TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️የሰብአዊ መብት ተሟጋች እና አርቲስት ታማኝ በየነ 150 ግራም ወርቅ ተበረከተለት፡፡ ትላንት ምሽት በአቫንቲ ብሉናይ ሪዞርትና ሰፓ በተካሄደው የእራት ግብዣ የባሕር ዳር ነዋሪዎች #ለታማኝ_በየነ 150 ግራም #ወርቅ አበርክተውለታል፡፡ የእንጅባራ ከተማ የለውጥ ደጋፊ ወጣቶች ደግሞ በስሙ የተሰራ ጭራ አበርክተውለታል፡፡ለባለቤቱ አርቲስት #ፋንትሽ_በቀለ የአካባቢውን የሚገልጽ የባህል ልብስ ተበርክቶላታል፡፡

©AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኃይሌ የለመደብህ #ወርቅ እንጂ ብር አይደለም›› ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ
.
.
የሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ኩባንያ የሆነው ማራቶን ሞተርስ ከቀረጥ የ155 ሚሊዮን ብር ገቢ በማስገኘት ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. የግብር ከፋዮች የማበረታቻ ዕውቅና ሽልማት የብር ደረጃ ተሸላሚ መሆን ችሏል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ኃይሌ የለመደብህ ወርቅ እንጂ ብር አይደለም›› በማለት በቀልድ መድረኩን አዋዝተውት ነበር፡፡ 

Via #reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጎይቶቶም ገ/ስላሴ 🇪🇹 ወርቅ 🥇 ! @tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ጎይቶቶም

ምን አይነት ድንቅ የሆነ ውድድር ነው ፤ ምን አይነት ጀግንነት ነው ፤ምን አይነት አይበገሬነት ነው ? ጎይቶቶም ገ/ስላሴ በድንቅ ብቃት ባለድል ሆናለች።

ኢትዮጵያ በጎይቶቶም አማካኝነት 3ኛውን #ወርቅ አግኝታለች።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia
ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች !

ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲካሄድ ሰንብቷል።

በዚችም ሀገራችን በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ ተሳትፋለች።

የአትሌቲክስ ቡድናችን በሻምፒዮናው ፦

🥇6 ወርቅ
🥈5 ብር
🥉1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች በማግኘት ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን በመከተል 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀናል።

የተመዘገበው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ #ከፍተኛው ውጤት ነው።

ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው።

ሜዳሊያ ያስመዘገቡ የነገዎቹ የሀገር ተስፋዎች እነማን ናቸው ?

#ወርቅ

🥇ኤርሚያስ ግርማ (800 ሜትር)
🥇መልክነህ አዘዘ (3000 ሜትር)
🥇አዲሱ ይሁኔ (5000 ሜትር)
🥇ሳሙኤል ዱጉና (3000 ሜትር መሰናክል)
🥇 ብርቄ ሀየሎም (1500 ሜትር)
🥇መዲና ኢሳ (5000 ሜትር)

#ብር

🥈ኤርሚያስ ግርማ (1500 ሜትር)
🥈ሳሙኤል ፍሬው (3000 ሜትር መሰናክል)
🥈ፅዮን አበበ (3000 ሜትር)
🥈መልክናት ውዱ (5000 ሜትር)
🥈ሲምቦ አለማየሁ (3000 ሜትር መሰናክል)

#ብር

🥉መሰረት የሻነህ (3000 ሜትር መሰናክል)

እንኳን ደስ አለን አላችሁ !

ይቀላቀሉ : @tikvahethsport
https: //t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

አማኔ በሪሶ #ወርቅ አመጣች ❤️

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ያለምዘርፍ የኃላው እስከመጨረሻዎቹ ኪሎሜትሮች ከመሪዎች ተርታ ሆና ብትመጣም 5ኛ ደረጃ ወጥታለች። ያለምዘርፍ በከፍተኛ ድካምና ህመም ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው። ያለምዘርፍን የቀደሟት የሞሮኮ እና የእስራኤል አትሌቶች ናቸው። ፀሀይ ገመቹ ውድድሩን ብታቋርጥም ያበረከተችው የቡድን ስራ የሚይኮራ ነው። #ጀግኖች @tikvahethiopia
ፎቶ፦ ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ጀግናዋ አትሌት አማኔ በሪሶ #ወርቅ ፤ ጀግናዋ አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ #ብር ለሀገራቸው አስገኝተዋል።

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኃላ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የተወሰዱ ፎቶዎችን ከላይ ይመልከቱ።

https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

ፎቶ፦ Tikvah Ethiopia Sport (Hungary , Budapest)

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ❤️

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን በዛሬው ዕለት መካሄዱን በጀመረው የሪጋ የአለም የጎዳና ላይ ሻምፒዮና የተለያዩ ድሎችን ማስመዝገብ ችለዋል።

በወንዶች የ 5ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት በሀጎስ ገብረሕይወት #ወርቅ እና ዮሚፍ ቀጀልቻ #የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችለዋል።

ሀገራችን የአለም ሪከርድ በሰበረችበት የአንድ ማይል ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በሴቶች የ 5ኪ.ሜ ውድድር አትሌት እጅጋየሁ ታዬ #ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሯን አጠናቃለች።

የሜዳሊያ ሰንጠረዡን የሚመሩት ሀገራት እነማን ናቸው ?

1. ኢትዮጵያ :- ሁለት ወርቅ ፣ ሁለት ብር እና አንድ ነሐስ

2. ኬንያ :- አንድ ወርቅ ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ

3. አሜሪካ :- አንድ ወርቅ እና አንድ ነሐስ

via @tikvahethsport

@tikvahethiopia