TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የስም ዝርዝር ጉዳይ !

ዛሬ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ታውቀዋል።

ጥዋት በነበረው የዕጣ አወጣት ስነስርዓት ባለዕድለኞች አዲስ በተዋወቀ ሲስተም አማካኝነት ነው የተለዩት።

ከዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ በኃላ ተመዝጋቢዎች የቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለማወቅ የስም ዝርዝሩን ሲጠባበቁ ነበር ፤ ነገር ግን ይፋ አልሆነም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባላቱን ጥያቄ ይዞ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን ጠይቆ ምላሽ አግኝቷል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በሰጠን ቃል ፤ የባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ይበልጥ ታማኝነት እንዲኖረው ይፋ ከሆነበት ሰዓት ጀምሮ ኦዲት (Audit) እየተደረገ ነው ብሏል።

ታማኝነቱ ፣ ግልፅነቱ ሁሉም ያየው ጉዳይ ነው ሲስተሙ ምንም አይነት የእጅ ንክኪ ስለሌለው በፊት ከነበሩት የዕጣ አወጣጦች ሁሉ ልዩ ያደርገዋል ሲልም ገልጿል። የዕጣ አወጣጡንም በአካል ተገኝተው ከተመዝጋቢዎች ታዝበዋል ፤ በሰዓቱ ታትሞ በወጣው ወረቀት ላይም ፈርመዋል ሲል አክሏል።

የባለዕድለኞች የስም ዝርዝር በእራሱ በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ድረገፅ እና በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ ይወጣል ሲልም ኮርፖሬሽኑ አሳውቆናል።

መቼ ? ለሚለው ጥያቄም እጅግ በጣም በተቻለው ፍጥነት እየተሰራ ነው ፤ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣም እጥፍ ክፍያ ተከፍሎም ቢሆን ለማሰራት ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል።

ዛሬ ካለቀ ነገ ቅዳሜ ፤ እና ከነገ በስቲያ እሁድ አልያም ሰኞ ዕለት የባለዕድለኞችን ስም ዝርዝር ይፋ እናዳርጋለን ሲል ገልጿል።

(ውድ ቤተሰቦቻችን ተከታትለን እናሳውቃለን ፤ ዛሬ ለህዝብ ከታዩት መካከል #ጥቂቱን ከላይ አያይዘናል ተጨማሪ - ይመልከቱ telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-08-2)

@tikvahethiopia
#አረፋ

(Tikvah 🕌 Family)

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በሀገራችን #ኢትዮጵያ እንዲሁም በተለያዩ ሀገራት ነው የተከበረ የሚገኘው።

በዚሁ አጋጣሚ የእስልምና ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለበዓሉ አደረሳችሁ ፤ አደረሰን እያልን በዓሉን ስናከብር በፀጥታ ችግር ፣ በጦርነት ፣ በሰላም እጦት የሚወዱትን የተነጠቁ ፣ በሀዘን ውስጥ ሆነው በዓሉን የተቀበሉትን ወገኖቻችን እያሰብን እንዲሆን አደራ እንላለን።

በተጨማሪ እንደሁል ጊዜው በዓሉን ካጡት ጋር ተካፍለን፣ የታመሙትን በመዘየር ፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ፣ ህዝባችንም ከሰቆቃ፣ ከችግር ያርፍ ዘንድ ፈጣሪያችንን እየተማፀንን እንድናከብረው አደራ እንላለን።

በድጋሚ በዓሉ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ እንዲሁም የአንድነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን!!

በኢትዮጵያና በተለያዩ ሀገራት የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ 👇
https://t.iss.one/+Rx7P5YHQp_G16wyX

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

" መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ ባያውጅልንም በራስ ተነሳሽነት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቁር ልብስ በመልበስ በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማችሁን ሐዘን እንድትገልጹ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱ ከቀኑ 6:30 ላይ ዅላችሁም በያላችሁበት የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንድታደርጉ፣ መገናኛ ብዙኃንም ዕለቱን በሙሉ ሐዘናችሁን ከመላው የኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚገባው እንድትገልጹ እንጠይቃለን። " - ኢሕአፓ፣ መኢአድ እና እናት

ኢሕአፓ ፣ መኢአድ እና እናት ፓርቲዎች ትላንት ያወጡት መግለጫ ሙሉ ቃል ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሽንዞ አቤ ተገደሉ። የቀድሞ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው ተገደሉ። ሺንዞ አቤ በምዕራባዊ ጃፓን በሚገኝና ናራ በተባለ ከተማ ጎዳና በአንድ ዕጩ ፖለቲከኛ ቅስቀሳ ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ ከበስተጀርባቸው በተተኮሰ ሁለት ጥይት ተመተው ነበር። በኃላ ወደ ሆስፒታል ቢገቡም ህይወታቸዉን መታደግ አልተቻለም። በቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ላይ ተኩስ ከፍቶ ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገው…
#Update

ትላንት አርብ በአደባባይ በአንድ የፖለቲካ ቅስቀሳ ላይ ንግግር ሲያደርጉ በጥይት ተመተገው የተገደሉት የቀድሞ የጃፓን ጠ/ሚ ሺንዞ አቤ አስክሬናቸው ቶክዮ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ገብቷል።

አስክሬናቸው ቶኪዮን መኖሪያ ቤታቸው ሲደርስ ፤ የገዢው ፓርቲያቸው አባላት LDP ጥቁር በጥቁር ለብሰው የተቀበሉ ሲሆን የአሁኑ ጠ/ሚ ፉሚዮ ኪሺዳ ከሰዓት በኃላ ወደ ሺንዞ አቤ ቤት ይመጣሉ ተብሏል።

ትላንት ግድያውን የፈፀመው የ41 አመት ዕድሜ ያለው ቴሱያ ያማጋሚ የተባለ ሰው ሲሆን ለፖሊስ በሰጠው ቃል ግድያውን በቤት ውስጥ በተሰራ መሳሪያ መፈፀሙን አምኗል።

ፖሊስ ለምን ግድያውን እንደፈፀመ እና ከጀርባው ሌላ አካል ይኖር እንደሆነ የማጣራት ስራ እየሰራ ሲሆን በወቅቱ ሺንዞ አቤ ላይ ከተኮሰ በኃላ የማምለጥ ሙከራ አለማድረጉን አመልክቷል።

ግድያውን የፈፀመው ግለሰብ ቤት ውስጥ በተሰራ መሳሪያ ሲሆን በኃላ ላይ ፖሊስ ቤቱን ሲበረብር ሌሎች ከእጅ የተሰሩ መሳሪያዎች እና ተቀጣጣይ ነገሮችን ማግኘት ችሏል።

ጃፓን እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የመሳሪያ ቁጥጥር ያለባት ሀገር ስትሆን በመሳሪያ ሰዎች የሚገደሉበት እድል እጅግ ጠባብ ነው።

@tikvahethiopia
#የእንቅስቃሴ_ገደብ_በአሶሳ !

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፦

" ... ከወቅታዊ ጸጥታ ጋር ተያይዞ በአሶሳ ከተማ ጊዚያዊ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

የእንቅስቃሴ ሰዓት ገደቡ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እሰከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ሲሆን ከሀምሌ 01/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ይቆያል።

በዚሁ መሰረት የእንቅስቃሴ ሰዓት ገደቡ ከተገለጸበት ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እሰከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ፦
- ሆቴሎች፣
- ግሮሰሪዎች፣
- መጠጥ ቤቶች እና ማናቸውም የንግድ ተቋማት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

የጸጥታ ስራ ከሚሰሩና የአምቡላንስ አገልግሎት ከሚሰጡ ውጭ ማንኛውም ተሸከርካሪ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ አይፈቀድለትም።

እግረኞች እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ ይችላሉ። እንደ ህመምና ድንገተኛ ማህበራዊ ችግር ካጋጠመ በአቅራቢያው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ጋር ተገናኝቶ በማስፈቀድ መንቀሳቀስ ይቻላል።

ህብረተሰቡ ይህን የሰዓት እላፊ ገደብ አውቆ በጊዜ ወደ ቤት በመግባት ከጸጥታ ሀይሉ ጎን በመቆም እና በእንዲህ አይነት ጊዜ የሰላሙ ባለቤት ህዝቡ በመሆኑ በሚሰሙ ወሬዎችና አሉባልታዎች ሳይረበሽ ማንኛውም አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥም ለጸጥታ ሀይሉ በመጠቆም ተባባሪ ሊሆን ይገባል። "

(የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ)

@tikvahethiopia
ዛሬ ዓለም እያነጋገረ ያለው የሲሪላንካ ጉዳይ ምንድነው ?

• የሲሪላንክ ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ ተወስደዋል።

• ተቃዋሚዎች የፕሬዜዳንቱ መኖሪያ ቤት ጥሰው ገብተው ሲዋኙ፣ ያሻቸውን ሲበሉ፣ ሲጠጡ ታይተዋል።

ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በሲሪላንካ ዋና ከተማ ኮሎምቦ የሚገኘውን የፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳ መኖሪያ ቤት ጥሰው ገብተዋል።

ገብተውም በፕሬዜዳንቱ የመዋኛ ገንዳ ሲዋኙ፣ በመኖሪያ ቤቱ በመግባትም ሲበሉ ፣ ሲጠጡ ፣ አልጋቸው ላይ ሲተኙ፣ መሳቢያዎቸውን እየከፈቱ እቃዎቻቸውን ሲበታትኑ ውለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ለጊዜው ደኅንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ መወሰዳቸውንና ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን አንድ ከፍተኛ የጦር ሹም ለኤኤፍፒ ገልጸዋል።

ፖሊስ፣ ወታደር ሀገሪቱ አለኝ የምትለው የፀጥታ ኃይል የዛሬውን ህዝባዊ ተቃውሞ መቆጣጠርም ሆነ መቋቋም አልቻሉም።

ለወራት በዘለቀውና የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር በአግባቡ ባለመቆጣጠር በተነሳ ነው ፕሬዚዳንቱ ህዝባዊ ተቃውሞ የገጠማቸው።

ከዚህ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክሬሜሲንጌ ስልጣኔ ይቅርብኝ እውርዳለሁ ማለታቸውን ፅ/ቤታቸው አሳውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉንም ያሳተፈ መንግሥት እንዲመሰረት ለማድረግ ስልጣን ለመልቀቅ ፍቃደኛ እንደሆኑ ነው የገለፁት።

ሲሪላንካ በአሁኑ ወቅት ላይ ከፍተኛ የሆነ ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ውስጥ ናት። ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት ያጋጠማት ሲሆን፤ መድኃኒት፣ ነዳጅ እና ምግብ ወደ አገር ውስጥ ማስገባት እንደተሳናት ቢቢሲ ፅፏል።

መረጃው ከሲሪላንካ ጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ ከቢቢሲ፣ ኤኤፍፒ የተሰባሰበ ነው።

Video Credit : Anoyme Citoyen, SLTweet, Jamila Husain

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተጨንቀናል ያሉበትን አሳውቁን " ቤተሰቦች ከቀናት በፊት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከቤቱ የተወሰደው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እስካሁን ያለበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ገለፁ። ቤተሰቦቹ ዛሬ በላኩልን መልዕክት ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ/ም 7 ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከቤቱ ከወሰዱት በኃላ እስካሁን ድረስ ያለበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። " ፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ብንፈልገውም ልናገኘው…
#Update

ጋዜጠኛ ያየሰድ ሽመልስ ከ11 ቀን በኃላ ወደ ቤቱ መግባቱን ለማወቅ ተችሏል።

ጋዜጠኛው በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ፤ " ቤቴን ሰብረው ገብተው፣አፍነው፣ ከአንገቴ በላይ ሸፍነው የወሰዱኝ ሰዎች ከ11 ቀናት በኋላ እንዳወሳሰዳቸው ሸፍነው አምጥተው በካራ ጫካ ጥለውኝ ሄደዋል " ሲል አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ያየሰው ላለፉት ቀናት የት እንደነበረ በየት በኩል እንደተወሰደ በየት በኩል እንዳመጡት እንደማያውቅ ገልጿል።

"የፈለጉትን ማድረግ ሚችሉ ሰዎች በእግዚአብሔር አዳኝነትና በእነርሱ መሀሪነት በሕይወት ተመልሻለሁ " ያለው ጋዜጠኛው ከአካሉ የጎደለ ሆነ የተጎዳ እንዳልደረሰበት ገልጿል።

የጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ቤተሰቦች ፤ ከቀናት በፊት ያለበትን ማወቅ እንዳልቻሉ እና ከፍተኛ ጭንቀት ላይ መውደቃቸውን ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የስም ዝርዝር ጉዳይ ! ዛሬ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ታውቀዋል። ጥዋት በነበረው የዕጣ አወጣት ስነስርዓት ባለዕድለኞች አዲስ በተዋወቀ ሲስተም አማካኝነት ነው የተለዩት። ከዕጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ በኃላ ተመዝጋቢዎች የቤት ዕጣ ደርሷቸው እንደሆነ እና እንዳልሆነ ለማወቅ የስም ዝርዝሩን ሲጠባበቁ ነበር ፤ ነገር ግን ይፋ አልሆነም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ…
" ምን አዲስ ነገር አለ ? "

ትላንት ይፋ ከሆነው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ የቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ይፋ እንዳልተደረገ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ትላንት የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በሰጠው መረጃ ዛሬ ቅዳሜ ወይም ነገ እሁድ አልያም ሰኞ ይፋ እንደሚደረግ ገልጾ ነበር።

ኮርፖሬሽኑ ዝርዝሩ ይፋ የሚያደርገው በራሱ ድረገፅ እንዲሁም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ አሳትሞ እንደሚያሰራጭ እወቁልኝ እንዳለ አይዘነጋም። በጋዜጣው ታትሞ እንዲወጣም በእጥፍ ክፍያም ቢሆን ለማሰራት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቆን ነበር።

ዛሬ በርካታ የቤተሰባችን አባላት " ምን አዲስ ነገር አለ ? " ስትሉ በርካታ ጥያቄዎች እየላካችሁ ነው እስካሁን ይፋ የተደረገ ነገር የለም ፤ ኮርፖሬሽኑም የቤት ባለዕድለኞችን ስም ዝርዝር ይፋ አላደረገም።

ውድ ቤተሰቦቻችን በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች በብዛት ስላሉ ጥንቃቄ አድርጉ ፤ አዲስ ነገር ካለ ወዲያው ወደስልካችሁ የምንልክላችሁ ይሆናል ፤ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽንን አድራሻም እናሳውቃችኃለን።

ትላንትና ከቤት ባለዕድለኞች ስም ዝርዝር ጋር በተያያዘ የላክንላችሁ መረጃም በዚህ አለ : https://t.iss.one/tikvahethiopia/71786?single

@tikvahethiopia