TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት (NCDO) በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ የወለጋ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።

ድርጅቱ ፤ የዒደ አል አድሐ በዓልን በማስመልከት በሁለት ዙር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ፤ በመጀመሪያው ዙር 19 በሬዎችን ፣ በሁለተኛ ዙር 10 በሬዎችንና 100 በጎችን በደምሩ 1.8 ሚሊዮን ብር ገደማ የሚገመት ድጋፍ አድርጓል።

ድርጅቱ ለወደፊቱም በሚችለው ሁሉ እገዛውን ለሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚያደርገውን ድጋፍ #አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

Credit : NCDO

@tikvahethiopia
👍173
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትና የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና ጅቡቲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሕክምናቸውን አጠናቀው ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር አስታውቋል።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ክሊቭላንድ ክሊኒክ ሆስፒታል አቡዳቢ (Cleveland Clinic Abu Dhabi) በቅዱስ ሲኖዶስ እና በጠቅላይ ቤተክህነት ፈቃድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕክምና ማኅበር አስፈላጊውን የዝውውር ሂደት ከባለሙያዎች ጋር በማመቻቸት ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም መጓዛቸውና ሕክምናቸውን በዚያው ሲከታተሉ ቆይተዋል።

ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ጤንነታቸው በአሁኑ ሰዓት #በመልካም ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሕክምናቸውን በማጠናቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ.ም ላይ ከማኅበሩ የሕክምና ቡድን ጋር ይመለሳሉ መባሉን ከEOTC ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።

@tikvahethiopia
👍101🙏1
" የተጭበረበራችሁ በስልክም ፤ በአካልም እየቀረባችሁ አመልክቱ " - የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በተለያዩ የኦንላይን ማጭበርበሪያ ድርጊት ገንዘባቸውን ያጡ ሰዎች በ991 ወይም 987 ላይ መረጃ መስጠት ይችላሉ አለ።

ፌዴራል ፖሊስ ይህን ያለው ለኢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጄይላን አብዲ ፤ " የማህበራዊ እና የኦንላይን ሚዲያዎችን በመጠቀም የበርካታ ሰዎችን ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ አድራሻቸውን በማጥፋት የተሰወሩ አካላት መኖራቸውን ከደረሰ ጥቆማና ከተለያዩ ምንጮች መረዳት ችለናል " ብለዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልከቶ ከተለያዩ የህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር መረጃ የማጣራት እና የምርመራ ስራ እየተሰራ ይገኛል የማጭበርበር ድርጊት የተፈፀመባቸው እና የተመለከቱ ከላይ ባሉት ስልኮች እየደወሉ ማመልከት ይችላሉ ብለዋል።

ከስልክ በተጨማሪ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ የኢንተለጀንስ ቢሮ በመቅረብ መረጃ መስጠት እንደሚችሉ ኃላፊው ለኢቢሲ ተናግረዋል።

ልክ እንደ FIAS 777 አሁን ላይ የተመሳሳይ የማጭበርበር ስራ ከሚሰራባቸው ድረገፆች መካከል hulu61፣ HDU፣ workxo፣ Crowd 1፣ vemo1 እና ሌሎችም ተጠቃሽ መሆናቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም በFIAS 777 እና መሰል ድርጅት ነን ባዮች ከ1 ሺ ብር አንስቶ ከ100 ሺህ ብር በላይ የተጭበረበሩ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይፈልግላቸው ዘንድ ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም።

(ማስታወሻ - https://t.iss.one/tikvahethiopia/71364)

@tikvahethiopia
👍103
በኮንሶ ያለው የምግብ እጥረት !

በደቡብ ክልል ውስጥ በሚገኘው ኮንሶ ዞን በተከሰተ የምግብ እጥረት ሳቢያ 13 ሕጻናት መሞታቸውን ተሰምቷል።

በኮንሶ ዞን ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የሚጥለው ዝናብ ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ እንዲሁም በተከታታይ በነበሩ ግጭቶች የተነሳ ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል።

አቶ ተስፋዬ ጫሬ የኮንሶ ዞን ዋና የመንግሥት ተጠሪ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ፤ " ከሐምሌ 01/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት በዞኑ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር 190 ሺህ 825 ይሆናል። " ብለዋል።

ከእነዚህ መካከል 122 ሺህ 735 በዝናብ እጥረት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ሲሆኑ፣ በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው እርዳታ የሚጠብቁ ደግሞ 68,087 መሆናቸውን አመልከተዋል።

በካራት ሆስፒታል ሄድ ነርስ የሆነው እና በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናት ክፍል የሚሰራው ሰምበቶ በሪሻ እንደተናገረው ወደ ሆስፒታላቸው በምግብ እጥረት ተጎድተው የሚመጡ ሕጻናት ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው።

ከዚህ ቀደም በወር እስከ 40 ሕጻናት በምግብ እጥረት ተጎድተው ይመጡ እንደነበር አስታውሶ፣ በአሁን ሰዓት ግን ይህ ቁጥር በእጥፍ አድጎ እስከ 80 ሕጻናት በምግብ እጥረት ተጎድተው እንደሚመጡ ገልጿል።

ወደ ካራት ሆስፒታል የሚመጡ አብዛኞቹ ሕጻናት ከገጠር ቀበሌዎች መሆኑን ያስታወሰው አቶ ሰምበቶ፣ በግጭት ምክንያት ከሰገን ዙሪያ የተፈናቀሉ እንደሚገኙበትም ገልጿል።

ያንብቡ : https://www.google.com/amp/s/www.bbc.co.uk/amharic/articles/cyj71e3jd0lo.amp

@tikvahethiopia
👍7
TIKVAH-ETHIOPIA
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ " መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ ባያውጅልንም በራስ ተነሳሽነት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቁር ልብስ በመልበስ በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማችሁን ሐዘን እንድትገልጹ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱ ከቀኑ 6:30 ላይ ዅላችሁም በያላችሁበት የአንድ ደቂቃ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

ሶስት ፓርቲዎች (እናት ፣ መኢአድ፣ ኢሕአፓ) ከቀናት በፊት ባወጡት መግለጫ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 4 በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖች ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሐዘን እንዲገልፁ ጥሪ አቅርበው ነበር።

ፓርቲዎቹ በግፍ ለተጨፈጨፉት ወገኖች " መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ አላወጀልንም " ያሉ ሲሆን በዚህም የተነሳ በራስ ተነሳሽነት የዛሬ ሐምሌ 4 መርሀግብር ማዘጋጀታቸውን ነበር የገለፁት።

በዛሬው ዕለትም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን #ጥቁር_ልብስ በመልበስ ሐዘናቸው መግለፃቸውን ሚያስዩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያጋሩ ነው።

ከቀኑ 6:30 ላይ ኢትዮጵያውያን በያሉበት የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንዲያደርጉም ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበው የነበረ ሲሆን ይህንን የሚያሳዩ ፎቶዎች ደርሰውን ተመልክተናል።

የፓርቲዎች አመራሮችም በፅ/ቤታቸው ሻማ በማብራት ሀዘናቸውን መግለፃቸውን ተመልክተናል።

@tikvahethiopia
👍13
ፎቶ ፦ ዛሬ መዲናችን አዲስ አበባ ከጥዋት ጀምሮ በጭጋግ ተሸፍናለች።

የዛሬው የአየር ሁኔታ ከአዲስ አበባ ለሚነሱ እና አዲስ አበባ ለሚያርፉ አውሮፕላኖችም መዘግየት ምክንያት ሆኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አበባ ላይ ባለው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራዎች መዘግየት እንዳጋጠመው ገልጿል።

አየር መንገዱ ፤ በአየር ሁኔታ ምክንያት ከአዲስ አበባ የሚነሱም ሆነ የሚያርፉ አውሮፕላኖች ለመዘግየት መገደዳቸውን ጠቅሶ መንገደኞችን ይቅርታ ጠይቋል።

ፎቶዎች ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የተሰባሰቡ

@tikvahethiopia
👍10
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ትላንት አርብ በአደባባይ በአንድ የፖለቲካ ቅስቀሳ ላይ ንግግር ሲያደርጉ በጥይት ተመተገው የተገደሉት የቀድሞ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ አስክሬናቸው ቶክዮ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ገብቷል። አስክሬናቸው ቶኪዮን መኖሪያ ቤታቸው ሲደርስ ፤ የገዢው ፓርቲያቸው አባላት LDP ጥቁር በጥቁር ለብሰው የተቀበሉ ሲሆን የአሁኑ ጠ/ሚ ፉሚዮ ኪሺዳ ከሰዓት በኃላ ወደ ሺንዞ አቤ ቤት ይመጣሉ ተብሏል። …
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " - ፖሊስ

የጃፓን ፖሊስ ባለፈው ዓርብ በደቡባዊቷ ናራ ከተማ የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ግድያ በተፈጸመበት ወቅት የፀጥታ ጥበቃ ክፍተቶች እንደነበሩ ገልጿጻ።

የናራ ፖሊስ አዛዥ ቶሞአኪ ኦኒዙካ ፤ " በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ተፈጥረዋል ያሏቸውን ክፍተቶች የት ላይ እንደሆኑ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

በሺንዞ አቤ ላይ ግድያውን በመፈጸም የተጠረጠረው የ41 ዓመቱ ቴሱያ ያማጋሚ አንድ በስም ያልተጠቀሰ ተቋም ላይ ቂም ይዞ ነበር ሲል ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

የጃፓን የመገናኛ ብዙኃን ፤ ለምርመራው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገቡት ከሆነ ተጠርጣሪው ወላጅ እናቱን የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ከከተተ አንድ የሃይማኖት ቡድን ጋር ሺንዞ አቤ ግንኙነት አላቸው ብሎ ያምናል።

ፖሊስ በተጠርጣሪውና በክስተቱ ላይ ጥልቅ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
👍10🙏2
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ዛሬ መዲናችን አዲስ አበባ ከጥዋት ጀምሮ በጭጋግ ተሸፍናለች። የዛሬው የአየር ሁኔታ ከአዲስ አበባ ለሚነሱ እና አዲስ አበባ ለሚያርፉ አውሮፕላኖችም መዘግየት ምክንያት ሆኗል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አበባ ላይ ባለው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራዎች መዘግየት እንዳጋጠመው ገልጿል። አየር መንገዱ ፤ በአየር ሁኔታ ምክንያት ከአዲስ አበባ የሚነሱም ሆነ…
#Update

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ጸባይ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን በረራ በአብዛኛው መጀመሩን አሳውቋል።

ባለፉት ጥቂት ሰአታት በአዲስ አበባ የነበረው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱንም ገልጿል።

በዚህም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉና ከኢትዮጵያ የሚነሱ በረራዎች #በአብዛኛው መጀመራቸውን አሳውቋል።

አየር መንገዱ ፤ ለደንበኞቹ ተጨማሪ መረጃዎች ማድረሱን እንደሚቀጥል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አስፍሯል።

@tikvahethiopia
👍8