TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ምዕራብ ጎንደር‼️

"ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያዎች በግለሰቦች ቤት ተገኝተዋል።"

"37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡"
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ የቡድን የጦር መሣሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት #መገኘታቸውን የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር ገለጸ፡፡

የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል #አንገሶም_አርአያ ለአብመድ እንደተናገሩት መሣሪያዎቹ የተያዙት #በመተማ ዮሐንስ ከተማ በተቃጠሉ ግለሰቦች ቤት ውስጥ ነው፡፡ ከጥይቶቹ በተጨማሪ ሀሰተኛ የብር ኖቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች፣ የቅስቀሳ መሣሪያዎች (ድምጽ ማጉያ) እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል፡፡ በአካባቢው ነባርና አዳዲስ ምሽጎች መገኘታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ጥይቶቹ የቅንቡላ፣ የአርፒጂ (የላውንቸር) እና የብሬን ናቸው፤ የእጅ ቦንብም ማግኘታቸውን ነው ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም የተናገሩት፡፡ መሣሪያዎቹ ለታንክ እና ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ ሆነው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ብቻ የሚፈቀዱ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡

ክላሽ፣ ሽጉጦች፣ ስለታማ መሣሪያዎች፣ የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ የደንብ ልብሶችም በተቃጠሉ ቤቶች ውስጥ መገኘታቸንም ነው ሌተናል ኮሎኔሉ ያረጋገጡት፡፡

አሁን የተገኙት የቡድን መሣሪያዎቹ ጥይቶቹ ናቸው፡፡ ሌሎች መሣሪያዎች አሁንም በግለሰቦቹ እጅ እንዳሉ እንደሚታመን ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም ተናግረዋል ፡፡ በቀጣይ የኅብረተሰቡን ሰላም ለመጠበቅ ከክልሉ ፖሊስና ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቀናጅቶ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

ሰላም ለማደፍረስ የሚሠሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር በሚውሉበት ጊዜ መንግሥት በቶሎ ለህግ አለማቅረቡን መገምገማቸውንም ነው ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም የተናገሩት፡፡

ውሳኔዎች የዘገዩት የፍትህ ስርዓቱን ተከትሎና ማስረጃዎችን ከማሰባሰብ በኋላ የሚሰጡ በመሆናቸው መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና የህዝብ ደኅንነት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ተናግረዋል፡፡

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia