TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HARGEISA

በሶማሊላንድ ሁለተኛ (2) ሰው በኮቪድ-19 መሞቱ ሪፖርት ተደረገ ፤ በዛሬው ዕለት ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው ግለሰብ የሀርጌሳ ነዋሪ ሲሆኑ ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Hargeisa

የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ሶማሌለንድ፣ ሃርጌሳ ይገኛሉ።

የክልሉ ፕሬዜዳንት በእሳቸው የሚመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑካን ቡድንን ይዘው ነው ዛሬ ከሰዓት ሀርጌሳ የገቡት።

ወደሶማሌላንድ ያቀናው ልዑክ ፦ የሶማሊ ክልል ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙባሽር ዲባድ ራጌ፣ የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲራህማን ኢድ ጣሂርና ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራር አካላት የሚገኙበት ነው።

ልዑካን ቡድኑ ከሶማሌላንድ መንግሥት ጋር በጸጥታ፣ በንግድ ትስስርና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Somaliland #US

ዛሬ በሶማሊያ የአሜሪካ አምባሳደር ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ነበሩ።

አምባሳደር ሪቻርስ ሪሌይ ፤ ሶማሌላንድ ሀርጌሳ ሄደው ከሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ጋር መክረዋል።

ከሌሎችም ከፍተኛ የፖለቲካ መሪዎች ፣ የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋርም መወያየታቸው ተሰምቷል።

አምባሳደሩ ፤ አሜሪካ በቀጠናው ብልጽግናን እና የዴሞክራሲ ተቋማትን ለመደገፍ የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት እንዳላት አረጋግጠዋል።

ዲፕሎማሲያዊ እና የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ቀጠናዊ ትብብር እና ውይይትን ያበረታቱም ሲሆን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር የምርጫ ጊዜን በማክበር አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

ከግሉ ሴክተር መሪዎች ጋር በመገናኘት ከአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ ጋር ግንኙነት እንዴት እንደሚጠናከር መነጋገራቸው ታውቋል።

የነቃ ሲቪል ማህበረሰብ እና ነፃና ሙያዊ ስርዓቱን ያከበረ ፕሬስ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል ተብሏል።

ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂም ከአሜሪካው አምባሳደር ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን አሳውቀዋል።

በቀጠናዊ ጉዳዮች ፣ በአፍሪካ ቀንድ ትብብርን ማጎልበት ፣ በምርጫ ጉዳይ ፣ በሶማሌላንድ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

በሶማሊያ፣ ሞቃዲሹ ያለው ኤምባሲ የዛሬውን የአምባሳደሩን የሀርጌሳ ጉብኝት በተመለከተ ያሰራጨውን የጽሁፍ መግለጫን አንዳንዶች ' ያልተለመደ ነው ' ብለውታል።

ሀገሪቱ " ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ ፤ የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንት " እያለች መጥራቷ በቋንቋ አጠቃቀም ላይ የታየ ጉልህ ለውጥ ነው ያሉ አልጠፉም።

የአምባሳደሩን ሀርጌሳ ላይ መገኘትን የኮነኑም አሉ። ገለልተኛ አይደሉም ሶማሊያን ይደግፋሉ በሚል።

ሶማሊያውያን ደግሞ በየማህበራዊ ሚዲያ ላይ አሜሪካን መቃወም ይዘዋል።

" መግላጫው ሶማሌላድ ስለ ተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ምንም ያለው ነገር የለም " በማለት እንዲሁም " ሶማሌላንድ የሶማሊያ ግዛት እንደሆነች ሳይገለጽ መቅረቡ ሌላ ነገር ከጀርባው የያዘ ነው " በሚል ነው የተቃወሙ ያሉት።

#Somaliland
#Hargeisa

@tikvahethiopia