TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ንግግር አድርገዋል። ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የ "እንኳን ደስ አልዎት!" መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን መሪዎቹ በንግግሮቻቸው ያነሷቸውን ጉዳዮች በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-10-04 @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ "አካታች ብሔራዊ ውይይት" እንደሚካሄድ ገለፁ።

ይህን የገለፁት በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ባሰሙት ንግግር ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ብሔራዊ ውይይቱ "ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን" የሚያካትት እና በኢትዮጵያውያን የሚመራ እንደሚሆን ጥቆማ ሰጥተዋል።

በትግራይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው እና "በክህደት እና በእብሪት የተጠነሰሰ" ያሉት ግጭት "እንደ ሀገር እጅግ ከባድ ዋጋ" ማስከፈሉንም ተናግረዋል።

" ጠላት ብረት አንስቶ እንደ ብሌናችን የምናየውን የሰሜን እዝ አጠቃ፤ የጥሞና ጊዜ እንስጥ ባልንብት ጊዜም ህጻናትን እያስታጠቀ በርካታ ዜጎቻችንን አጠቃ፤ ንብረትም አወደመ" ሲሉም ተደምጠዋል።

“እኛ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ ይዘን ስንዘምትም ሆነ ሰይፍ ይዘን ስነነሳ ጠባችን ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑት ጋር ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፤ ኢትዮጵያ የተማሏ አቅም እና አቋም ያለው የፀጥታ ሀይል ታደራጃለች” ሲሉም ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ "በመጪው ዘመን ብዝኃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችል ሐሳባችንን አስታርቀን መከበር የሚገባው ልዩነቶቻችችን አክብረን ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠንክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል" ያሉ ሲሆን "ይኸም እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን" ብለዋል።

መረጃው ከዶቼቨለ እና አል ዓይን የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ "እንኳን ደስ አለዎት! " መልዕክት አስተላለፉ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ዶ/ር አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን ተከትሎ የ "እንኳን ደስ አለዎት" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ፥ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመልካም የወዳጅነት እና እርስ በርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ…
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀጣይ 5 ዓመታት ኢትዮጵያን እንዲመሩ ከተሾሙ በኃላ የተለያዩ ሀገራት የደስታ መግለጫ እያስተላለፉ ይገኛሉ።

ኬንያ፣ ሱማሊያ ፣ ዩጋንዳ፣ ደ/ሱዳን፣ ጁቡቲ ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ አልጄሪያ መሪዎቻቸው እና ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው እዚህ ኢትዮጵያ ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የኤርትራ በፕሬዘዳንቷ ፣ የዩኤኢ መሪዎች ፣ ቬትናምም በጠቅለይ ሚኒስትሯ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን የላኩ ሲሆን ዛሬም ሩሲያ በፕሬዜዳንቷ ለ5 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ እንዲሆኑ ለተሾሙት ዶ/ር ዐቢይ "እንኳን ደስ አልዎት" መልዕክት ልካለች።

ማምሻውን ደግሞ የኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰራጩት መልዕክት ፥ " በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መንግሥት በሚፈተን ግን በማይቀለበስ የለውጥ ጉዞ ላይ ነው " ብለዋል።

መንግሥት ጊዜያዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የልማት ግቦችን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ገንቢ በሆነ መልኩ ለመሥራት ምንጊዜም ዝግጁ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

" መሰናክሎች ያስተምሩናል እንጂ አያስቆሙንም " ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ " በያዝነው የለውጥ ጎዳና ወደ ፊት ለመጓዝ ቁርጠኞች ነን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed #JoeBiden

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ጠቁመዋል።

ውይይቱ ሁለቱ አገራት በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ተሳትፎ በማድረግ ትብብራቸውን ለማጠናከር ትልቅ ጥቅም እንዳለው ሁለታችንም ተስማምተናል ብለዋል።

#DrAbiyAhmed #ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#JustinTrudeau #OlusegunObasanjo የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተነጋግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ትሩዶ ልዩ መልዕከተኛው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንዲያበቃ እና በሁሉም አካላት መካከል ውይይት እንዲፈጠር ለማበረታታት የሚያደርጉትን ጥረት በደስታ ተቀብለዋል።…
#DrAbiyAhmed #JustinTrudeau

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።

ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እንደ ካናዳ ያሉ ወዳጅ ሀገራት የሚሰጧትን ድጋፍ እንደምታደንቅ ገልፀዋል።

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ፥ ትላንት ከሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት ጋር በተያያዘ ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መዕክተኛ እና የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር መነጋገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ማህበራት ተወካዮች እና አባላትን አግኝተዋል። በበርካታ ጉዳዮችም ላይ መወያየታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ማረፋቸውን በመስማቴ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል። " ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ተለያይተው የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች አንድ እንዲሆኑ ቅዱስነታቸው ወሳኙን ሚና መጫወታቸውን አስታውሰዋል።

" ነገሮችን በአርምሞ እየተመለከቱ ሀገራችንን በጸሎት ያግዙ ነበር። " ያሉት ጠቅለይ ሚኒስትሩ " በዚህ ወቅት እርሳቸውን ማጣት ከባድ ጉዳት ነው። ለሁላችንም መጽናናትን እመኛለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AtoGelesaDilbo በኢህአዴግ የሽግግር ወቅት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የፓርላማ አባሉ አቶ ገላሳ ዲልቦ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸውን ቤተሰቦቻቸው ገልፀዋል። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አንዱ መስራች የሆኑት አቶ ገላሳ ዲልቦ ባለፈው ዓመት በነበረው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎላኦዳ ቁምቢ መልካ በሎ ወረዳዎችን በመወከል በግል ተወዳድረው…
#DrAbiyAhmed

የአቶ ገለሳ ዲልቦ ህልፈትን ተከትሎ የኢትዮጵያው ጠ/ሚ ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

" አቶ ገለሳ ከተማሪዎች ንቅናቄ ጀምሮ ለኦሮሞ ሕዝብ ነጻነት እና እኩልነት ታግለዋል ያሉት " ዶ/ር ዐቢይ ፤ " በተለይ ሶማሌ በነበራቸው የትግል ቆይታ ብዙ መከራ እና ችግር እንዳሳለፉ አጫውተውኝ ነበር " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " በቅርቡ በለውጡ አመራር በተደረገላቸው ግብዣ የሰላማዊ ትግል ጉዞ መርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በሰላማዊ መንገድ መታገል ከመጀመራቸውም ባሻገር በ2013 ምርጫ በግል ተወዳድረው የፓርላማ አባል ለመሆንም ችለዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

" በትግል ውጣ ውረድ ውስጥ የገጠማቸውን በጎ እና ክፉ ለማሄስ እና ወጣቶች ከሁለቱም እንዲማሩ ለማድረግ ይተጉ ነበር " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " አቶ ገላሳ ዝምተኛ፤ አስተዋይ፤ ምክንያታዊ እና ለሰላማዊ ንግግር እጅግ የሚያመች ሰብእና የተላበሱ ግለሰብ ነበሩ ፤ ያጣናቸው ይበልጥ በሚያስፈልጉን ጊዜ ነው። " ሲሉ ገልፀዋቸዋልም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት እየተነሳላቸው ላለው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።

በአሁን ሰዓት በፀጥታ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እና ምላሽ እየሰጡ ነው። በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በቀጥታ መከታተል ይቻላል።

ዋና ዋና ነጥቦችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

እስካሁን ድረስ ያነሷቸው ጉዳዮች እና ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡባቸው (ከፀጥታ ጉዳዮች ውጭ) በዚህ ተያይዟል : https://telegra.ph/PM-Abiy-Ahmed-06-14

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ዛሬ ከሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን ያለበትን ደረጃ አንስቷል።

በተጨማሪም የ2015 የበጀት ዓመት ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫን መቃኘቱን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ዶ/ር ዐቢይ ስብሰባውን በተመለከተ ፤" ባለፈው ዓመት የሚያበረታታ የወጪ ንግድ አፈጻጸም፣ ቀጥተኛ የውጭ ሙዓለ ነዋይ ፍሰት መጨመር ታይቷል። ባለፉት ሁለት ወራት የዋጋ ግሽበት መቀነስ፣ ከፍተኛ የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን፣ የበጎ ፈቃደኝነት ተግባራት፣ የሬሚታንስ ጭማሪ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥራ ክንውን የተመዘገቡበት እንደ ሆነ አረጋግጠናል። በዚህ ዓመት የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል በእጅጉ አስፈላጊ ነው። " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#USA

ዛሬ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ይጀመራል።

ለዚሁ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አሜሪካ ላይ ተሰባስበዋል።

ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ይኸው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች ፦
- የአየር ንብረት ቀውስ፣
- መልካም አስተዳደር፣
- የምግብ ዋስትና እና የዓለም ጤናን የሚጨምር ሲሆን፣ እንዲሁም የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል።

አሜሪካ ጉባዔው አፍሪካ ቁልፍ የጂኦፖለቲካል ተጫዋች እንደሆነች ዕውቅና በመስጠት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጻለች።

በአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ባይደን በቡድን 20 ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ቦታ እንዲያገኝ ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

በተጫማሪም የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ከአፍሪካ አገራት መካከል " ቋሚ አባል እንዲያካትት " ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ፕሬዝዳንት ባይደን ቁርጠኛ እንደሆኑ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ለአፍሪካውያን አገራት ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል (#አጎዋ) ጋር በተያያዘ ከተጠቃሚ አገራቱ ንግድ ሚኒስትሮች ጋር የሚካሄደው ጉባኤ ዛሬ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ቢቢሲ ዘግቧል።

#DrAbiyAhmed -  " አፍሪካ ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት " በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንትና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? " አጠቃላይ የሀገራችን የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታዎች በዋና ዋና አመላካቾች በምን ደረጃ  ላይ ናቸው ? በተለይ የኑሮ ውድነት እየከፋ ነው። የዋጋ ንረትን ደግሞ ማረጋጋት አልተቻለም። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለው ማህበረሰብ እና የመንግሥት ሰራተኛው መኖር አቅቶታል። መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው። ስለሆነም እንደ መንግሥት በቀጣይ አመታት…
#DrAbiyAhmed

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ለተጠየቀው ጥያቄ ምን መለሱ ?

" የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡

በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡

በኢትዮጵያም የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሸቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው፡፡

በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል፡፡

ምርታማነትን ማሻሻልም ሌላኛው ስራ ነው፡፡

በዘንድሮው ዓመት ከዓለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ አድርጓል፡፡

ይህ ሁሉ የሚከናወነው የኑሮ ውድነቱ ዜጎቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለማቃለል ነው፡፡ በዚህም የዋጋ ንረቱን ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ ተችሏል፡፡ "

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia