TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ለአንድ ዓመት ጊዜ ዝግጅት ተደርጎበታል የተባለው የመጀመሪያው የሃጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ሰኔ 22 ይካሄዳል። የሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ሰኔ 22 በሚካሄደው መጀመሪያው ዙር የሽልማት መርሐግብር አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ጀምሮ እስከ ዓመት ከስምንት ወር ያሉ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎችን ለመሸለም የታቀደ መሆኑን ባለቤቱ ወ/ሮ ፋንቱ ደምሰው ተናግረዋል። ሰኔ…
ፎቶ፦ ዛሬ ሰኔ 22 ቀን 2014 የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የመጀመሪያ አዋርድ እየተካሄደ ይገኛል።

በስነስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቹን ጨምሮ የውድድሩ እጩዎች እንዲሁም በርካታ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

ስነስርዓቱ የተጀመረው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በማሰብ ሲሆን ቤተሰቦቹን ጨምሮ በአዳራሹ የተገኙ እንግዶች በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆነው ሲያለቅሱ ተስተውሏል።

የሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ሁሌ በየዓመቱ ሰኔ 22 የሚቀጥል ሲሆን በሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን በኩል የሚዘጋጅ ነው።

(Tikvah Family)

Tikvah Ethiopia AFAAN OROMOO
https://t.iss.one/+UTMftkYHBuOGaQ23

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ከግንቦት 15 እስከ 20/2014 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሰመራ እና አጋቲና ካምፖች በመባል በሚታወቁ ቦታዎች ውስጥ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ " ለደኅንነታቸው ጥበቃ እና በወንጀል ጥርጣሬ የሚፈለጉ ሰዎችን ለመለየት " በሚል ምክንያት ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ከሆኑ 3 የአፋር ክልል ወረዳዎች ፦
- ከአባላ
- ከኮነባ
- ከበረሃሌ በታኅሣሥ ወር 2014 ዓ/ም ተይዘው የቆዩና በሁለቱ ካምፖች የሚገኙ ወደ 9,000 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ያሉበትን ሁኔታ በቦታው በመገኘት፣ በማነጋገር፣ የመንግሥት አካላትና አገልግሎት ሰጪዎችን እንዲሁም ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማነጋገር ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ያነጋገራቸው በካምፖቹ ውስጥ የሚገኙት ሰዎች ከመኖሪያቸው አካባቢ እንዲወጡና በነዚህ ቦታዎችም እስካሁንም ድረስ እንዲቆዩ የተደረጉት ከፍቃዳቸው ውጪ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

በካምፖቹ የሰብአዊ እርዳታና የሕክምና አገልግሎት አቅርቦት እጅግ ውስን በመሆኑና በካምፑ በተከሰተ ወረርሽኝ መሰል በሽታ #ለሕይወት_መጥፋት ጭምር ምክንያት ሆኗል፡፡

በወሊድ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በአካባቢው ወደሚገኝ የጤና ተቋም ሄዶ ለመታከም ባለመፈቀዱ ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎታል።

ባለፉት አምስት ወራት ሰመራ ካምፕ ብቻ በበሽታ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች እና ካምፑ ውስጥ በወሊድ ወቅት ልጅ የሞተባት እናት መኖራቸውን ተይዘው የሚገኙት ሰዎች አስረድተዋል።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፤ በካምፕ ውስጥ ተይዘው የሚገኙት ሰዎች ሁኔታ በመጠለያ ጣቢያ ስም የተፈጸመ፣ በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል ብለዋል፡፡

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Sudan የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በአረብኛ ቋንቋ ባሰራጩት መልዕክት የሱዳንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድማማቾች መሆናቸውን ገልፀው በሁለቱ ሀገራት መካከል ችግር መኖሩ ግልፅ ነው ብለዋል። ነገር ግን ሁለቱ ሀገራት እነዚያን ችግሮች ለመፍታት ሊጥሩ እና ሊተባበሩ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ለማጋጨት የሚፈልጉ…
#Update #Ethiopia #Sudan

" መረጃው ውሸት ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

" በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ በተጠንቀቅ ቆሟል " - አቶ አብራራው ተስፋ

" ሱዳን ትሪቡን " የተባለው የሱዳን ሚዲያ የሱዳን ጦር ሰራዊት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኃይሎች ተወሰደብኝ ያለውን እርምጃ ለመበቀል የይገባኛል ጥያቄ በሚናሳበት የአልፋሽጋ አካባቢ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ስር የነበሩ " ካላ ላባን " እና " በረከት " የተባሉ አካባቢዎችን ተቆጣጥሯል ሲል ዘግቧል።

በዘገባውም ላይ የሱዳን ጦር በርካታ የኢትዮጵያ የጦር ተሸከርካሪዎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ  / እንዳቃጠለ ፣ ወታደሮችንም እንደማረከ ገልጿል።

ዛሬ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃላቸውን የሰጡት የኢፌድሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስተር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ መረጃው #ውሸት እንደሆነ አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል በም/ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የሱዳን ጦር አካባቢው እንዳይለማ አልሞ አሁንም ድረስ ከእርቀት መድፍ እየተኮሰ እንደሆነ የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ አብራራው ተስፋ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪም የሱዳን ጦር ትንኮሳውን በአካባቢው ትናንት ማምሻውን ቀጥሎ እንደነበር አስረድተዋል፡፡ 

መድፍ ከእርቀት ከመተኮስ ያለፈ ነገር እንደሌለ የሚናገሩት የወረዳው የሰላምና ደህንነት ኃላፊ ፥ " በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ #በተጠንቀቅ_ቆሟል ነው " ያሉት፡፡ 

ህብረተሰቡ በሚተኮሱት ከባባድ መሳሪያዎች ከመደናገጥ ይልቅ ተደራጅቶ ዘልቀው የሚመጡ ከሆነ እየጠበቀ እንደሆነ ነው ለሬድዮ ጣቢያው ያስረዱት፡፡

@tikvahethiopia
#ZH

ያገለገሉ እና አዲስ ካሜራ እና የካሜራ እቃዎችን እንገዛለን እንሸጣለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ያገኙ https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEUTeB3LSYVFukiuQw

ይደውሉልን 0911284905

አድራሻ= ቦሌ ወሎ ሰፈር HMM ህንፃ 2ኛ ፍቅ 205
#Sudan #June30March

ዛሬ በሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

ዛሬ #June30 በጎረቤት ሱዳን በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራውን ወታደራዊ ጁንታን በመቃወም ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በተቃውሞ ሰልፉ ወታደራዊው ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ እና የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም ይጠየቅበታል ነው የተባለው።

ተቃውሞውን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች የተለያዩ መንገዶችን ዘግተዋል። በተጨማሪ የፀጥታ ኃይሎች ሰልፍ የሚያስተባብሩትን አክቲቪስቶች እያደኑ እያሰሩ ነው ተብሏል።

የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኃላ በሱዳን ዜጎች የሚደርስበት ተቃውሞ እስካሁን የቀጠለ ሲሆን ስልጣኑን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ ግፊት እየተደረገበት ይገኛል።

እስከዛሬ ድረስ በነበሩት ተቃውሞዎች የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች በወሰዷቸው እርምጃዎች ብዙ ሰዎች ሞተዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan #June30March ዛሬ በሱዳን ከፍተኛ ተቃውሞ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። ዛሬ #June30 በጎረቤት ሱዳን በሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን የሚመራውን ወታደራዊ ጁንታን በመቃወም ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። በተቃውሞ ሰልፉ ወታደራዊው ክንፍ በመፈንቅለ መንግስት የያዘውን ስልጣን ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክብ እና የሲቪል መንግስት እንዲቋቋም ይጠየቅበታል…
ሱዳን ኢንተርኔት ዘጋች።

ሱዳን ዛሬ ሀሙስ ከሚካሄደው ታላቁ የ #June30 የተቃውሞ ሰለፍ ጋር በተያያዘ ከጥዋት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጣለች።

የኢንተርኔት ጉዳይን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ ፤ ዛሬ #June30 ሊካሄድ ከታሰበው የሱዳን ፀረ ጁንታ (ወታደራዊ አገዛዝ) ተቃውሞ እና የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ከሚጠይቀው ሰልፍ ጋር በተገናኘ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የናፍጣ እጥረት እና ምክንያቱ ምንድነው ? ከ2 ሳምንታት ወዲህ ከፍተኛ የናፍጣ እጥረት በአዲስ አበባ ከተማ እየተፈጠረ ሲሆን ለምን እጥረቱ እንደተፈጠረ በሚሰጡት ምላሽ ላይ መንግሥትና የነዳጅ አቅራቢዎች ሊግባቡ አልቻሉም፡፡ ማደያዎችና ነዳጅ አመላላሾች እጥረቱ የተፈጠረው ከጂቡቲ የሚመጣ ነዳጅ በመጥፋቱ ነው በማለት መኪኖቻቸው ለቀናት ነዳጅ አጥተው ጂቡቲ መስመር ላይ መቆማቸውን ገልጸዋል፡፡ ቃላቸውን…
#ነዳጅ

" 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ ርምጃ ይወሰዳል " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

ከጂቡቲ ተነስተው አዲስ አበባ እና የተለያዩ ዋና ከተሞች መድረስ የነበረባቸው 200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰዓረላ አብዱላሂ በሰጡት መግለጫ " በተለይ አዲስ አበባና ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ላይ ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት ተከስቷል " ብለዋል።

ይህም በህገወጥ መንገድ የነዳጅ ቦቴዎቹ በየመንደሩ ተደብቀው የኢኮኖሚ አሻጥር በፈጠሩ የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፋር ፣ መተሃራ ፣ በሞጆ ፣ በአዳማ እና በተለያዩ ከተሞች ተደብቀው የተገኙት ቦቴዎች ዛሬ እስከ 10 ሰዓት ድረስ ነዳጁን በሚፈለገው ማደያ ማድረስ እንዳለባቸው ለባለቤቶቹ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

በተጨማሪ 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ ርምጃ እንደሚወስድ ጠቁመው ይህንን ቁጥጥር የሚመራ ግብረሃይል ተቋሟል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች በየመንገዱ እና በየሰፈሩ ተደብቀው የሚቆሙት / ነዳጁን ለማድረስ የሚዘገዩት ገና ለገና የነዳጅ ዋጋ ሲጨምር በአዲሱ ዋጋ ተመን ከፍተኛ ትርፍ ለማግኘት በማሰብ ነው።

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ እጥረት ነዋሪዎች እየተንገላቱ ነው ፤ የህዝብ ትራንስፖርት የሚጠቀመው ነዋሪው ወደ ጉዳዩ ለመሄድ በዚህ ክረምት በዝናብ ረጅም ሰዓት ተሰልፎ ትራንስፖርት ለመጠበቅ ተገዷል። ታክሲዎችም አንድ ቀን ስራ አንድ ቀን የነዳጅ ሰልፍ ላይ ነው የሚውሉት።

(ፎቶ ፦ ከአፋር ክልል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች ዉስጥ እንደሚሰጥ ተገለፀ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሆሳዕና፣ በወራቤና በወልቂጤ ከተሞች የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃና ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸው ወቅት ከተማሪዎችና ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በትምህርት ቤቶች ሳይሆን #በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል። እንደሚኒስትሩ…
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ ይሰጣል ?

የትምህርት ሚኒስቴር የብሄራዊ ፈተና መሰረቅንና ኩረጃን ለመከላከል ፈተናው በኦንላንይ መስጠት እስኪጀመር ድረስ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል።

የፈተናውን አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደም የ2014 ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20 / 2015 ዓ/ም በኃላ እንደሚሰጥ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም ፤ እስካሁን ድረስ የተቀየረም ሆነ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለፀ አዲስ ነገር የለም።

ከትላንት ጀምሮ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ፈተናው ሃምሌ እና ነሃሴ ላይ ነው የሚሰጠው እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ ያልታወቀና ሀሰተኛ በመሆኑ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ በጥናታችሁ ላይ እንድታተኩሩ ወላጆችም ልጆቻችሁ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እገዛችሁን እንድታጠናክሩ ይሁን።

እጅግ በርካታ ተማሪዎች እንዲሁም ወላጆች የሚከታተሉት የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጉዳይን በተመለከተ ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ የሚወጡ መረጃዎችን አምናችሁ አትቀበሉ። አንድን መረጃ ስትሰሙ ከትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን አረጋግጡ።

@tikvahethiopia