በሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ተማሪዎችን ሲያስተምሩና ደመወዝ ሲበሉ የቆዩ ግለሰቦች ተፈረደባቸው።
ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማሰራት በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ 3 ግለሰቦች ያለ ብቃታቸው እና ያለ ሙያቸው ሲያስተምሩ በመገኘታቸው ክስ ተመስርቶባቸው ውሳኔ ተላለፈባቸው።
1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ፣
2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ፣
3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ የተባሉት ግለሰቦች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ውስጥ " አንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት " በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ያለ ሙያቸው እና ያለ ብቃታቸው ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ተይዘው የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።
1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ ፦ ከአርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ #በባዮሎጂ መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 10/04 /2011 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያየ የደመወዝ መጠን #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 215 ሺህ 739 ብር ተከፍሎታል።
2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ #በእንግሊዘኛ መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከ04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 800 ብር ተከፍሎታል።
3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ በሂሳብ ትምህርት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 008 ብር ደመወዝ ተከፍሎታል።
ሶስቱም ተከሳሾች ያለሙያቸውና ብቃታቸው ሲያስተምሩ በቆዩባቸው ጊዜያት በተማሪዎች ላይ በገንዘብ የማይተመን እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እና በመንግሥት ላይ ባልተገባ መልኩ በተቀበሉት ደመወዝ 455, 755 የሚገመት ብር ጉዳት አድርሰዋል።
ዓቃቤ ህግ በፈፀሙት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማዘጋጀት እና በመገልገል በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቷል።
የበሉትን ደመወዝም እንዲመልሱ በክሱ ላይ ቀርቧል።
የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ናቸው በማለት ሶስቱም ተከሾች ጥፋተኛ ብሏቸዋል።
እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ እንዲሁም ያለአግባብ የበሉትን አጠቃላይ 455,755 ብር ለመንግሥት እንዲመልሱ ውሳኔ አሳልፏል።
@tikvahethiopia