TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ህገ-ወጥ ንግድ⁉️

በቦሌ አየር መንገድ ተቀጥረው የሚሰሩ አንዳንድ #ሰራተኞች ያላቸውን ነፃ ቲኬት በመጠቀም ወደ ተለያዩ ሀገራት በሚመላለሱበት ወቅት ህገወጥ ንግድ ውስጥ ገብተዋል ተባለ፡፡

ይህ የተገለጸው በዛሬው እለት ክብርት የገቢዎች ሚንስትር ወ/ሮ #አዳነች_አቤቤ በቦሌ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተው የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ከአየር መንገዱ የስራ ሃላፊዎች ጋር በነበራቸው ውይይት እንደተገለጸው አንዳንድ የአየር መንገዱ ሰራተኞች በሳምንት ከአራት እስከ አምስት ጊዜ ያህል ወደ ዱባይ፤ ታይላንድ እና ቻይና በማቅናት የተለያዩ የንግድ እቃዎችን ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት እየነገዱ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ሌሎች ህጋዊ ነጋዴዎች ለስራችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው ሲሉ ቅሬታ አሰምቷል፡፡

የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለጹት ይህ አይነቱ ድርጊት የአየር መንገዱን አለም አቀፋዊ መልካም ገጽታ የሚያጠፋ እና ህገወጥ ድርጊት ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም እንደዚህ አይነት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞችን ደረጃ በደረጃ ተጠያቂ የማድረጉ ስራ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም እነዚህን እና ሌሎች ህገወጥ ድርጊቶችን ለመቆጣጠር የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመናበብ እና በቅንጅት መስራት
እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቄዶንያ!

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚንስትር ወ/ሮ #አዳነች_አቤቤ፣ የመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የታክስ አምባሳደሮች የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የሜቄዶኒያ የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ጎበኙ።

በጉብኝቱ፤ ግምታዊ ዋጋዉ 3.5 ሚሊዮን ብር የሆነ ዘይትና ስኳር በድጋፍ መልክ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አበርክቷል፡፡ ድጋፉን ያበረከቱት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ “ሁሉም ሰው የሚጠበቅበትን ግብር በሀቀኝነትና በወቅቱ ቢከፍል አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን ህይወት የተሻለ ማድረግ ይቻል ነበር” በማለት ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የግብር አምባሳደሮችም ሌላ አገርና ወገን የሌለን በመሆኑ ግብርን በታማኝነት በመክፈል የአገራችን ኢኮኖሚ ማሳደግና ማበልፀግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

የሜቄዶኒያ ማዕከል መስራች አቶ ቢንያም በለጠ በበኩላቸው በበጎ ፍቃደኝነት ተነስታችሁ ያደረጋችሁት ጉብኝትና ያሳያችሁት ፍቅር የበለጠ ብርታት እንደሚሆናቸው ተናግረዋል፡፡

ግብርን በታማኝነትና በፍቃደኝነት በመክፈል ሁሉም ሰው ማህበራዊ ኃላፊነቱንና ግዴታዉን እንዲወጣም ሚንስትሯ በጎበኙቱ ወቅት አሳስበዋል ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

በበደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት #በሃዋሳ ከተማ የታክስ ንቅናቄ መድረክ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ #አዳነች_አቤቤ በተገኙበት በይፋ ተከፈተ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር‼️

የ14 ቢሊየን ብር የታክስ ስወራ እና ማጭበርበር የፈፀሙ 105 ግለሰቦች #በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሯ ወይዘሮ #አዳነች_አቤቤ በሰጡት መግለጫ የህዝብን ሀብት በመበዝበር እና የታክስ ማጭበርበር በመፈፀም የተለዩ 135 ድርጅቶች መለየታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በታክስ ስወራው ከተጠረጠሩት 105 ግለሰቦች መካከል 64 የሚሆኑት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡

ሚኒስትሯ በመግለጫቸው 9 ቢሊየን ብሩ 100 ቀናቱ የተለዩ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ቀሪው 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በጥርና የካቲት ወር የተለየ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ የታክስ ስወራና ማጭበርበር ላይ በዋነኝነት ተሳታፊ ሆነው የተገኙት አከፋፋዮች እና አስመጪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ማለትም 30 በመቶዎቹ ብቻ ቸርቻሪ መሆናቸውን በመግለጫቸው ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ በታክስ #ስወራና #ማጭበርበር የተለየውን 14 ቢሊየን ብር ድርጅቶቹ ለመንግስት ገቢ እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ህግ የማስከበሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት ሚኒስትሯ ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia