TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.6K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም…
#የአሜሪካ_አቋም!

" ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ?

- በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው።

- የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል።

- ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

- የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል።

- ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ።

- በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም።

- ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው።

- ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው።

- የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ።

- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው።

- በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።  

- ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል።

- ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች።

- የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል።

- ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል።

- ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው።

- የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል።

- ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

- ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል።

#USEmbassyAddisAbaba
#VOA
#EthiopiaInsider

@tikvahethiopia
😡722549👏207🕊130🙏56😭35🤔29😢27😱23🥰20
#USA #VISA

" የቪዛው የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር አጥሯል ፤ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትም ተከልክሏል " - ኤምባሲው

የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢትዮጵያውያን የሚሰጠው ቪዛ የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ማጠሩን አስታውቋል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስደተኛ ባልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ላይ ባደረገው የፖሊሲ ለውጥ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ኤምባሲው ገልጿል።

በአዲሱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፖሊሲ መሠረት፤ " ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለኢትዮጵውያን የሚሰጠው ቪዛ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል እና የሦስት ወር ቆይታ " እንደሚኖረው አስታውቋል።

ኤምባሲው ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም. በፊት የተሰጡ ቪዛዎች ባሉበት እንደሚቀጥሉ ገልጿል።

ለንግድ እና ለጉብኝት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን የሚያገኙት ቪዛ "B1" እና "B2" በሚለው ምድብ ውስጥ ይካተታል።

እስካሁን በነበረው አሰራር በዚህ ምድብ ውስጥ የሚገቡ ተጓዦች የሚያገኙት ቪዛ ለሁለት ዓመት የሚቆይ ነበር። በተጨማሪም የቪዛው የቆይታ ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ያስችል ነበር።

አሁን ይፋ የተደረገው ፖሊሲ የቪዛውን የቆይታ ጊዜ ወደ ሦስት ወር ከማሳጠር በተጨማሪ በአንድ ቪዛ ተደጋጋሚ ወደ አገሪቱ መግባትን ከልክሏል።

በአዲሱ ፖሊሲ ቪዛ የሚያገኙ ተጓዦች የቆይታ ጊዜ ባይጠናቀቅም እንኳ ከአሜሪካ ከወጡ በኋላ በዚያው ቪዛ ተመልሰው መግባት አይችሉም።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተለያዩ አፍሪካ አገራትን ቪዛ የቆይታ ጊዜን ወደ ሦስት ወራት ማሳጠሩን ትላንት ይፋ አድርጓል። ይህ ውሳኔ ከተላለፈባቸው ሀገራት መካከል ናይጄርያ እና ጋና ይገኙበታል።

#USEmbassyAddisAbaba #BBCAmharic

@tikvahethiopia
1.01K😭404😡109🤔61👏37😢36🙏27🕊20😱12🥰11