TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TokyoOlympics2020

የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ከመጀመሩ ከ5 ቀናት በፊት በአትሌቶች መንደር ውስጥ 2 ስፖርተኞቸ ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

ስፖርተኞቹ ለቫይረሱ ታጋላጭ የሆኑ የመጀመሪያዎቹ ተወዳዳሪዎች ሆነዋል፡፡

2ቱ ስፖርተኞች ቅዳሜ ዕለት ተመርምረው ቫይረሱ ከተገኘባቸው ባለሥልጣን ጋር በተመሳሳይ ቡድንና ስፖርት ዘርፍ የሚገኙ ናቸው ሲሉ አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

ሌሎች የቡድኑ አባላት በክፍላቸው ተለይተው እንዲቀመጡ ተደርጓል።

በመንደሩ ቫይረሱ የተገኘባቸው #የመጀመሪያዎቹ ስፖርተኞቹ ሲሆኑ ሌላ ቦታ አንድ ተጨማሪ ስፖርተኛ እሑድ ዕለት በተመሳሳይ ቫይረሱ ተገኝቶበታል፡፡

በአጠቃላይ እሁድ ዕለት ጋዜጠኞች፣ ተባባሪ አካላትን እና ሌሎች ሠራተኞችን ጨምሮ ከኦሎምፒክ ጋር የተገናኙ 10 አዳዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች አዘጋጆቹ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

በቶኪዮ የቫይረሱ ስርጭት መጠን እየጨመረ ሲሆን ለአራት ተከታታይ ቀናት ከ 1 ሺህ በላይ አዳዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡

ብዙ ጃፓናዊያን በዚህ ወቅት ይህ ውድድር መካሄዱን እንደሚቃወሙ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Somalia

የግብፁ " Banque Misr " እና የቱርኪዬ " Ziraat Katilim " ባንኮች ሶማሊያ ውስጥ እንዲሰሩ ፍቃድ ፀደቀላቸው።


ጎረቤት ሶማሊያ ለግብፅ እና ቱርኪዬ ባንኮች የስራ ፍቃድ አፅድቃለች።

የሶማሊያ ማዕከላዊ ባንክ ቦርድ ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ መስፈርት አሟልተው ለተገኙት ሁለት ዓለም አቀፍ ባንኮች በሀገሪቱ ውስጥ ቅርጫፎቻቸውን እንዲመሰርቱ እና እንዲንቀሳቀሱ ፍቃድ አፅድቋል።

ፍቃዱ ረጅም ወራት ከወሰደ ሂደት በኃላ ነው የፀደቀው።

ፍቃድ የፀደቀላቸው ባንኮች የግብፁ " Banque Misr " እና የቱርኩ " Ziraat Katilim " ሲሆኑ በሶማሊያ የፋይናንስ ሴክተር እና በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ፍቃዱን ያፀደቀው CBS ገልጿል።

ሁለቱ ባንኮች ሶማሊያ ውስጥ እንዲሰሩ ፍቃድ ያገኙ #የመጀመሪያዎቹ ዓለም አቀፍ ባንኮች ሆነው ተመዝገበዋል።

@tikvahethiopia