TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Dessise

የደሴ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለመጡ ዜጎች ጊዜያዊ ማረፊያ አዘጋጅቷል።

1ኛ. ቅዳሜ ገበያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ አንድ ":- ከወልድያ እና ከጉባላፍቶ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።

2ኛ.ዳዉዶ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሁለት":- ከባላ፡ከራያ አላማጣ እና ከኮረም አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።

3ኛ. ካራጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የማረፊያ "ጣቢያ ሶስት" ከመርሳ እና ከሀብሩ ወረዳ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ።

4ኛ. አድስ ፋና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ማረፊያ "ጣቢያ አራት" ቆቦ ከተማና ከራያ ቆቦ አካባቢ የመጡ ተፈናቃዮች ማረፊያ እንዲሆን ተወስኗል።

ከተማ አስተዳደሩ በክፍለ ከተማ እና በቀበሌ ደረጃ መላ ህዝቡ፣ አመራሩ፣ በጎፍቃደኛ ወጣቶች አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ ለተፈናቃዮች እንደሚያደርጉላቸው እምነት እንዳለው ገልጿል።

ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለውን የተፈናቃይ ቁጥር በመገንዘብ ልዩ እገዛ ለማድረግ ከወዲሁ ፍቃደኝነታቸውን በመግለፅ ወደተግባር ለገቡት የከተማድ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ምስጋና ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#Dessise : ከደሴ ከተማ ውጭ ካለ ስፍራ ወደ ደሴ ከተማ በተተኮሱ የመድፍ አረሮች ምክንያት 1 ሰው ሲገደል 3 ሰዎች መቁሰላቸውን የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል አስታውቁ።

አቶ አበበ ገብረ ይህን ያሳወቁት ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ነው።

ከንቲባው ጥቃቱ ትናንት ሐሙስ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ በግምት 9:30 የተፈፀመ መሆኑን ገልፀው ፥ "የህወሓት ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች ላይ በመድፍ በፈጸሙት ጥቃት የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል" ብለዋል።

አቶ አበበ ህወሓት ትላንት 5 የመድፍ አረሮችን በከተማዋ ላይ መተኮሱን ፤ ሁለቱ መናፈሻ በሚባለው የከተማዋ አካባቢ፣ ሁለቱ ዳውዶ በሚባለው ስፋራ እንዲሁም ቀሪው አንድ ደግሞ እርሻ ሰብል ከሚባለው ቦታ ላይ መውደቁን ጠቁመዋል።

በሰዎች ላይ ሞትና የመቁሰል ጉዳት የደረሰው እርሻ ሰብል እና መናፈሻ በተባሉት ሁለት ስፍራዎች ላይ ሲሆን "በአንደኛው ቦታ 3 ንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ሲደርስ ከእነዚህ መካከል አንዱ ወዲያውኑ ህይወቱ ማለፉን" ከንቲባው ገልጸዋል።

የመድፍ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ በጦርነቱ ምክንያት ከሰሜን ወሎ ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች የተጠለሉበትና እርዳታ የሚያገኙበት ስፍራ ይገኛል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በደሴ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ስፍራዎች ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን እየተካሄደ ስላለው ውጊያ የተረጋገጠ መረጃ ማግኘት አዳጋች ሆኗል።

የደሴ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረ መስቀል በተለያዩ የወሎ ግንባሮች ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን አረጋግጠው፤ የከተማው ነዋሪ ግን መደበኛ ሕይወት መቀጠሉን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Dessise

የዓለም ምግብ ፕሮግራም /WFP/ ከትላንት ወዲያ በደሴ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ቤተሰቦችን መዝግቧል።

በቀጥታ የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት /USAID/ ን የምግብ እርዳታ በጆይንት ኢመርጀንሲ ኦፕሬሽን (JEOP) አማካኝነት ማድረስ መጀመሩንም አሳውቋል።

WFP ፤ "ስራውን ለመጨረስ እና በጣም የተቸገሩትን ጋር ለመድረስ የጋራ ዋና ስራችን ጠንካራ ጅምር ነው " ብሏል።

@tikvahethiopia
#Amhara , #Dessise 📍

ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) የደሴ አካል ተሃድሶ ማዕከልን ስራ ለማስጀመር የሚያግዙ መሰረታዊ ቁሳቁሶች እና ማሽነሪ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማዕከሉ ያሉበትን ክፍተቶች ለመሙላት እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚሰጠውን ድጋፍ እንዲቀጥል ለማገዝ ከግጭቱ በኋላ ማዕከሉ የሚገኝበትን ሁኔታ ላይ ዳሰሳ አድርጓል፡፡

#ICRC

@tikvahethiopia
#Dessise #Kombolcha

በዛሬው ዕለት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የ #ደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ሲሾሙ አቶ መሀመድ አሚን ደግሞ የ #ኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

የደሴ ከተማ አሰተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት 31ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

በሌላ በኩል የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ መሀመድ አሚን ኮምቦልቻ ከተማን በከንቲባነት እንዲመሩ ሾሟቸዋል።

@tikvahethiopia