TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ ዓለም እያነጋገረ ያለው የሲሪላንካ ጉዳይ ምንድነው ? • የሲሪላንክ ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ ተወስደዋል። • ተቃዋሚዎች የፕሬዜዳንቱ መኖሪያ ቤት ጥሰው ገብተው ሲዋኙ፣ ያሻቸውን ሲበሉ፣ ሲጠጡ ታይተዋል። ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሲሪላንካ ዋና ከተማ ኮሎምቦ የሚገኘውን የፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤት ጥሰው ገብተዋል። ገብተውም በፕሬዜዳንቱ የመዋኛ…
" ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት በሰላማዊ መንገድ የሥልጣን ርክክብ እንዲኖር ነው ፤ ሕዝቡ ሕግ ሊያከብር ይገባል " - የሲሪላንካ ፓርላማ አፈጉባኤ

የሲሪለንካ ፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ አስታወቁ።

ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዊክሬሜሲንጌ ስልጣን ይቅርብኝ ከሥልጣን ለቃለሁ ማለታቸው አይዘነጋም።

ትላንት ተቃዋሚዎች የፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት ጥሰው ገብተው እንደነብር ይታወሳል ፤ ተቃዋሚዎቹ በደረሱበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ፕሬዚዳንቱ በቅጥር ግቢው ውስጥ አልነበሩም።

ተቃዋሚዎቹ በቤተመንግስቱ ውስጥ ሲዋኙ ፣ ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ የፕሬዜዳንቱ መኖሪያ ቤት አልጋ ላይ ሲተኙ ፣ መሳቢያዎች እየከፋፈቱ ሲበረብሩ ነው የዋሉት።

የፕሬዜዳንቱ ስልጣን ለቃለሁ ውሳኔ በተመለከተ የሀገሪቱ ፓርላማ አፈ-ጉባዔ " ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት በሰላማዊ መንገድ የሥልጣን ርክክብ እንዲኖር ነው " ብለዋል። ሕዝቡም “ሕግ እንዲያከብር” ጠይቀዋል።

ሲሪላንካ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እየተናጠች ሲሆን በአገሪቱ በ70 ዓመታት ውስጥ ያልታየ በተባለው አስከፊ የኢኮኖሚ ቀውስ ምግብ፣ ነዳጅ እና መድኃኒት ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየታገለች ነው።

የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ተመናምኖ ያለቀ ሲሆን፣ ለግል ተሽከርካሪዎች ቤንዚንና ናፍጣ ሽያጭ ላይ እገዳ ተጥሏል። ከዚህም ጋር ተያይዞም ነዳጅ ለማግኘት ለቀናት በርካቶች ረጃጅም ሰልፎች ላይ ታይተዋል።

የትላንቱ ያልተለመደ ክስተት በሲሪላንካ ውስጥ ለወራት የተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ማክተሚያ ይመስላል ሲል ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

Photo Credit : Dr. Gorge

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ?

በፎቶው የምትመለከቱት ቢንያም ኢሳያስ ይባላል።

ተማሪ ቢኒያም ከልጅነቱ አንስቶ በትምህርቱ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ የልጅነት ህልሙ የሆነውን ህክምና ትምህርት ለመከታተል ወደ ጥቁር አንበሳ ሊገባ ችሏል።

4 ዓመት ድረስ ፈታኝ ነው የሚባለውን የህክምና ትምህርት (ሜዲስን) በከፍተኛ ውጤት ከተማረ በኃላ ግን ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በኃላ መማር አትችልም ሲል ገልጾለታል።

ለምን ? ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ ከህፃንነቱ ጀምሮ የአካል ጉዳተኛ ነው፤ በዚህም ሳቢያ ነው 5ኛ ዓመት ከደረሰ በኃላ ዩኒቨርሲቲው አካል ጉዳተኛ ስለሆንክ ለዚህ ትምህርት አትመጥንም ብሎ እንዲወጣ ያደረገው።

ይህ ችግር እንዲስተካከል ብዙ ቢለፋም ምንም መፍትሄ አልተገኘም።

በዚህ ሁኔታ ትምህርቱን መከታተል የማይችል ከሆነ ለምን በቅድሚያ ትምህርቱን እንዲጀምር ተደረገ ለሚለው ? ዩኒቨርሲቲው መጀመሪያውኑ መመዘን እንደነበረበት ነገር ግን እንዳልመዘነ ገልጿል።

ተማሪ ቢንያም ግን ቀድሞውንም አካል ጉዳተኛ የሚል ፎርም መሙላቱን አረጋግጧል።

ካሪኩለሙ ላይ ተማሪ ወደ ህክምና ክፍሉ ሲገባ የአካል፣ የአእምሮ ችሎታው ሙሉ መሆኑን መረጋገጥ አለበት የሚል ሲሆን ዩኒቨርሲቲው መጀመሪያ ይሄን ባላደረገበት ሁኔታ አምስት አመት ከደረሰ በኃላ ከትምህርቱ ውጣ ማለቱ በተማሪው እንዲሁም በቤተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል። ቅሬታ ብቻ ሳይሆን መላ ቤተሰቡን፣ በፊት ያስተማሩትን መምራንን አሳዝኗል።

በሌላ በኩል በህክምና ትምህርት ሁለት እጅ የማይጠይቁ ስራዎች ላይ መግባት ችላለሁ ብሎ ተማሪ ቢንያም ቢጠይቅም (ሳይካትሪ፣ ፐብሊክ ሄልዝ ሌሎችም) ዩኒቨርሲቲው ግን ለመቀበል ፍቃደኛ አልሆነም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Binyam-Esayas-07-10

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በተገኘ መረጀ በሐምሌ የመጀመርያዎቹ ሳምንታት ከፍተኛ የሆነ ነጎድጓዳማና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ይኖራል።

በተከታታይ ቀናት የሚኖረው የዝናብ መጠን ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊፈጥር ስለሚችል አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡

በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኘውን ውኃ በጥንቃቄ መያዝም እንደሚገባ ተገልጿል።

የሚፈጠረው ዝናብ ከመጠን በላይ ማሣ ላይ ውኃ እንዲተኛ ስለሚያደርግ በእርሻ እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ እንቅስቃሴ እንዳያስከትል የማጠንፈፊያ ቦዮችና የጎርፍ መከላከያ እርከኖች በመሥራት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ከመደበኛ በላይና መደበኛ ዝናብ የሚጠበቅባቸው ቦታዎች ፦
- አፋር፣
- አማራ፣
- ትግራይ፣
- ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች መሆናቸውን ኢንስቲትዩቱ አሳውቋል።

በተለይም ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ ማለትም ተዳፋትና ገደላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የክረምቱ የዝናብ ሁኔታ በሐምሌና ነሐሴ ወራት እንደሚጠናከር የሚጠበቅ ሲሆን መብረቅ፣ ጎርፍና የበረዶ ግግር ሊኖር ስለሚችል ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ተብሏል።

መረጃውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩትን ዋቢ አድርጎ ሪፖርተር ነው ያጋራው።

@tikvahethiopia
ባለሃብቱ ለወጣቶች ስራ ፈጠራ 10 ሚሊዮን ብር አበረከቱ !

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ ፤ #ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተሰማ።

አቶ በላይነህ ለሰከላ ወረዳ ወጣቶች ነው የስራ ዕድል መፍጠሪያ የሚውል 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉት፤ ድጋፉንም ሰከላ ወረዳ ግሽ ዓባይ ላይ ተገኝተው ለወጣቶቹ አስረክበዋል።

ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ ለወጣቶቹ የህይወት ተሞክሯቸውን እና ምክር አካፍለዋል።

አቶ በላይናህ ክንዴ በርክክብ መድረኩ ላይ ፦

" መንግስት ብቻ ሳይሆን ባለሀብቱ #ለወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ትልቅ ሀላፊነት አለበት።

ወጣቶቻችን የስራ ዕድል ካልተፈጠረላቸው እና ሀብት ማፍራት ካልቻሉ የባለሀብቱ ዕድገትም ይገታል። ስለሆነም ለወጣቶቻችን የስራ ዕድል በመፍጠር ተያይዘን ማደግና ሀገር መለወጥ ይገባናል።

ለእኛ ሀብታችን ወጣቶቻችን ናቸው ፤ ወጣቶች በገቢ እራሳቸውን ችለው ለቤተሰብና ለሀገር እንዲተርፉ እንደ ዜጋ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል።

ወጣቶችም የትኛውንም ስራ ሳይንቁ መስራት አለባቸው። እኔ ከዝቅተኛ ስራ እና ከትንሽ ገንዘብ ተነስቼ ነው እራሴን እየለወጥኩ የመጣሁት።

ይህ በድጋፍ የተሰጠ 10 ሚሊዮን ብር በተዘዋዋሪ ብድር መልክ ነው።

ወጣቶች አሁን የወሰዳችሁትን ገንዘብ ቁምነገር ላይ በማዋል አቅም እንድትፈጥሩ እና ብድሩን በመመለስ ለሌሎች ወንድሞቻችሁ የስራ ዕድል መፍጠሪያ እንዲሆን መስራት አለባችሁ " ሲሉ ተናግረዋል። (APP)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" እንወጣም " - ተቃዋሚዎች

የስሪላንካ ጉዳይ ዓለምን ማነጋገሩ ቀጥሏል።

የስሪላንካ ፕሬዜዳንት ከስልጣን ወርዳለሁ ቢሉም ተቃዋሚዎች ከመኖሪያ ቤታቸው ለቀን አንወጣም ብለዋል።

የስሪላንካ ፕሬዜዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤትን የተቆጣጠሩት ተቃዋሚዎች ዛሬም ፕሬዝዳንታዊ መኖሪያውን እንደማይለቁ ገልፀዋል።

ተቃዋሚዎቹ የፕሬዜዳንቱን መኖሪያን ከተቆጣጠሩ በኃላና ፕሬዝዳንቱ በባህር ኃይል ታግዘው ከሸሹ በኃላ ከስልጣን እወርዳለሁ ቢሉም ተቃዋሚዎች ግን እስካሁን አልተቀበሉትም።

የተማሪዎች ንቅናቄ መሪ የሆነው ላሂሩ ዋራሴካራ ለጋዜጣኞች በሰጠው መግለጫ " ትግላችን ግና አላበቃም እሱ እስካልተወገደ ድረስ ትግላችንን እናቆምም " ሲል ተደምጧል።

ተቃዋሚዎቹ በፕሬዜዳንቱ አቅም ማነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ውድቀት መከተሉን እና ሙስና መንሰራፋቱን ይገልፃሉ ፤ በሀገሪቱ ለተፈጠረው የመድሃኒት ፣ የነዳጅ፣ የምግብ እጥረት እና ለድሃው ህዝብ ኑሮ መመሰቃቀልም ፕሬዜዳንቱን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

በሌላ በኩል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን " የሩሲያ ወረራ " ሲሪላንካ ውስጥ ለተፈጠረው ቀውስ አስተዋጽኦ ሳይኖረው አይቀርም ብለዋል። ብሊንከን " የሩሲያ ወረራ ያስከተለው ችግር በየቦታው እየታየ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

መረጃው፦ ከአሶሼትድ ፕሬስ ፣ አርቲ እና ዶቼቨለ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላት ዛሬ በፎቶ ታይተዋል።

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሃሙድ ላለፉት 2 ዓመታት በኤርትራ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙትን የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላትን ጎብኝተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ጦር አባላትን ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ነው የጎበኙት ተብሏል።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከትላንት ጀምሮ በኤርትራ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

Photo Credit - Yemane G. Meskel

@tikvahethiopia
#ጋና

" የእኔን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎች ደመወዝ በ30 በመቶ ቀንሷል " - የጋና ፕሬዜዳንት

የጋናው ፕሬዝደንት ናና አዶ ዳንኩዋ አኩፎ-አዶ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ የራሳቸውን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎቻቸው ደመወዝ በ30 % እንዲቀንስ መደረጉን አስታውቀዋል።

ይህን ያስታወቁት ትላንትና የዒድ አል-አድሃ በዓል ሲከበር ባሰሙት ንግግር ነው።

የ30% ቅነሳው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን፣ የመንግስት ኤጀንሲዎችን እና መምሪያዎችን ወጪ ይነካልም ተብሏል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መንግስት እያሽቆለቆለ ያለውን ኢኮኖሚ ለመታደግ በሚያደርገው ጥረት ጋናውያን መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ተማጽነዋል።

" አሁን ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሁላችንም መስዋዕትነት መክፈል አለብን " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ መምሪያዎች እና ኤጀንሲዎች ወጪ በ30 በመቶ ቀንሷል። የእኔን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎች ደመወዝም በ30 በመቶ ቀንሷል " ብለዋል።

የነዳጅ ኩፖን ምደባ በ50 % መቀነሱን እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች መታገዳቸውን ገልፀዋል።

ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ጋናውያን እንዲታገሷቸው አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንት ናና አዶ አኩፎ አዶ እኤአ ሰኔ 1/2022 የገንዘብ ሚኒስትሩ ኬን ኦፎሪ-አታ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጋር ይፋዊ ግንኙነቶችን እንዲጀምሩ አዘው ነበር።

የIMF ድጋፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ እያጋጠሙ ያሉ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ነው ተብሏል።

Video Credit : Citi TV, Ghana

@tikvahethiopia