TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ " መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ ባያውጅልንም በራስ ተነሳሽነት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቁር ልብስ በመልበስ በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማችሁን ሐዘን እንድትገልጹ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱ ከቀኑ 6:30 ላይ ዅላችሁም በያላችሁበት የአንድ ደቂቃ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

ሶስት ፓርቲዎች (እናት ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ) ከቀናት በፊት ባወጡት መግለጫ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 4 በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖች ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሐዘን እንዲገልፁ ጥሪ አቅርበው ነበር።

ፓርቲዎቹ በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች " መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ አላወጀልንም " ያሉ ሲሆን በዚህም የተነሳ በራስ ተነሳሽነት የዛሬ ሐምሌ 4 መርሀግብር ማዘጋጀታቸውን ነበር የገለፁት።

በዛሬው ዕለትም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን #ጥቁር_ልብስ በመልበስ ሐዘናቸው መግለፃቸውን ሚያስዩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያጋሩ ነው።

ከቀኑ 6:30 ላይ ኢትዮጵያውያን በያሉበት የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንዲያደርጉም ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበው የነበረ ሲሆን ይህንን የሚያሳዩ ፎቶዎች ደርሰውን ተመልክተናል።

የፓርቲዎች አመራሮችም በፅ/ቤታቸው ሻማ በማብራት ሀዘናቸውን መግለፃቸውን ተመልክተናል።

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን በማስመልከት ጾምና ጸሎት አወጀ።

ቅዱስ ሲኖዶስ አዋጁን ያስተላለፈው ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት በሰጠው መግለጫ ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በቤተክርስቲያኗ በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮች በጣሰ ሁኔታ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ ጥር 18 ቃለ ውግዘት ታላልፎ እንደነበር ገልጿል።

" ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ አልቻሉም " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ከዚህም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ነው ብሏል።

እንዲሁም የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ፣ ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግሥት ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር አልቻለም ያለ ሲሆን " ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ተረድተናል " ሲል አሳውቋል።

በዚህም " ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ " ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላልፏል።

" ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው " ሲልም አክሏል።

(ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዛሬም እስር እና ማንገላታት ቀጥሎ መዋሉን ገለፁ።

ተሚማ የተሰኘው ሚዲያ ፤ በዛሬው ዕለት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ መታሰራቸውን ገልጿል።

ሚዲያው ፤ " ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፉት የመንግሥት አካላት ሥራ አስኪያጁን ቁልፍ አስረክበው እንዲወጡ ቢነግሯቸውም አልቀበልም በማለታቸው ዛሬ ጠዋት ታሥረዋል " ሲል ነው ያስረዳው።

በሌላ በኩል በሀገረ ስብከቱ ያሉ 13 ወጣቶችም በዛሬው ዕለት መታሠራቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል በቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ዛሬ የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ጥቁር ለብሰው የዋሉ ሲሆን ጥቁር ልብስ የለበሱ ምእመናን በኮልፌ ፊሊዶሮ ልደታ፣ በቀራንዮ መድኃኔዓለምና በወይብላ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ ፖሊስ ድብደባ መፈፀሙን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሌላ በኩል በአንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጥቁር እንዳይለብሱ ፤ የቤተክርስቲያኗን ትዕዛዝ እንዳይፈፅሙ የማድረግ እንቅስቃሴ መኖሩን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል።

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ ምዕመናን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ጸሎትና ምሕላ እንዲያቀርቡ በቤተክርስቲያኗ የቀረበው ጥሪ በቀጣይ ቀናትም ተግባራዊ ሆኖ ይቀጥላል።

ፎቶ፦ የጾመ ነነዌ የፀሎት ስነስርዓት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን በማስመልከት ያወጀው ጾምና ጸሎት ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ያበቃል።

ቅዱስ ሲኖዶስ " ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ " ሲል ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት ምዕመኑን ይህንኑ ተግባራዊ ሲያደርግ ነበር።

ቤተክርስቲያኗ ፤ " ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው " ማለቷ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በጸሎትና በምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ ማሳወቁ ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰልፍ ይደረጋል ያለው በየካቲት 5/2015 ዓ.ም ሲሆን በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ፤ ቤተክርስቲያኗ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል እንዲሁም እየተፈፀመ ያለው ህገወጥ ድርጊት ለዓለም ህዝብ የሚገለፅበት እንደሆነ ማስረዳቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia