TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Alert😷

በአ/አ እና በተወሰኑ ክልሎች የኦክስጅን እጥረት አጋጠመ።

በኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 ምክንያት በ "ጽኑ የሚታመሙ" ሰዎች ቁጥር እጅግ በመጨመሩ በአዲስ አበባ እና በተወሰኑ የክልል ከተሞች ከፍተኛ የሆነ #የኦክስጅን እጥረት ማጋጠሙ ተሰማ።

አሁን ላይ 597 ከፍተኛ ክትትል እና የፅኑ ሕክምና የሚፈልጉ ወገኖች እንዳሉ የጤና ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ያዕቆብ ሰማን ገልፀዋል።

ትላንት የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 591 የነበረ ሲሆን ዛሬ 597 ደርሷል።

ዳይሬክተሩ ያዕቆብ፤ በፍጥነት የወረሽኙን የመከላከያ መንገዶች ትግበራ ወደ #አስገዳጅነት እንዲገባ ካልተደረገ እና ሁሉም በሚገባ ካልተጠነቀቀ የከፋ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia