TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UnityPark

"አንድነት ፓርክ" መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቆ ለህዝብ ጉብኝት ክፍት ይሆናል። በአንድነት ፓርክ ዘጠኙም ክልሎች በአግባቡ ተወክለው በቤተ መንግስቱ እልፍኝ ተበጅቶላቸዋል። ታላቁ ቤተ መንግስት ስያሜው አንድነት ፓርክ ሆኖ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቆ ለህዝብ ጉብኝት ክፍት ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በትላንትናው ዕለት በአንድነት ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ማንኛውም ሀገር የራሱ ታሪክ ያለው መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንት ኬያንታ፥ ለወደ ፊት የተሻለ ሀገር ግንባታም ካለፉት ታሪኮች ውስጥ ጥሩ ተሞክሮዎችን መውሰድ እንደሚገባ አንስተዋል።

ኬንያ እና ኢትዮጵያ በባህል፣በኢኮኖሚ እና በተለያዩ ዘርፎች ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከርም በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያካሄደቸው ያለው ሁለንተናዊ ለውጥ የሚበረታታ መሆኑም ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጠቁመዋል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ምርቃቱን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ሁለንተናዊ ግንኙነት ያላት መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር፥ ለዚህም በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የሰላም ችግር ወቅት ኢትዮጵያ በርካታ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በመቀበል ያደረገቸውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንስተዋል። ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች መካከል ሰላም እንዲወርድ ያደረገችውን ከፍተኛ ጥረትም አድንቀዋል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ የተከናወነው የቤተ-መንግሥት ዕድሳት አስደናቂ መሆኑን በመግለፅ ለሀገሪቱ ቱሪዝም እንዲሁም የኢኮኖሚ ለውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል። የአንድነት ፓርክ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማስፋፋት እና ቱሪዝምን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውና የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በፕሮግራም ላይ በመገኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ ለኢዮጵያ መንግስትና ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያ በሱዳን ተፈጥሮ የነበረውን ቀወስ ለመፍታት የነበራት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አብደላ ሃምዶክ፥ የአንድነት ፓርክ ለሀገሪቱ ታላቅ ስጦታ መሆኑን አንስተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark|በደማቅ ሁኔታ ተመርቆ የተከፈተው የአንድነት ፓርክ በ2 ሺህ የሃገር መከላከያ እና በ2 ሺህ የፖሊስ ሰራዊት አባላትን በማስጎብኘት ስራውን በይፋ ጀምሯል፡፡

አንድነት ፓርክ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

መደበኛ የክፍያ ጉብኝት ከነገ ሰኞ ይጀምራል!

ከነገ ሰኞ ማለትም ከጥቅምት 3 2012 ጅምሮ ማንኛውም ዜጋ 200 ብር እንዲሁም በቪአይፒ (VIP) 1 ሺህ ብር በመክፈል ቤተ መንግስቱን መጎብኘት ይችላል።

የአንድነት ፓርክን ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲኖርበት በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመሁኔታዎች ካላሟሉ ፓርኩን መጎብኘት አይችሉም።

ጎብኚዎች ይዘው መምጣት የሌለባቸው ነገሮች፦

- ስለት
- ተቀጣጣይ ቁሶች
- የጦር መሳሪያዎች
- ምግብ መጠጦች እና ጣፋጭ ነገሮች
- ማስቲካ
- የመዋቢያ ቁሶች
- የግል ካሜራዎች
- ስልኮች ታብሌቶች እና ማንቸውንም የምስልና ድምጽ መቅረጫ መሳሪያዎችን
- ሲጋራ እና አደንዛዥ ዕጾች

በፓርኩ ውስጥ ማድረግ የተከለከሉ ተግባራትና ባህሪያት፦

- መጮህና መረበሽ
- ከአስጎብኚ ውጪና ከተመደቡበት የጉብኝት ቡድን ውጪ መንቀሳቀስ
- በታሪካዊ ህንጻዎቹ ላይ መደገፍ
- ቅርሶችንና እንስሳትን መነካካት
- እንስሳትን ከተፈቀደው ቦታ ውጪ መቅረብ
- እንስሳትን መመገብ
- እንስሳትን ማስቆጣት (ጠጠር መወርወር፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ ማስፈራራት፣ አላስፈላጊ ድምጽ ማውጣት)
- ከተቀመጡ የቆሻሻ ማስወገጃ እቃ ውጪ ቆሻሻ መጣል
- ሲጋራና ሌሎች አደንዛዥ እጾችን መጠቀም
- የቤት እንስሳትን ይዞ መምጣት
- መንገድ ከተበጀለት ዉጪ መራመድ እና አጥሮችን ከልክ በላይ መጠጋትም ሆነ መደገፍ
- ማንኛዉንም በፓርኩ የሚገኝ የኤሌትሮኒክስ ቁስ ያለፍቃድ መንካት

#አንድነት_ፓርክ
#UnityPark

@tsegabwolde @tikvahethiopia