን ከገቡበት የዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከምዕራባውያን ሃገራት ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ጦሩ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ እንዲሆን ያዘዙት፡፡
ዛሬ ከከፍተኛ ባለስልጣናቶቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) አባል የሆኑ ሃገራት ጠንከር ያለ መግለጫ እያወጡ መሆኑን እና ማዕቀቦችን እየጣሉ በመሆኑ ጸረ ኑክሌር ኃይሉ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዋል፡፡
ትዕዛዙ ለሃገሪቱ ጦር አመራሮች የተሰጠ ነው፡፡
ይህ ሁኔታውን የበለጠ እንዳያባብሰውና ወዳልተፈለገ አስከፊ #የኑክሌር_ጦርነት እንዳያመራ ተሰግቷል፡፡
የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎችንም እርምጃዎችን በሚወስዱ እና ጣልቃ በሚገቡ ሃገራት ላይ ጠንከር ያለ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲያስጠነቅቁ ነበር።
#አልዓይን
@tikvahethiopia