TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተጠርጣሪዎቹ ከእስር እየተለቀቁ ነው‼️

የድሬደዋ አስተዳደር በቅርቡ በከተማው በተካሄደው ተቃውሞ እና ሁከት ጋር በተያያዘ #ጠረጠርኳቸው በሚል በቁጥጥር ስር ካዋላቸው ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች የአብዛኞቹን ክስ በማቋረጥ በነፃ እየለቀቀ ይገኛል። ከቀናት አስር በኃላ በቂ ማስረጃ ባለመኖሩ የተለቀቁ ተጠርጣሪዎችና ቤተሰቦች እንዲሁም ወዳጆች በእምባ ተራጭተዋል፡፡ በከተማው ለቀናት የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የፀጥታ ሀይሉ በወሰደው ሰፊ እርምጃ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን አፍሶ በመያዝ ከአስራ አምስት ቀናት በላይ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው ሲመረመር ቆይቷል፡፡ ከነዚህ ተጠርጣሪዎች ሁለት መቶ አስራ ስምንት የሚሆኑትን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና ፖሊስ ውሰኔ ክሳቸው ተቋርጦ በነፃ እንዲለቀቁ ተደርጓል፡፡

ከሳምንት በፊት በሀላፊነት የተሾሙት የአስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር ኮማንደር አለሙ መርጋ ተጠርጣሪዎቹ ስለተለቀቁበት ምክንያት አስረድተዋል፡፡

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ተጠርጣሪዎችን በመልቀቅ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ከመልቀቃቸው በፊት ከተጠርጣሪዎች ፣ ከቤተሰብና በነፃ ጥብቅና ቆመው ከነበሩ የህግ ባለሞያዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ኮምሽነሩ ስለውይይቱ ዓላማ ተናግረዋል፡፡ በተለያዩ ቀናት በተካሄደው በዚህ ውይይት በከተማው የተፈጠረውን ሁከት ተከትሎ በጅምላ ተይዘው የቆዩ ተጠርጣሪዎች ከድርጊቱ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ሳይኖር ጭምር መሆኑነንና፣ በምርመራ ሂደትም ከመርማሪዎች ከብቃት ጋር የተያያዙ ችግሮች እንደነበሩ ተነስተዋል፡፡ ወጣቶቹም #በሰላማዊ መንገድ ትግላችንን እንቐጥላለል ብለዋል፡፡

ከህብረተሰቡ ለተነሱት ጉዳዮች በፖሊስ እና ዐቃቤ ህግ በኩል ተወስደው የሚታረሙ መሆኑ ተገልፇል፡፡ በሌላ በኩል ከዚሁ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ፍ/ቤት ቀርበው ግዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ከነበሩና ዛሬ ፍርድ ቤት ከሚቀርቡ ዘጠና ተጠርጣሪዎች አብዛኞቹን ክስ በማቋረጥ መልቀቃቸው ለፍ/ቤቱ ተገልፃል፡፡

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia