TIKVAH-ETHIOPIA
በዛሬው ዕለት 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ይካሄዳል። ምክር ቤቱ በስብሰባው ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014 ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የሚቀርበውን የውሳኔ ሃሳብ በመመርመር ያፀድቃል። @tikvahethiopia
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በህ/ተ/ም/ቤት ፀደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ6 ወራት ተፈጻሚ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአንድ ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።
#ተጨማሪ_መረጃ ፦ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድን ፤ አቶ ለማ ተሰማ - በሰብሳቢነት ፤ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ- በም/ሰብሳቢነት ይመሩታል።
መርማሪ ቦርዱ ሌሎች አምስት አባላት አሉት።
@tikvahethiopia

#AddisAbaba ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል። በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ ኮምዶሚኒየም በሁለት ህፃናት ላይ እጅግ አሰቃቂ ግድያ መፈፀሙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ ሲሆን ፤ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ የምትሰራ አንዲት ግለሰብ ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ…
የፖሊስ መልዕክት !
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ የሰጡት ቃል ፦
" ምንም በማያውቁት ጉዳይ በህጻናቱ ላይ የተፈጸመው ይህ አሰቃቂ ወንጀል ሁሉንም በእጅጉ አሳዝኗል።
ወላጆች የሚቀጥሯቸው የቤት ሠራተኞችን ማንነት ጠንቅቀው ማወቅ ይገባቸዋል።
እንደ ቤተሰብ ሆነው የሚኖሩ የቤት ሠራተኞች እንዳሉ ሁሉ እንደዚህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል የሚፈጽሙም ስላሉ ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። "
#ተጨማሪ_መረጃ ፦
• በአንድ ቀን በአሰቃቂ ሁኔታ ሁለት ታዳጊ ልጆቻቸውን ያጡት ወላጆች በከባድ ሐዘን ውስጥ ይገኛሉ።
• ወንጀሉ በተፈጸመበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችም በእጅጉ ተረብሸው ነው የሚገኙት።
• ፖሊስ በወንጀሉ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ነው።
- ተጠርጣሪዋ ህጻናቱን አንቃ እና ስለት ተጠቅማ በአስቃቂ ሁኔታ መግድሏ የሚያመላክቱ መላምቶች አሉ።
- ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ለመፈጸም ምን እንዳነሳሳት ለማወቅ ምርመራዎች እየተካሄዱ ነው።
- በወንጀሉ የተጠርጠረችው ግለሰብ በቤት ሠራተኛነት ግድያው ለተፈጸመበት ቤተሰብ ስታገለግል ቆይታለች።
• ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው ወላጆች የሌሉበትን ሰዓት ጠብቃ ነው።
መረጃው ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ የአማርኛ አገልግሎት ከሰጡት ቃል የተወሰደ ነው።
#AddisAbabaPolice