TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የህዝብ ተወካይ አባሉ ህግ ተጥሶ እንደታሰሩበት ገለጸ።

ፓርቲው አባሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል።

ኢዜማ ፤ በ2013 ዓ.ም በተደረገው 6ኛ ሀገር አቀፉ ምርጫ #ካሸነፈባቸው የምርጫ ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው " ዛይሴ ልዩ ምርጫ ክልል " በሚገኙ አባላት ላይ በተለያየ ጊዜ ልዮ ልዮ ጥቃቶች እየደረሱ እንደሆነ አመልክቷል።

ፓርቲው በጋሞ ዞን የሚገኙ የመንግሥት አካላት ፦
- ከሕግ አግባብ ውጪ የሚፈጽሟቸውን ተግባራት እንዲያቆሙ፣
- በእነዚህ ድርጊቶች የተሣተፉ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ 
- ያለአግባብ የታሠሩ አባሎቹ እንዲፈቱና አስፈላጊው ካሣ እንዲፈጸምላቸው በተደጋጋሚ መጠየቁን ገልጾ ፤ የዞኑ አመራሮች ግን ከዚህ ተግባራቸው ለመቆጠብ ምንም አይነት ተነሣሽነት የሌላቸው መሆኑን እና ህገወጥ ድርጊቱም ተባብሶ መቀጠሉን  አረጋግጠናል ብሏል።

በዚህም የዛይሴ ልዩ ምርጫ ክልል የቀድሞው የደቡብ ብ/ብ/ክልል የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ተወካይ እና የኢዜማ አባል የሆኑት አቶ አማንያስ ጉሹና መታሰራቸውን አሳውቋል።

እስሩ " በኢፌድሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 54(6) የተጠቅሰውን ድንጋጌ የተላለፈ ነው  " ያለው ፓርቲው " ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ባልተያዙበት እና ያለመከሰስ መብታቸው በም/ቤቱ ባልተነሳበት ሁኔታ ከታህሳስ 09 ጀምሮ በጋሞ ዞን አሰተዳደር ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ይገኛሉ ፤ ፍ/ቤት ያለመቅረባቸውን አረጋግጠናል ብሏል።

ህግ ተስጥሶ የተሳሩት አባሉ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ አማንያስ ጉሹና በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።

በሌላ በኩል . . .

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ ሰብሳቢ ኢንጂነር መልካሙ ሼጌቶ በፖሊስ ተይዘው መታሠራቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

የክልሉ የፖርቲው ምክትል ሰብሳቢ አቶ አስቻለው ገ/ሚካኤል ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ ኢንጂነር መልካሙ በከፋ ዞን ፖሊስ አባላት የተያዙት በሥራ ገበታቸው ላይ እንዳሉ መሆኑና ፖሊስ #የፍርድ_ቤት ማስረጃ እንዳላቀረበ ገልጸዋል።

ፓርቲው እስሩን ህግን ያልተከተለ መሆኑ በመግለፅ ለካፋ ዞን ፍትሕ ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ የአባሉ ጉዳይ በህግ እንዲታይ ጠይቋል። የተፈፀመውን ተግባራም አውግዟል።

የከፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር መኮንን ገ/መድኅን ሰብሳቢው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰራጩት ጹሑፍ ተጠርጥረው መታሰራቸውን አረጋግጠዋል።

" መታሰሩ ትክክል ነው በሶሻል ሚዲያ የተላለፈ ነገር አለ። በዚህ በሶሻል ሚዲያ እርስ በእርሱ ህዝቡን የሚያጋጭ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ አንተ ተነስ እከሌ ተነስ  የእከሌ ዘር ብሎ ማስተላለፍ ይሄ የተከለከለ ነው። ይሄንን እያጣራን ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠረጠረ ነው።" ሲሉ ምላሻቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል።

የፓርቲው የካፋ ዞን ኢዜማ ማስተባበሪያ በበኩሉ ፤ " እኛ እንደ ፖርቲ በግለሰቡ ሶሻል ሚዲያ አካውንት ህዝብን ከህዝብ ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭ መልዕክት ፖስት ተደርጎ አላገኝንም " ብሏል።

በ24 ሰዓት ውስጥ  ቃል መስጠት እና በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው ሁለቱም ሳያደረጉ እስከ አሁን እስር ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia