TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል።

በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ያወጡት እናት ፓርቲ ፣ መኢአድ እና ኢሕአፓ ሲሆኑ ፓርቲዎቹ " ሀገር በህግ እና በስርዓት እንጂ በአፈና አትመራም " ሲሉ ነው ወግለጫ ያወጡት።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው የኑሮ ውድነት፣ በአዲስ አበባ እየተሰራ ነው ስላሉት ደባ ፣ የመሬት ማዳበሪያ ጉዳይ፣ የሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል ጉዳይ፣ የፋኖን ጉዳይ፣ መንግስት እየወሰድኩ ነው ስላለው የህግ ማስከበር እርምጃ እና ሌሎች ጉዳዮችን በስፋት አንስተዋል።

ፓርቲዎቹ በሕግ ማስከበር ላይ የማያወላዳ አቋም እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን በአፈናና በግድያ ሕግ ማስከበር እንደማይቻል አጠንክረን እናሳስባለን ብለዋል።

" ማፈን መግደልና የማኅበረሰብን ቅስም የመስበር አካሄድ በአፋጣኝ እንዲቆም " ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም ፤ በሕግ ማስከበር ሰበብ የታፈኑ ንጹሓን፣ ጋዜጠኞች፣ ማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የፋኖ አባላትና ቤተሰቦቻቸው፣ ምሑራን፣ የጸጥታ ተቋማት ተመላሾችና አባላት፣ የፓርቲ አመራርና አባላት እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

መንግስት ጠረጥሬያቸዋለሁ ብሎ ካሰበም ተገቢውን የሕግ ሂደት በመከተል ለፍርድ ቤት ከማቅረብ ጀምሮ መሰል ሰብዓዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ሶስቱ ፓርቲዎች " ፋኖ " በጭንቅ ጊዜ ሀገር " ድረስልኝ " ብላ የጠራችው ባለውለታ እንጂ ለሹመትና ለሽልማት የመጣ ባለመሆኑ መንግስት አጉል ሥጋቱን አስወግዶ የያዘውን አካሄድ ይፈትሽ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

በሌላ በኩል መንግስት ያለው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ሚሊዮኖችን ለጎዳና እና ለከፋ ረሃብ ከመዳረጉ በፊት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ያለውን የገበያ ምስቅልቅል እንዲያርምና እንዲያረጋጋ ጠይቀዋል።

(ሙሉ መግለጫቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

" መንግስት በቅጡ ሐዘናችንን እንድንወጣ ባያውጅልንም በራስ ተነሳሽነት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በመጪው ሰኞ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ጥቁር ልብስ በመልበስ በቅርቡ በወለጋ፣ ቤኒሻንጉል እና ጋምቤላ ለተጨፈጨፉ ወገኖቻችን የተሰማችሁን ሐዘን እንድትገልጹ ጥሪያችንን እያስተላለፍን በዕለቱ ከቀኑ 6:30 ላይ ዅላችሁም በያላችሁበት የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት እንድታደርጉ፣ መገናኛ ብዙኃንም ዕለቱን በሙሉ ሐዘናችሁን ከመላው የኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚገባው እንድትገልጹ እንጠይቃለን። " - ኢሕአፓ፣ መኢአድ እና እናት

ኢሕአፓ ፣ መኢአድ እና እናት ፓርቲዎች ትላንት ያወጡት መግለጫ ሙሉ ቃል ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#እናት #መኢአድ #ኢሕአፓ

ባለፈው ሳምንት ህዳር 27 ቀን 2015 እናት ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቢዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የትብብር ሰነድ ፈረመዋል።

ስምምነቱ ዋነኛው ተግባር ምንድነው ? ፋይዳውስ ? ስለ ስምምነቱስ በጋራ ምን አሉ ?

" የትብብር ስምምነቱ ፓርቲዎቻችን በሚከተሉት አንኳር ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራና በትብብር እንዲሠሩ ማዕቀፋዊና ሞራላዊ ግዴታ ይጥልባቸዋል፡፡

በሀገራዊ መግባባት፣ በምርጫ፣ በሰላም ማስፈን እና መሰል ጉዳዮች  ላይ የጋራ አቋሞችን በማራመድ #በሰላማዊ_መንገድ በትብብር #እንታገላለን፡፡

በተለይ በየዕለቱ ለሚሞተው እና በድርሱልኝ ሲቃ ለሚቃትተው ወገናችን ድምጽ በመሆን ከገባበት ችግር እንዲላቀቅ መሥራት ከግንባር ቀደም ተግባሮቻችን ዋናው ነው፡፡ "

@tikvahethiopia
#እናት #ኢሕአፓ #መኢአድ

እናት ፓርቲ፣ ኢሕአፓ እና መኢአድ ዛሬ በሰጡት የጋራ መግለጫ መንግሥት በአማራ ክልል ህገወጥ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን በመግለፅ እንቅስቃሴውን እንዲያቆም ጠይቀዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ በሕወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል የተከናወነው ከባድ የእርስበርስ ጦርነት አገርንና ህዝብን ከፍተኛ ጉዳት ላይ መጣሉ አስታውሰዋል።

" ጦርነቱ የትግራይ ፣ የአማራ፣ የአፋር ህዝብን የበለጠ  ጎድቶታል " ያሉት ፓርቲዎቹ " ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችን  የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፤ በመቶ ሺ የሚቆጠሩት የአካል ጉዳተኛ ተደርገዋል፡፤ ዜጎች በገዛ ሐገራቸው ተፈናቃይና ስደተኛ ሆነዋል፤ የመሠረተ-ልማት አውታሮችና ተቋማት ወድመዋል " ብለዋል።

ህዝቡ ገና ከጦርነቱ ቁስል አላገገመም ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን መንግሥት በአማራ ህዝብ ላይ ጥቃት መክፈቱን የገለፁት ፓርቲዎቹ " ይህ አይነቱ አካሄድ አገር አፍራሽ በመሆኑ ከወዲሁ ጊዜው ሳይሄድ መንግስት እጁን ሊሰበስብ ይገባል " ብለዋል።

አሁን ላይ ነገሮች በተወሳሰቡበት ሁኔታ የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሚያባብስ መልኩ ወደ አማራ ክልል ሠራዊት አዝምቶ ' ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶችን መቆጣጠርና ትጥቅ ማስፈታት ' በሚል ሽፋን በየቦታው በከባድ መሣሪያ ጭምር በዜጎች ላይ ተኩስ ከፍቷል ሲሉ ሶስቱ ፓርቲዎች በመግለጫቸው ላይ ገልጸዋል።

" የተረጋጋና አስተማማኝ ሁኔታዎች ሳይፈጠሩ፣ ተቻኩሎ፣ በኃይል ትጥቅ ለማስፈታት መሞከር ሌላ ጦርነት ከመቀስቀስ የተለየ ውጤት የለውም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ሠላም የተነፈጉና እየተሳደዱ ያሉ ዜጎችን፣ በቅድሚያ ትጥቅ ማስወረድ ለምን አስፈለገ ? " ሲሉ የጠየቁት እነዚህ ሶሶት ፓርቲዎች " ኢትዮጵያ ከተዘፈቀችበት #የጎሰኝነት አረንቋ ሳትወጣ፣ በዘውግ በተደራጁ ሃይሎች በሚመራ መንግሥት የሚወሰዱ ማናቸውም እርምጃዎች ወደ ሌላ ችግር የሚያስገቡ ናቸውና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል " ብለዋል።

ፓርቲዎቹ ፤ " መንግስት በአማራ ክልል ዉስጥ የጀመረውን ህገ-ወጥ ጥቃት በአስቸኳይ አቁሞ ውይይትን መሰረት ባደረጉ አካሄዶች ብቻ ችግሮችን እንዲፈታ አጥብቀን እናሳስባለን " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

(የፓርቲዎቹ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia