TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሪፖርት : Human Rights Watch !

ሂዩማን ራይትስ ዋች የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል #ጭና እና #ቆቦ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በጅምላ መግደላቸውን ይፋ አደረገ።

በሁለቱ ስፍራዎች ግድያው የተፈጸፀመው ከነሐሴ 25 - ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም. በነበሩት 10 ቀናት ውስጥ ነው።

መጀመሪያ የህወሓት ኃይሎች ነሐሴ 25/2013 ዓ.ም ጭና ወደተባለችው መንደር በመግባት ከፌደራል ሠራዊትና ከአማራ ኃይሎች ጋር ውጊያ ካካሄዱ በኋላ ቦታውን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት በነበሩ 5 ቀናት በ15 የተለያዩ ስፈራዎች 26 ሰላማዊ ሰዎችን ገድለዋል።

በተመሳሳይ በቆቦ ከተማ ጳጉሜ 04/2013 ዓ.ም በ4 የተለያዩ ስፍራዎች ላይ 23 ሰዎችን እንደገደሉ የዓይን ምስክሮች ለሂዩማን ራይትስ ዋች ገልፀዋል።

ድርጅቱ 36 ሰዎች ቃለመጠይቅ ያደረገ ሲሆን 19ኙ ጭና እና ቆቦ ውስጥ የህወሓት ኃይሎች በአጠቃላይ 49 ሰለማዊ ሰዎችን ሲገድሉ ማየታቸውንና ከሟቾቹ የ44ቱን ሰዎች ስም ገልፀዋል፤ በተጨማሪም የሟቾቹን ቁጥር ከፍ የሚያደርግ የስም ዝርዝር ማግኘቱን አመልክቷል።

የሂማን ራይትስ ዋች የቀውስና የግጭት ጉዳዮች ዳይሬክተር ላማ ፋኪህ ስለግድያዎቹ ሲናገሩ " የትግራይ ኃይሎች በጥበቃቸው ስር ያሉ ሰዎችን በመግደል ለሰው ህይወትና ለጦርነት ሕግጋት ጭካኔ የተሞላበት ግድየለሽነት አሳይተዋል" ብለዋል።

አክለው " እነዚህ በኢትዮጵያ የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ውስጥ በተካሄዱ ግጭቶች በሁሉም ወገኖች የተፈጸሙ ግድያዎችና ጭፍጨፋዎች ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ምርመራ እንደሚያስፍልግ ያመለክታሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ሙሉ ሪፖርት : www.hrw.org/news/2021/12/09/ethiopia-tigray-forces-summarily-execute-civilians

@tikvahethiopia