#update ቤንሻንጉል ክልል⬇️
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኦዳ ዳለቲ እና በጉባ አልመሃል ላይ በተፈጠሩ ግጭቶች 69 ተጠርጣሪዎችን #በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የክልሉ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ መንግስት #የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከፌደራልና ከአጎራባች ክልሎች ጋር እየሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
የከልሉ መንግስት የህግ የበላይነት ለማስከበር #ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ይገኛልም ብለዋል፡፡
ነሐሴ 26 እና 27 2010 ዓ'ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በኦዳ ቢልዲጊሉ ወረዳ ዳለቲ ቀበሌ ላይ በተፈጠረው ግጭት 48 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ የማጣራት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ግጭቱ በቤኒሻንጉልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ላይ የተከሰተ በመሆኑ የማረጋጋት ስራዉንም ሆነ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር
የማዋል ሂደቱ በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ ነዉ አቶ ማሃመድ የተናገሩት፡፡
በተመሳሳይም መስከረም 3 2011 ዓ.ም በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሃል ቀበሌ ላይ በደረሰዉ ጥቃት 21 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተካሄደባቸዉ ይገኛል፡፡
ሰኔ 17 እስከ 21 በአሶሳ ከተማ፣ በሽርቆሌ ወረዳ እና በማኦኮሞ ልዩ ወረዳ ላይ ተከስቶ በነበረዉ ግጭት በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑንም አቶ መሃመድ ገልፀዋል፡፡
#በአሶሳ ከተማ እና በሸርቆሌ ወረዳ ላይ ተከስቶ በነበረዉ ግጭት ከ 1 መቶ በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የኦፕሬሽ ስራ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር ጥረት እያደረገ ነዉ ያሉት ሃላፊዉ ከፌደራል መንግስት የተላከ ቡድን እንዳለም ተናግረዋል፡፡
©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል‼️
#በአሶሳ_ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ “ታምሚያለሁ” በሚል ወደ መኖሪያ ቤቱ እንዲሄድ በመፍቀድ በግለሰቡና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ውጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል የተጠረጠሩ ሶስት #የፖሊስ_አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአሶሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማደር አኑር ሙስጣፋ ለኢዜአ እንዳስታወቁት በከተማው የወረዳ ሁለት መደበኛ ፖሊስ አባላት የሆኑ ሶስት ግለሰቦች ማምሻውን #ትጥቃቸውን ፈትተው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
የፖሊስ አባላቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለው ግለሰብ ላቀረበው የ”ታምሚያለሁ” ጥያቄ ጉዳዩ ከሚመለከተው የወረዳው አካል ትዕዛዝ ሳያገኙ በራሳቸው ፈቃድ ግለሰቡን ወደ መኖሪያ ቤቱ በመውሰዳቸው ነው፡፡
የጸጥታ ሃይሎቹ ተጠርጣሪውን ወደ ህክምና ተቋም መውሰድ ሲገባቸው ወደ መኖሪያ ቤቱ መውሰድ እንዳልነበረባቸው ኮማንደር አኑር አስረድተዋል፡፡
ግለሰቡም ወደ መኖሪያ ቤቱ በተወሰደበት ወቅት ክላሽንኮብ በማውጣት በጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡
ይህንኑ ተከትሎ በከተማው በተወሰኑ ቦታዎች አለመረጋጋት ታይቶ እንደነበረ ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ግን የከተማው ሁኔታ በጸጥታ ሃይሎች እና በህብረተሰቡ ትብብር ወደ ነበረበት እንደተመለሰ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፦ ena

ቤጉህዴፓ‼️
የቤንሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጀመረ።
የፓርቲው ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ ለኢዜአ እንደተናገሩት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ #በአሶሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። በስብሰባው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ዋነኛ አጀንዳ እንደሆነ ነው ኃላፊው የገለፁት፡፡
እያንዳንዱ የማዕከላዊ ኮሚቴ እና ስራ አስፈፃሚ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እንደሚገመገም አስታውቀዋል።
በስብሰባው የፀጥታ ችግሩን በመፍታት ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚያግዝ አቅጣጫ ይጠበቃል ብለዋል ኃላፊው።
በዝግ የሚካሄደው ይኸው ስብሰባ ለአራት ተከታታይ ቀናት ይቆያል።