TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከግንቦት 15 እስከ 20/2014 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሰመራ እና አጋቲና ካምፖች በመባል በሚታወቁ ቦታዎች ውስጥ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ " ለደኅንነታቸው ጥበቃ እና በወንጀል ጥርጣሬ የሚፈለጉ ሰዎችን ለመለየት " በሚል ምክንያት ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ከሆኑ 3 የአፋር ክልል ወረዳዎች ፦
- ከአባላ
- ከኮነባ
- ከበረሃሌ በታኅሣሥ ወር 2014 ዓ/ም ተይዘው የቆዩና በሁለቱ ካምፖች የሚገኙ ወደ 9,000 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ያሉበትን ሁኔታ በቦታው በመገኘት፣ በማነጋገር፣ የመንግሥት አካላትና አገልግሎት ሰጪዎችን እንዲሁም ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማነጋገር ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው በካምፖቹ ውስጥ የሚገኙት ሰዎች ከመኖሪያቸው አካባቢ እንዲወጡና በነዚህ ቦታዎችም እስካሁንም ድረስ እንዲቆዩ የተደረጉት ከፍቃዳቸው ውጪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

በካምፖቹ የሰብአዊ እርዳታና የሕክምና አገልግሎት አቅርቦት እጅግ ውስን በመሆኑና በካምፑ በተከሰተ ወረርሽኝ መሰል በሽታ #ለሕይወት_መጥፋት ጭምር ምክንያት ሆኗል፡፡

በወሊድ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በአካባቢው ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሄዶ ለመታከም ባለመፈቀዱ ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎታል።

ባለፉት አምስት ወራት ሰመራ ካምፕ ብቻ በበሽታ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች እና ካምፑ ውስጥ በወሊድ ወቅት ልጅ የሞተባት እናት መኖራቸውን ተይዘው የሚገኙት ሰዎች አስረድተዋል።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፤ በካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙት ሰዎች ሁኔታ በመጠለያ ጣቢያ ስም የተፈጸመ፣ በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል ብለዋል፡፡

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia