TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ደብዛው የጠፋው ጋዜጠኛ⬇️

የቱርክ ፕሬዚዳንት #ጣይብ_ኤርዶሃንና የሳዑዲው ንጉስ #ሳልማን_ቢን አብዱልአዚዝ ደብዛው በጠፋው ጋዜጠኛ ጉዳይ ላይ በስልክ #ተወያዩ

ጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጊ ከሁለት ሳምንት በፊት ቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ ኮንስላ ጽህፈት ቤት ጉዳይ #ሊያስፈፅም እንደገባ ደብዛው ከጠፋ 13 ቀናት ተቆጥረዋል።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ጣይብ ኤርዶሃንና የሳዑዲው ንጉስ ሳልማን ትናንት ሌሊት በስልክ ባደረጉት ውይይት የጋዜጠኛው መጥፋት ጉዳይ አጀንዳቸው ነበር ተብሏል።

ኤርዶሃን በጀማል ካሾጊ ጉዳይ ላይ ጥምር ቡድን ተቋቁሞ ምርመራ እንዲካሄድ በአፅንኦት መናገራቸው ተሰምቷል።

ካሾጊ በሳዑዲ ቆንስላ ጽህፈት ቤት በነበረበት ወቅት 10 ሳዑዲዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት በሁለት አውሮፕላኖች ወደ ኢስታንቡል በማምራት ጽህፈት ቤቱን በተመሳሳይ ቀን መጎብኘታቸውን የቱርክ ፖሊስ መረጃዎች ያሳያሉ።

የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ አምደኛ የሆነው የሳዑዲ ዜግነት ያለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ የት እንደገባ አለመታወቁን ተከትሎ ቱርክ፣ አሜሪካ እና ብሪታኒያ ከሳዑዲ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቱርክ ጋዜጠኛው #መገደሉን የሚያሳዩ መረጃዎችን አግኝቻለሁ እያለች ነው።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዳሉት ጋዜጠኛው በቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ውስጥ መገደሉ ከተረጋገጠ ሳዑዲ ከባድ #ቅጣት ይጠብቃታል ብለዋል።

ይህን ተከትሎም ሳዑዲ በሰጠችው ምላሽ ማንኛውም ሀገር በጀማል ካሾጊ ጉዳይ ሀሰተኛ ውንጀላ የሚያቀርብ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር የሚያስብ ሀገር ካለ የአፀፋ ምላሽ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።

ምንጭ፦ አናዶሉና ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳውዲ አረቢያ አመነች‼️ሳውዲ አረቢያ ከ17 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጂ በኢስታንቡል ቆንስላዋ ውስጥ በተፈጠረ አምባጓሮ #መገደሉን አመነች። ከዚህ ጋር በተያያዘ የደህንነት መስሪያ ቤቷን ም/ኅላፊ ማባረሯን አስታውቃለች።

©BBC
@tsegawolde @tikvahethiopia
የአፋር ውሎ...🔝

በአፋር ክልል አንድ ታዳጊ በመከላከያ ሰራዊት አባላት #መገደሉን ተከትሎ #ፍትህ የጠየቁ ወጣቶች በገዋኔ፣ በረሃሌና አዋሽ አካባቢዎች መንገዶችን ዘግተው ውለዋል። በዚህም አዲስ አበባን ከጅቡቲና የትግራይ ክልልን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው መንገድ ለሰዐታት ተዘግቶ ነበር።

Via #ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba

“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” - የሟች ቤተሰብ

“ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ

ወጣት ሶፎኒያስ አስራት የሚባል ሹሬር ማክሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ/ም ከሌሊቱ 8 ሰዓት ገደማ ሰዎችን አሳፍሮ እንደወጣ አለሙለሱን፣ በመጨረሻም ሹፌሩን ገድለው ፣ ተሽከርካሪውን ይዘው እንደተሰወሩ፣ ገዳዮቹ አስካሁን #እንዳልተያዙ፣ በዚህም መሉ ቤተሰቡ መራራ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን የሟች ቤተሰብ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የሟች ቤተሰብ በሰጡት ቃል፣ “ ከላፍቶ ነበር መነሻውን ያደረገው (ልዩ ስሙ መስቀልኛ የሚባለው አካባቢ ናሆም ሆቴል የሚባል አለ)። ከዚያ ነበር ሦስቱንም ተሳፋሪዎች ማክሰኞ ከሌሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ያሳፈራቸው። መዳረሻቸውን ‘ቦሌ ሚካኤል’ ብለው ነበር መሳፈር የፈለጉት ” ብለዋል።

“ ትንሽ ወረድ እንዳለ/እንደተጓዘ ከእኔ ጋር ተገናኝተናል። አብረን የምንሰራበት ቦታ ነው። ሦስት ሰዎች እንዳሳፈረ አይቻለሁ” ያሉት የሟች ቤተሰብና የዓይን እማኝ፣ “ሶፊ ወዴት ነህ ስለው ‘መጣሁ። ቦሌ ሚካኤል አድሻቸው ልምጣ’ አለኝ። በቃ ደርሰህ ና ስራ የለም እንገናኛለን ተባባልን። በዛው እንደወጣ አልተመለሰም ” ሲሉ ሁነቱን አስረድተዋል።

አክለውም፣ ጠዋት ላይ ላፍቶ ፓሊስ ጣቢያ ሲያመለክቱ የቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ እንዲጠይቁ እንደነገሯቸው፣ ቃሊቲ ፓሊስ ጣቢያ ሲጠይቁ ፓሊስ ስለተፈላጊው ሰው ሙሉ መለያ መረጃ ከጠየቃቸው በኋላ “ እንግዲህ ጠንከር በሉ። ኤቲኤሙን አግኝተናል። አሁን ያለው ጳውሎስ ሆስፒታል ነው። አዲስ አበባ ፓሊስ ሂዳችሁ ቃል ሰጥታችሁ ትወስዳላችሁ ” ብለው #መገደሉን እንዳረዷቸውም ተናግረዋል።

“ ማሰልጠኛ ተሻግሮ ወደ አቦ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ዳር ላይ ነው ሞቶ የተገኘው። ፓሊሶች አስከሬኑን ያነሱት ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ነው። ከጥበቃ ሥራ የሚመለሱ አንድ አባት ናቸው በወደቀበት አግኝተውት ጥቆማ አድርገው ፓሊስ የሄደው ” ነው ያሉት።

“ በለበሰው ሹራብ የኮፍያ ገመድ አንቀው ነው የገደሉት። ተሽከርካሪውን ይዘው ተሰውረዋል ” ያሉት የሟች ቤተሰብ፣ ማንም ጋ ፀብ እንዳልነበር ገልጸው፣ ሙሉ ቤተሰቡ ሀዘን ላይ እንደሆነ፣ ቢያንስ ገዳዮቹ እንዲያዙ ፓሊስ ርብርብ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

ስለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ ስለሟች ሁኔታ ጠይቀው ጉዳዩን እንዲያጣሩ ፋታ እንዲሰጣቸው ከጠየቁ በኋላ በሰጡት ቃል ፣ “ አረጋግጫለሁ። ፓሊስ ሥራ ላይ ነው ያለው። የተለያዩ ዝርዝር መረጃዎችን ለመግለጽ የሚያስፈልግ የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ” ብለዋል።

“ መረጃ እየተሰበሰበ ነው ያለው ” ያሉት ኮማንደር ማርቆስ፣ “ አንተ ማክሰኞ ሌሊት 8 ሰዓት አልከኝ እንጂ፣ ስጠይቅ ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ 8 ሰዓት ላይ ነው ወንጀሉ የተፈጸመው የሚል መረጃ ነው ያለው። ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተለያዩ ሥራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት ” የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ወንጀሉ የተፈጸመው ማክሰኞ ሌሊት 8 ነው ያሉት የሟች ቤተሰብ በስህተት እንዳይሆን በሚል በድጋሚ የጠየቀ ሲሆን፣ ማክሰኞ ለረቡዕ ሌሊት 8 ሰዓት እንደሆነ፣ ረቡዕ ማታ ጣቢያ አስክሬን እንዳገኙ አስረድተዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
" ... የት እንኳን እንዳለ አላውቅም። #መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " - አባ ገዳ ጎበና ሆላ

የቱልማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሶ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) አባል የሆነ ልጃቸው መገደሉን ከማኅበራዊ ሚዲያ መስማታቸውን ተናገሩ።

ከ1 ሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል ፣ የምዕራብ አርሲ ዞን ኮሚዩኒኬሽን የ ‘ ሸኔ ’ ቡድን አባል ነው የተባለውን የአባ ገዳ ጎበና ልጅ " ሰላማዊ ሰዎችን ለመግደል ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል " ብሎ ነበር።

ኮሚኒኬሽኑ " የኦሮሞ ልጆችን ሕይወት ሲቀጥፍ የነበረው የአባ ገዳ ጎበና ሆላ ልጅ (ፎሌ ጎበና) ላይ በምዕራብ አርሲ ዞን ገደብ አሳሳ ወረዳ ውስጥ የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት ለመቅጠፍ ሲንቀሳቀስ እርምጃ ተወስዶበታል  " ነው ብሎ የነበረው።

ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አባ ገዳ ጎበና ሆላ ምን አሉ ?

- የልጃቸውን የመገደል ዜና የሰሙት በማህበራዊ ሚዲያ እንደሆነ እና እስካሁን ምንም ማረጋገጫ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

- የልጃቸውን ሞት ባያረጋግጡም በእርግጥ ልጃቸው መንግሥት ኦነግ-ሸኔ ብሎ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባል መሆኑን #አረጋግጠዋል

- ልጃቸው ፎሌ ጎበና ዕድሜው ወደ 33 ዓመት እየተጠጋ መሆኑን እና ከልጃቸው ጋር ከተያዩ 6 ዓመታት ማለፉን ገልጸዋል።

- " ከ6 ዓመታት በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀናት በፊት ፎቶ ግራፉን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የተመለከትኩት " ብለዋል።

- " የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ውስጥ እንዳለ አውቃለሁ ፤ ነገር ግን ምንም ግንኙነት የለንም። የት እንዳለም አላውቅም። መገደሉን በተመለከተም ገድዬዋለሁ ያለውን መጠየቅ ነው የሚሻለው " ብለዋል።

- ልጃቸው ሰላማዊ ሰዎች እየዞረ እንደሚገድል በመንግሥት የቀረበበትን ክስ በተመለከተ ፥ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸዋል።

- " እኔ አባ ገዳ ነኝ አልዋሽም ፤ ከልጄ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለኝም። ስልክ አንደዋወልም። ከ6 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፎቶግራፉን እንኳ የተመለከትኩት " ብለዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባል የሆነው እና የአባ ገዳው 7ኛ ልጃቸው የሆነው ፎሌ ጎበና ከቤት የወጣው የ26 ዓመት ወጣት ሳለ እንደነበረ አባቱ ገልጸዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አባ ገዳ ጎበና ልጃቸው ወደ ትጥቅ እንቅስቃሴ መግባቱን ተከትሎ ከዚህ ቀደም የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በተደጋጋሚ መኖሪያ ቤታቸው ላይ ብርበራ ማድረጋቸውን ሲናገሩ ነበር።

ከጥቂት ወራት በፊት አባ ገዳ ጎበና ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቤታቸው ላይ ብርበራ በተደረገበት ወቅት ከወላጅ አባታቸው የወረሱት የጦር መሳሪያ መወሰዱን እና ክስተቱን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን ተናግረው ነበር።

መረጃው የቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው።

@tikvahethiopia