TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለትውስታ ከአምናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቲክቫህ ቤተሰቦች ጉዞ...

ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ፤ በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩና በማህበራዊ ሚዲያ(ቴሌግራም) ብቻ የተሰባሰቡት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች...

በልዩነቶቻቸው ተከባብረው፤ በሰውነታቸው ተዋደው፤ ከምንም ነገር በላይ ሰብዓዊነታቸውን አስቀድመው፤ ጥላቻን፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ሰዎችን በማንነታቸው ማሸማቀቅን፣ መግፋትን፣ ሰዎችን በሰውነታቸው አለማክበርን #ተፀይፈው "ነጩን የሰላም ምልክት፣ባንዲራ ተሸክመው ለሀገራች ህዝቦች ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር።

ለሀገራቸው ሰላም እና ፍቅር ቀና አስበው፤ ያለ አንዳቸው የግለሰብም ሆነ የድርጅት ድጋፍ፣ የትምህርት ጊዜያቸውን ሰውተው፤ ረጃጅም ጉዞዎችን እየተንገላቱ ተጉዘው፤ ከቤተሰባቸው ከሚላክላቸው ገንዘብ ቀንሰው ለጉዞ አውለው፣ ከራሳቸው ኪስ አውጥተው ተመገበው፣ የሚስማማቸውን ምግብ ካገኙ በልተው ከሌለም ፆም አድረው፤ ለፍቅር እና ለሰላም ሲሉ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። እንደ አንድ #ዜጋ ከራሳቸው የሚጠበቀውን በዚህ እድሜያቸው አድርገዋል። የህሊና ተወቃሽ ከመሆንም ድነዋል። ሁሌም ለሰው ልጅ ባላቸው ቀና አመለካከት ስናከብራቸው እና ስናወድሳቸው እንኖራለን።

የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
.
.
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"

#Jimma #Wollo #Haramaya #DebreBrihan #Mekelle #Woldia #ArbaMinch #Hawassa #WolitaSodo #Wachamo #Wolkite

የቲክቫህ ቤተሰቦች ትውስታ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Hawassa #AddisAbeba #Wolkite

በሞጣ ከተማ የተፈፀመውን የመስጂዶችና የንብረት ቃጠሎ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። በጅማ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ በጅማ ከተማ ስታዲየም ተገኝቶ ድርጊቱን አውግዟል። በሃዋሳ ከተማ በመስጂደ-ራህማ ፣ በወልቂጤ ፣ በአሰላ ፣ በአዲስ አበባ ኑር መስጂድ፣ በኢሊባቡር እና ሌሎች ከተሞች ህዝበ መስሊሙ "ድምፃችን ይሰማ" በሚል የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል።

በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ ህዝቡ መንግስት አጥፊዎችን በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርብ፤ የንብረትም ሆነ ሌላ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች እና ድርጅቶች ተገቢው ካሳ እንዲሰጣቸውና በክልሉ መንግሥት ይቅርታ እንዲጠየቁ፣ የተቃጠሉ መስጂዶችን በአፋጣኝ በማስገንባት የዘወተር አገልግሎታቸውን እንዲሰጡ እንዲደረግ ተጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GurageZone በደቡብ ክልል ያሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለሁለት ተከፍለው በሁለት አዲስ ክልሎች ለመደራጀት በየም/ቤቶቻቸው ወስነው ውሳኔውን ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ካቀረቡ ቀናት ተቆጥሯል። በጋራ በአዲስ ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ውሳኔ አሳልፈው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጥያቄውን ካቀረቡት መካከል ግን የጉራጌ ዞን እንደሌለበት ይታወቃል። ዞኑ ከአጎራባቾቹ ስልጤ ፣ ከምባታ ጠምባሮ ፣…
#Wolkite : የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልቂጤ ከተማ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ የስራ ማቆም እና ከቤት ያለመውጣት አድማ ተመቶ መዋሉን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የንግድ እንቅስቃሴ እና ትራንስፖርትም ተቋርጦ ነው የዋለው።

ዓድማው ከጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነበር።

ምንም እንኳን በዞኑ ውስጥ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መሰል የድማ እንቅስቃሴ እንዳይካሄድ ቢያሳውቅም ዛሬ ከተማይቱ በእንቅስቃሴ ውጭ ሆና መዋሏ ተገልጿል።

አሁን ከክልልነት ጥያቄ ጋር ያለው ጥያቄ የቀጠለ ሲሆን በዚህ ሳቢያ ከሰሞኑን ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

የደቡብ ክልል ፖሊስ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን አረጋግጦ የሚታሰሩት ህዝብ ከህዝብ ለማጋጨት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት (በዞን ደረጃ በኃላፊነት ደረጃም ጭምር ያሉ) ናቸው ሲል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

@tikvahethiopia
#Wolkite

ዛሬ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ደቡብ ክልል፣ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በማቅናት ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት ስለማድረጋቸው አሳውቀዋል።

ውይይቱን ተከትሎ ፤ " የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው። " ያሉ ሲሆን " በዛሬው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል።

በየደረጃው ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንሠራለን ሲሉ ገልጸዋል።

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ወልቂጤ ከተጓዙ ባለስልጣናት መካከል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መሀመድ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይገኙበታል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የወልቂጤ ጉዞ ጋር በተገናኘ ዛሬ የማህበራዊ መገናኛዎች ትኩረት ሆኖ የነበረው በከተማው የነበረው የእንቅስቃሴ / የስራ ማቆም አድማ እንዲሁም ደግሞ የሚጠበቀውን ያህል የከተማው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ አቀባበል አለማድረጉ ነበር።

በወልቂጤ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መምጣት ተከትሎ ከተማዋ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ እንደነበር አመልክተዋል ፤ ይህ የሆነውን ህዝቡ እየጠየቀው ካለው #የክልልነት_ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንደሆነ አመልክተዋል።

ምንም እንኳን የዞን ምክር ቤት በክልል መደራጀትን ውሳኔ አሳልፎ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቢያስገባም እንዲሁም የክላስተር አደረጃጀትን እንደማይደግፍ በአብላጫ ድምፅ ቢወስንም የክልልነት ጥያቄው ግን ምላሽ እንዳላገኘ ይህ ደግሞ የህዝቡን ህገመንግስታዊ መብት የሚጥስ እንደሆነ አስረድተዋል።

" ህዝቡ መብቱን ነው የጠየቀው ፤ ለዚህ ደግሞ ኃይል ፣ እስር ፣ ማሳደድ፣ ማፈን መልስ አይሆንም መንግሥት አሁንም የያዘውን ግትር አቋሙን መልሶ ማጤን ይገባዋል " ሲሉ አስረድተዋል።

በዞኑ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ አመራሮችን ጨምሮ በርካቶች ታስረው እንደነበር አይዘነጋም። በተጨማሪ ዞኑ ላይ የአመራር ለውጦችም ተደርገዋል።

የደቡብ ክልልን ለሁለት ለመክፈል በተላለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ በወላይታ (እንዲደገም) ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዴኦ፣ ኮንሶ ዞኖች፣ ደራሼ፣ አማሮ፣ ቡርጂ፣ አሌ፣ ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች ላይ በቅርቡ ህዝበ ውሳኔ መደረጉ ይታወቃል።

አንድ ላይ እንዲቀጥለው የተባሉት ሀዲያ፣ ሀላባ፣ ከምባታ ጠምባሮ፣ ስልጤ፣ ጉራጌ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል የጉራጌ ዞን የክላስተር የአደረጃጀትን ውሳኔ ቀደም ብሎ ያልተቀበለው / በምክር ቤቱም በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ያደረገው ዞን እንደነበር አይዘነጋም።

Photo : PM OFFICE & TIKVAH WOLKITE FAMILY

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " ም/ቤት መሥራች ጉባዔ በመጪው ዓርብ ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድ ተነግሯል። ክልሉ ካቀፋቸው ከአምስቱ ዞኖች ፦ - ከከምባታ ጠምባሮ፣ - ከሀዲያ፣ - ከጉራጌ፣ - ከስልጤ - ከሀላባ ዞኖች እንዲሁም ከየም ልዩ ወረዳ የተወከሉ የክልል ም/ቤት አባላት ለስብሰባው ሐሙስ ወልቂጤ ገብተው እንዲያድሩ ጥሪ ተላልፏል። በአርቡ ጉባኤ…
#Wolkite

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የ " ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " መስራች ጉባኤ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራ ማጠናቀቁን አሳውቋል።

በሰባት የክልል ማእከላት እየተደራጀ ያለው የ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " ነሀሴ13 /2015 ዓ/ም በጉራጌ ዞን፤ በወልቂጤ ከተማ የምስረታ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው ተናግረዋል።

ከንቲባው ፤ አስተዳደሩ በዚህ ጉባኤ ምክንያት ከ2500 እስከ 3000 እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን አመልክተዋል።

ከፀጥታው ጋር በተያያዘ ሁሉም የፀጥታ መዋቅር የዞን ፣ ከተማ ፣ አበሽጌ እና ቀቤና ወረዳ በጋራ በመሆን የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ በጋራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

መረጃው የከተማው ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Wolkite

ለአመታት በውሃ ችግር የሚፈተነው የወልቂጤ ከተማ ህዝብ ዛሬም " የመንግስት ያለህ " እያለ ነዉ።

ችግሩን ለመፍታት ጥረት ላይ እየተደረገ ነዉ የሚለው የከተማው አስተዳደር በበኩሉ " ሩጫ ላይ ነኝ " ይላል።

የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የውሀ ጀሪካኖች በጫኑ ባጃጆችና ጋሪዎች ተሞልተዉ ይታያሉ። ሆቴሎች የሻወር አገልግሎትን ከረሱ የቆዩ ይመስላሉ።

በአጠቃላይ ውሀ ቅንጦት መሆኑ ግለጽ ነዉ ይህን ጉዳይ ተመልክቶ የአካባቢዉን ማህበረሰብ ስለጉዳዩ የጠየቀዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ችግሩ ለአመታት የቀጠለ መሆኑን ተረድቷል።

እንደነዋሪዎቹ ገለጻ የቧንቧ ውሀ በወር አንዴ በጣም ፈጠነ ሲባል በሁለት ሳምንት አንዴ ያውም ለሰአታት ብትመጣም አንዳንዴ የምትመጣዉ ሌሊት ሲሆን እንደምታመልጣቸዉ ይገልጻሉ።

ለሽንኩርትና ቲማቲም ከሚያወጡት እኩል ለውሀ ግዥ እንደሚያወጡ የሚገልጹት ነዋሪዎቹ መንግስት ችግራቸዉን ይቀርፍላቸዉ ዘንድ በምሬት ይጠይቃሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ጥያቄ ከሰሞኑ በነበረ የምክር ቤት ጉባኤ የቀረበለት የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በበኩሉ የውሀ ችግሮች ያለመፈታታቸዉ ምክኒያት በየዞንና ከተሞች የተጀመሩ የውሀ ጉድጓድ ፕሮጀክቶች እየተጀመሩ በመቆማቸዉ የተከሰተ መሆኑን ገልጾ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በሙሉ ሀይሉ እንደሚሰራ ገልጾ ነበር።

ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ የህዝብ ጥያቄ  የቀረበላቸዉ የወልቂጤ ከተማ የውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ቢሮ ሀላፊዉ  አቶ ዳዊት ሀይሌ በበኩላቸዉ ችግሩ መኖሩን በመግለጽ አሁን ላይ የቅሀ አጥረቱ ከተማዉን እየፈተነ መሆኑና ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች እንዳሉና ከሚጠበቁ መፍትሄዎች አንዱ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ስራው ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ዳዊት አክለዉም ፤ በቅርቡ የጉራጌ ዞን የውሀና መአድን ቢሮ ጋር በመሆን ሁኔታዎች እንደሚገመገሙና ለህዝብ አስፈላጊዉ መረጃ እንደሚሰጥ በመግለጽ ሁኔታዉን ከከተማዉ ባለስልጣናት ባለፈ የዞኑም ሆነ የበላይ አካላት በትኩረት እየሰሩበት መሆኑን ጠቁመዋል።

መረጃው ወደ ወልቂጤ ተጉዞ የነበረው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው አዘጋጅቶ የላከው።

ፎቶ ፦ Tikvah Family

@tikvahethiopia