TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ያለውን ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (#ሀዋሳ እና #መቅደላ_አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት #በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ተጥሏል።

እግዱ መጣሉን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው።

ይኸው እግድ የተላለፈው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።

የእግዱ መተግበር በአማካኝ ግማሽ ያህል የውጭ ምንዛሬን ሊያስቀር ይችላል ተብሏል።

#ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው እገዳ የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ  ሲሆን እገዳ የተጣለባቸውን ምርቶች ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ መጠየቅ እንደማይቻል የብሄራዊ ባንክ አሳውቋል።

ወደ አገር እንዳይገቡ አገዳ የተጣለባቸው ምርቶች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት #በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ተጥሏል። እግዱ መጣሉን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው። ይኸው እግድ የተላለፈው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ…
ከውጭ እንዳይገቡ እገዳ የተጣለባቸው ምርቶች ዝርዝር ፦

- ከረሜላዎች፣ ማስቲካዎችና ሌሎች ጣፋጭ ዝግጅቶች

- ቸኮሌት

- ብስኩቶች እና ዋፈሮች

- የፍራፍሬ ጭማቂዎች እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች

- ከፍራፍሬ የተዘጋጁ ጃሞች፣ የድንች ጥብሶች ፣

- የታሸጉ ውሃዎች ለስላሳ መጠጦችና አልኮል የሌላቸው መጠጦች

- ውሰኪ፣ ወይን ቢራና ለሎች አልኮል መጠጦች በሙሉ

- ሲጋራ

- ሽቶዎችና ቶይሌት ዋተርስ

- የውበት ወይም የመኳኳያ ዝግጅቶች ፣

- ሳሙናዎች

- ርችቶች

- ቦርሳና ዋሌቶች

- ሳይክሎች

- በታሪፍ ቁጥር 9401 እስከ 9403 የሚመደቡ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች

- የገበታ ጨው

- የተለያዩ መጫወቻ እቃዎች

- የእጅ፣ የጠረጴዛና የግድግዳ ሰአቶች

- ዣንጥላዎች

- ምንጣፎች

- የአሳማ ስጋዎች

- የዶሮ ስጋዎች

- ቱናዎች፣ ሰርዲኖችና ሌሎች የአሳ ምርቶች

- ከህፃናት አልሚ ምግቦችና ወተቶች #በስተቀር የተለያዩ የታሸጉ ምግቦች

- ከሴራሚክስና ፖርስሊን የተዘጋጁ የቤት እቃዎች

- ጋዝ ላይተር

- የተለያዩ የጸጉር ጌጣጌጦች

- ልብስ ማሳያ አሻንጉሊቶች

- ከብርጭቆ የተዘጋጁ የመጠጥ መጠጫ እቃዎች፣ የስጋራ መተርኮሻዎች፣የአበባ መያዣና ተመሳሳይ እቃዎች

- የተታተመ ስዕላዊ መግለጫ ያላቸው ካርዶች፣

- የቀን መቁጠሪያ ካሌንደሮች፣

- ስዕሎች የግድግዳ ሥዕሎች ጨምሮ

- ባርኔጣዎችና ኮፍያዎች

- አርቲፊሻል አበባዎች

- የሰውና አርቴፊሻል ጸጉሮች ፣

- አርቴፊሻል ጌጣጌጦች

- የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢል ና ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች /በኤሌክትሪክ ሞተር የሚሰሩትን ሳይጨምር/

- የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎች /በኤሌክትሪክ ሞተር የሚሰሩትን ሳይጨምር/

@tikvahethiopia