TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የስም ዝርዝር ጉዳይ !

ዛሬ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ታውቀዋል።

ጥዋት በነበረው የዕጣ አወጣት ስነስርዓት ባለዕድለኞች አዲስ በተዋወቀ ሲስተም አማካኝነት ነው የተለዩት።

ከዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ በኃላ ተመዝጋቢዎች የቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለማወቅ የስም ዝርዝሩን ሲጠባበቁ ነበር ፤ ነገር ግን ይፋ አልሆነም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላቱን ጥያቄ ይዞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን ጠይቆ ምላሽ አግኝቷል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በሰጠን ቃል ፤ የባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ይበልጥ ታማኝነት እንዲኖረው ይፋ ከሆነበት ሰዓት ጀምሮ ኦዲት (Audit) እየተደረገ ነው ብሏል።

ታማኝነቱ ፣ ግልፅነቱ ሁሉም ያየው ጉዳይ ነው ሲስተሙ ምንም አይነት የእጅ ንክኪ ስለሌለው በፊት ከነበሩት የዕጣ አወጣጦች ሁሉ ልዩ ያደርገዋል ሲልም ገልጿል። የዕጣ አወጣጡንም በአካል ተገኝተው ከተመዝጋቢዎች ታዝበዋል ፤ በሰዓቱ ታትሞ በወጣው ወረቀት ላይም ፈርመዋል ሲል አክሏል።

የባለዕድለኞች የስም ዝርዝር በእራሱ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ድረገፅ እና በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ይወጣል ሲልም ኮርፖሬሽኑ አሳውቆናል።

መቼ ? ለሚለው ጥያቄም እጅግ በጣም በተቻለው ፍጥነት እየተሰራ ነው ፤ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣም እጥፍ ክፍያ ተከፍሎም ቢሆን ለማሰራት ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።

ዛሬ ካለቀ ነገ ቅዳሜ ፤ እና ከነገ በስቲያ እሁድ አልያም ሰኞ ዕለት የባለዕድለኞችን ስም ዝርዝር ይፋ እናዳርጋለን ሲል ገልጿል።

(ውድ ቤተሰቦቻችን ተከታትለን እናሳውቃለን ፤ ዛሬ ለህዝብ ከታዩት መካከል #ጥቂቱን ከላይ አያይዘናል ተጨማሪ - ይመልከቱ telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-08-2)

@tikvahethiopia