TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰኔ15 #ባህርዳር

"ነገ ከነገ ወዲያ መግለጫ ከሰጠነው ሰዎች ውስጥም ማንኛችንም ልንገባ [እስር ቤት] የምንችልበት እድል እንዳለ መገመት ያስፈልጋል። ምንም መተማመኛ የለም" የአማራ ክልል ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ሃላፊ ሳባ ደመቀ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BDC-07-06-2
#ሰኔ15 #ባህርዳር

በእነየማነ ታደሠ መዝገብ በተጠርጣሪዎች ላይ ቀዳሚ ምርመራ ለመስማት ለነሐሴ 9/2011 ተቀጠረ። በአማራ ክልል ተሞከረ ከተባለው ‘መፈንቅለ መንግሥት’ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ግለሰቦች መካከል የ47ቱ ጉዳይ ዛሬ በባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታይቷል። ችሎቱ ቀዳሚ ምርመራን ለመስማት ቢሰየምም ተጠርጣሪዎች ጠበቃ ለማቆም በቂ ጊዜ አልነበረንም፤ የክስ ወረቀትም አልደረሰንም በሚል ጉዳያቸው ሌላ ቀን እንዲታይ ጠይቀዋል።

ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ ለማዘጋጀት ከአርብ ጀምሮ ጊዜ ነበራቸው፤ የክስ ወረቀትም ያልደረሳቸው ምስክሮች ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ ይችላል በሚል መሆኑን ጠቅሶ ለቀዳሚ ምርመራው የመንግሥት ጠበቃም ቢሆን ቆሞላቸው ችሎቱ ይቀጥል ብሏል።

ግራ ቀኙን ያደመጠው ፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎች የክስ ወረቀት ሊደርሳቸው ይገባል፤ ጠበቃ ማቆም የሚችሉ ከሆነ የመንግሥት ጠበቃ የሚያስቀርብ አይደለም በሚል ቀዳሚ ምርመራውን ለመስማት ለሐሙስ ቀጥሯል።

Via #BBCAMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰኔ15

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ በተጠረጠሩ ግለሰቦች የምርመራ ቡድን ያቀረበውን ይግባኝ ለመወሰን ለመስከረም 21/2012 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጠ። በባህር ዳር ከተማ በተፈፀመው የባለስልጣናት #የግድያ ወንጀል መረጃ የማሰባሰብና የማጣራት ስራው ባለመጠናቀቁ ክስ መመስረት በሚያስችል ደረጃ ላይ አልደረስኩም ሲል መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-09-17